ٱللَّهُ ٱلَّذِى رَفَعَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ بِغَيْرِ عَمَدٍ تَرَوْنَهَا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ كُلٌّ يَجْرِى لِأَجَلٍ مُّسَمًّى يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ يُفَصِّلُ ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّكُم بِلِقَآءِ رَبِّكُمْ تُوقِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy2. አላህ ያ ሰማያትን የምታይዋት ቋሚዎች ሳይኖራት በችሎታው ከፍ ያረጋት፤ ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ፤ ጸሐይንና ጨረቃንም የገራ ነው:: ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ:: ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል:: ከጌታችሁ ጋር መገናኘትን ታረጋግጡ ዘንድ ተዓምራትን ይዘረዝራል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ያ ሰማያትን የምታዩዋት አዕማድ ሳትኖር ያነሳት፤ ከዚያም በዐርሹ (ዙፋኑ) ላይ (ለሱ ክብር በሚስማማ መልኩ) የተደላደለ፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ያገራ ነው፡፡ ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ፡፡ ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል፡፡ በጌታችሁ መገናኘት ታረጋግጡ ዘንድ ተዓምራቶችን ይዘረዝራል፡፡