caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ar-Ra'd፣ አንቀጽ 31

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 96 · 13:31

وَلَوْ أَنَّ قُرْءَانًا سُيِّرَتْ بِهِ ٱلْجِبَالُ أَوْ قُطِّعَتْ بِهِ ٱلْأَرْضُ أَوْ كُلِّمَ بِهِ ٱلْمَوْتَىٰ بَل لِّلَّهِ ٱلْأَمْرُ جَمِيعًا أَفَلَمْ يَا۟يْـَٔسِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَن لَّوْ يَشَآءُ ٱللَّهُ لَهَدَى ٱلنَّاسَ جَمِيعًا وَلَا يَزَالُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ تُصِيبُهُم بِمَا صَنَعُوا۟ قَارِعَةٌ أَوْ تَحُلُّ قَرِيبًا مِّن دَارِهِمْ حَتَّىٰ يَأْتِىَ وَعْدُ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُخْلِفُ ٱلْمِيعَادَ

Amharic Translation - Africa Academy31. ቁርኣንም በእርሱ ተራራዎች የሚነዱበት፤ ወይም በእርሱ ምድር የሚቆራረጥበት፤ ወይም በእርሱ ሙታን እንዲናገሩ የሚደረጉበት ቢሆን ኖሮ (ይሀው ቁርአን በሆነ ነበር።) በእውነቱ ነገሩ ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያ በአላህ ያመኑት ሰዎች እነሆ አላህ በሻ ኖሮ ሰዎችን በመላ በእርግጥ ወደ ቀናው መንገድ ይመራቸው እንደ ነበረ አያውቁምን? እነዚያን የካዱት በሥራቸው ምክንያት አጥፊ አደጋ የምታገኛቸው ከመሆን ወይም የአላህ ቀጠሮ እስኪ መጣ በሀገራቸው አቅራቢያ አንተ የምትሰፍርባቸው ከመሆን አይወገዱም:: አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqቁርኣንም በእርሱ ተራራዎች በተነዱበት ወይም በእርሱ ምድር በተቆራረጠችበት ወይም በእርሱ ሙታን እንዲናገሩ በተደረጉበት ኖሮ ( ከሓዲዎች ባላመኑ ነበር)፡፡ በእውነቱ ነገሩ ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑት ሰዎች እነሆ አላህ በሻ ኖሮ ሰዎችን በመላ በእርግጥ ይመራቸው እንደነበረ አያውቁምን? እነዚያም የካዱት በሥራቸው ምክንያት (አጥፊ) ዐደጋ የምታገኛቸው ከመኾን ወይም የአላህ ቀጠሮ እስኪመጣ በአገራቸው አቅራቢያ (አንተ) የምትሰፍርባቸው ከመኾን አይወገዱም፡፡ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70