وَٱلَّذِينَ ءَاتَيْنَٰهُمُ ٱلْكِتَٰبَ يَفْرَحُونَ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمِنَ ٱلْأَحْزَابِ مَن يُنكِرُ بَعْضَهُۥ قُلْ إِنَّمَآ أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ ٱللَّهَ وَلَآ أُشْرِكَ بِهِۦٓ إِلَيْهِ أَدْعُوا۟ وَإِلَيْهِ مَـَٔابِ
Amharic Translation - Africa Academy36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም መጽሐፉን የሰጠናቸውን ወደ አንተ በተወረደው ይደሰታሉ:: ከአህዛብም ከፊሉን የሚክዱ ሰዎች አሉ። «እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድገዛና በእርሱም እንዳላጋራ ነው። ወደ እርሱ እጠራለሁ:: መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም መጽሐፉን የሰጠናቸው ወዳንተ በተወረደው ይደሰታሉ፡፡ ከአሕዛብም ከፊሉን የሚክዱ ሰዎች አልሉ፡፡ «እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድገዛ በእርሱም እንዳላጋራ ነው፡፡ ወደእርሱ እጠራለሁ፤ መመለሻዬም ወደእርሱ ነው» በላቸው፡፡