وَفِى ٱلْأَرْضِ قِطَعٌ مُّتَجَٰوِرَٰتٌ وَجَنَّٰتٌ مِّنْ أَعْنَٰبٍ وَزَرْعٌ وَنَخِيلٌ صِنْوَانٌ وَغَيْرُ صِنْوَانٍ يُسْقَىٰ بِمَآءٍ وَٰحِدٍ وَنُفَضِّلُ بَعْضَهَا عَلَىٰ بَعْضٍ فِى ٱلْأُكُلِ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4. በምድርም ውስጥ የተጎራበቱ ቁርጥራጮች አሉ:: የወይኖች አትክልቶችም፤ አዝርዕቶችም መንታዎችና መንታዎች ያልሆኑ ዘንባባዎችም አሉ:: በአንድ ውሃ ይጠጣሉ:: በጣዕም ግን ይለያያሉ ከፊልዋንም በከፊሉ ላይ በሚበላው ሰብል እናበልጣለን:: በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ ብዙ ተአምራት አለበት::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበምድርም የተጎራበቱ ቁርጥራጮች አልሉ፡፡ ከወይኖችም አትክልቶች አዝርዕቶችም መንታዎችና መንታዎች ያልኾኑ ዘንባባዎችም አልሉ፡፡ በአንድ ውሃ ይጠጣሉ፤ (በጣዕምም ይለያያሉ)፡፡ ከፊሉዋንም በከፊሉ ላይ በሚበላው ሰብል እናበልጣለን፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ተዓምራት አለበት፡፡