caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yusuf يوسف

111 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 53

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓر تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْمُبِينِ

Amharic Translation - Africa Academy1.አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ አናቅጽ ግልጽና የተብራራ ከሆነው መጽሐፍ አናቅጽ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy2. እኛ ይህንን ቁርኣንን ትረዱት ዘንድ በዐረበኛ ቋንቋ አወረድነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نَحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ أَحْسَنَ ٱلْقَصَصِ بِمَآ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانَ وَإِن كُنتَ مِن قَبْلِهِۦ لَمِنَ ٱلْغَٰفِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህንን የቁርኣን ወደ አንተ በማውረዳችን እጅግ ውብና ማራኪ የሆነ ታሪክ እንተርክልሃለን:: ከዚህ በፊት አንተም ይህንን ታሪክ ከማያውቁት ነበርክ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ يُوسُفُ لِأَبِيهِ يَٰٓأَبَتِ إِنِّى رَأَيْتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوْكَبًا وَٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ رَأَيْتُهُمْ لِى سَٰجِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነብዩ ዩሱፍ በልጅነቱ ለአባቱ «አባቴ ሆይ! እኔ አስራ አንድ ኮከቦችን፤ ጨረቃንና ጸሐይን ሲሰግዱልኝ በሕልሜ አየሁኝ።» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ ለህዝቦችህ አስታውስ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ يَٰبُنَىَّ لَا تَقْصُصْ رُءْيَاكَ عَلَىٰٓ إِخْوَتِكَ فَيَكِيدُوا۟ لَكَ كَيْدًا إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ لِلْإِنسَٰنِ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy5. አባቱም አለ: «ልጄ ሆይ! ይህን ህልምህን ለወንድሞችህ አትንገር። ባንተ ላይ ተንኮል እንዳያሴሩ። ምክንያቱም ሰይጣን ለሰው ልጅ ሁልጊዜም ግልጽ ጠላት ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ يَجْتَبِيكَ رَبُّكَ وَيُعَلِّمُكَ مِن تَأْوِيلِ ٱلْأَحَادِيثِ وَيُتِمُّ نِعْمَتَهُۥ عَلَيْكَ وَعَلَىٰٓ ءَالِ يَعْقُوبَ كَمَآ أَتَمَّهَا عَلَىٰٓ أَبَوَيْكَ مِن قَبْلُ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْحَٰقَ إِنَّ رَبَّكَ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy6. «ጌታህ ልክ ይህን ህልም እንዳሳየህ ሁሉ ለነብይነትም ይመርጥሃል:: የንንግግሮችን ፍፃሜ ያስተምርሃል:: ጸጋውንም ቀደም ሲል ለአባቶችህ ለኢብራሂምና ለኢስሃቅ እንደሞላ ሁሉ ላንተና ለያዕቁብ ቤተሰቦችም ይሞላል:: ጌታህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّقَدْ كَانَ فِى يُوسُفَ وَإِخْوَتِهِۦٓ ءَايَٰتٌ لِّلسَّآئِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy7. በዩሱፍና በወንድሞቹ ታሪክ ዉስጥ እውቀትን በመሻት ለሚጠይቁ ሁሉ እያሌ ተዓምራት አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالُوا۟ لَيُوسُفُ وَأَخُوهُ أَحَبُّ إِلَىٰٓ أَبِينَا مِنَّا وَنَحْنُ عُصْبَةٌ إِنَّ أَبَانَا لَفِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) ባሉ ጊዜ: «እኛ በቁጥር ብዙዎች ሁነን እያለ ዩሱፍና ወንድሙ (ብንያም) ከአባታችን ዘንድ ከእኛ ይበልጥ ተወዳጆች ናቸው:: በእውነቱ አባታችን ግልጽ ስህተት ውስጥ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱقْتُلُوا۟ يُوسُفَ أَوِ ٱطْرَحُوهُ أَرْضًا يَخْلُ لَكُمْ وَجْهُ أَبِيكُمْ وَتَكُونُوا۟ مِنۢ بَعْدِهِۦ قَوْمًا صَٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy9. «ዩሱፍን ግደሉት ወይም እሩቅ ቦታ ጣሉት:: ይህን ካረጋችሁ የአባታችሁን ፊት ትኩረትና ውዴታ የራሳችሁ ብቻ ታደርጋላችሁ:: ከዚህ በኋላ ከኃጥያታችሁ በመመለስ መልካም ሰዎች ትሆናለችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ قَآئِلٌ مِّنْهُمْ لَا تَقْتُلُوا۟ يُوسُفَ وَأَلْقُوهُ فِى غَيَٰبَتِ ٱلْجُبِّ يَلْتَقِطْهُ بَعْضُ ٱلسَّيَّارَةِ إِن كُنتُمْ فَٰعِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy10. ከእነሱ አንድ ተናጋሪ «ዩሱፍን አትግደሉ ግን በጉድጓድ አዘቅት ጨለማ ውስጥ ጣሉት፤ ከተጓዢዎች አንዱ ያነሳዋልና፡፡ ሠሪዎች ብትኾኑ (በዚሁ ተብቃቁ) አላቸው፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ يَٰٓأَبَانَا مَا لَكَ لَا تَأْمَ۫نَّا عَلَىٰ يُوسُفَ وَإِنَّا لَهُۥ لَنَٰصِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. አሉም: «አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ጉዳይ እኛ ለእርሱ ቅን አሳቢዎች ሁነን ሳለ ለምን አታምነንም?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَرْسِلْهُ مَعَنَا غَدًا يَرْتَعْ وَيَلْعَبْ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ

Amharic Translation - Africa Academy12. «እስቲ ይዝናና ይጫወት ዘንድ ነገ ከእኛ ጋር አብረህ ላከው::እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ إِنِّى لَيَحْزُنُنِىٓ أَن تَذْهَبُوا۟ بِهِۦ وَأَخَافُ أَن يَأْكُلَهُ ٱلذِّئْبُ وَأَنتُمْ عَنْهُ غَٰفِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy13. አባቱም «እርሱን መውሰዳችሁ ያሳዝነኛል። ዘንግታችሁት ተኩላ እንዳይበላዉም እፈራለሁ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ لَئِنْ أَكَلَهُ ٱلذِّئْبُ وَنَحْنُ عُصْبَةٌ إِنَّآ إِذًا لَّخَٰسِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. እነርሱም «እኛ እንዲህ ጭፍሮች ሆነን ተኩላ ከበላውማ ከሳሪዎቹ እኛ ነን።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا ذَهَبُوا۟ بِهِۦ وَأَجْمَعُوٓا۟ أَن يَجْعَلُوهُ فِى غَيَٰبَتِ ٱلْجُبِّ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِ لَتُنَبِّئَنَّهُم بِأَمْرِهِمْ هَٰذَا وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy15. እርሱንም ወስደውት በጉድጓድ ወለል ላይ ሊጥሉት በወሰኑ ጊዜ «እነርሱ ሳያውቁ ይህን ጸያፍ ተግባራቸውን ወደ ፊት ትነግራቸዋለህ» የሚል መልዕክት ላክንለት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَآءُوٓ أَبَاهُمْ عِشَآءً يَبْكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy16. አባታቸውንም በምሽት እያለቀሱ መጡት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ يَٰٓأَبَانَآ إِنَّا ذَهَبْنَا نَسْتَبِقُ وَتَرَكْنَا يُوسُفَ عِندَ مَتَٰعِنَا فَأَكَلَهُ ٱلذِّئْبُ وَمَآ أَنتَ بِمُؤْمِنٍ لَّنَا وَلَوْ كُنَّا صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy17. «አባታችን ሆይ! እኛ ለሩጫና ለውርወራ ልንሽቀዳደም ሄድን። ዩሱፍንም እቃችን ዘንድ ተውነው:: ወዲያዉም ተኩላ በላው:: አንተም እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَآءُو عَلَىٰ قَمِيصِهِۦ بِدَمٍ كَذِبٍ قَالَ بَلْ سَوَّلَتْ لَكُمْ أَنفُسُكُمْ أَمْرًا فَصَبْرٌ جَمِيلٌ وَٱللَّهُ ٱلْمُسْتَعَانُ عَلَىٰ مَا تَصِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy18. በቀሚሱም ላይ የውሸትን ደም አመጡ:: አባታቸውም: «ይህ ትክክል አይደለም። ይልቁን ነፍሶቻችሁ ውሸት ነገርን ለናንተ ሸለሙላችሁ:: ስለዚህ መልካም ትዕግስት ማድረግ አለብኝ:: በምትሉትም ነገር ላይ መታገዣው አላህ ብቻ ነው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَآءَتْ سَيَّارَةٌ فَأَرْسَلُوا۟ وَارِدَهُمْ فَأَدْلَىٰ دَلْوَهُۥ قَالَ يَٰبُشْرَىٰ هَٰذَا غُلَٰمٌ وَأَسَرُّوهُ بِضَٰعَةً وَٱللَّهُ عَلِيمٌۢ بِمَا يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. መንገደኞችም መጡ:: ውሃ ቀጂያቸውንም ላኩ:: አኮሌውንም ወደ ጉድጎዱ ሰደደ:: የምስራች:: «ይህ ልጅ ነው።» አለ:: ሸቀጥ አድርገዉም ደበቁት:: አላህ የሚሠሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَشَرَوْهُ بِثَمَنٍۭ بَخْسٍ دَرَٰهِمَ مَعْدُودَةٍ وَكَانُوا۟ فِيهِ مِنَ ٱلزَّٰهِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy20. በርካሽ ዋጋና በሚቆጠሩ ዲርሃሞች ሸጡት:: በእርሱም ላይ ከቸልተኞቹ ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِى ٱشْتَرَىٰهُ مِن مِّصْرَ لِٱمْرَأَتِهِۦٓ أَكْرِمِى مَثْوَىٰهُ عَسَىٰٓ أَن يَنفَعَنَآ أَوْ نَتَّخِذَهُۥ وَلَدًا وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِى ٱلْأَرْضِ وَلِنُعَلِّمَهُۥ مِن تَأْوِيلِ ٱلْأَحَادِيثِ وَٱللَّهُ غَالِبٌ عَلَىٰٓ أَمْرِهِۦ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ «ይህ ልጅ መኖሪያውን አክብሪ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጅላልና።» አላት:: ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ገዥ ልናደርገውና የሕልሞችንም ፍች ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ አሸናፊ ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥٓ ءَاتَيْنَٰهُ حُكْمًا وَعِلْمًا وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy22. ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው:: ልክ እንደዚህም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرَٰوَدَتْهُ ٱلَّتِى هُوَ فِى بَيْتِهَا عَن نَّفْسِهِۦ وَغَلَّقَتِ ٱلْأَبْوَٰبَ وَقَالَتْ هَيْتَ لَكَ قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِ إِنَّهُۥ رَبِّىٓ أَحْسَنَ مَثْوَاىَ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. ያችም እርሱ በቤትዋ የነበረባት ሴት ከነፍሱ አባበለችው:: ደጃፎቹንም ዘጋችና «ይኸው ላንተ ተዘጋጂቼልሃለሁና ቶሎ በል» አለችው:: እሱም «ከዚህ ጸያፍ ተግባር በአላህ እጠበቃለሁ:: እርሱ የገዘኝ ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና አልከዳዉም:: እነሆ በደለኞች ሁሉ አይድኑምና» አላት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ هَمَّتْ بِهِۦ وَهَمَّ بِهَا لَوْلَآ أَن رَّءَا بُرْهَٰنَ رَبِّهِۦ كَذَٰلِكَ لِنَصْرِفَ عَنْهُ ٱلسُّوٓءَ وَٱلْفَحْشَآءَ إِنَّهُۥ مِنْ عِبَادِنَا ٱلْمُخْلَصِينَ

Amharic Translation - Africa Academy24. በእርሱም በእርግጥ አሰበች፡፡ በእርሷም አሰበ ፡፡የጌታውን ማስረጃ ባላዬ ኖሮ (በእርሷም ባሰበ ነበር) ፡፡ልክ እንደዚሁ መጥፎ ነገርንና ኃጢአትን ከእርሱ ላይ ልንመልስለት አስረጃችንን አሳየነው ፡፡እርሱ ከተጠበቁት ባሮቻችን አንዱ ነዉና ፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱسْتَبَقَا ٱلْبَابَ وَقَدَّتْ قَمِيصَهُۥ مِن دُبُرٍ وَأَلْفَيَا سَيِّدَهَا لَدَا ٱلْبَابِ قَالَتْ مَا جَزَآءُ مَنْ أَرَادَ بِأَهْلِكَ سُوٓءًا إِلَّآ أَن يُسْجَنَ أَوْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy25. እርሱና እርሷ በሩን ተሸቀዳደሙና ቀሚሱን ከኋላው ቀደደችው። ባለቤትዋን እበሩ አጠገብ አገኙት:: እርሷም ቀደም ብላ «በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጂ ሌላ አይደለም።» አለችው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ هِىَ رَٰوَدَتْنِى عَن نَّفْسِى وَشَهِدَ شَاهِدٌ مِّنْ أَهْلِهَآ إِن كَانَ قَمِيصُهُۥ قُدَّ مِن قُبُلٍ فَصَدَقَتْ وَهُوَ مِنَ ٱلْكَٰذِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy26. ዩሱፍም «እርሷ ናት ከነፍሴ ያባበለችኝ።» አለ:: ከቤተሰቦቿም አንድ መስካሪ (እንዲህ) መሰከረ: «ቀሚሱ ከበስተፊት ተቀዶ ከሆነ እርሷ እውነት ተናገረች:: እርሱ ከውሸታሞቹ አንዱ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن كَانَ قَمِيصُهُۥ قُدَّ مِن دُبُرٍ فَكَذَبَتْ وَهُوَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy27. «ቀሚሱም ከበስተኋላው ተቀዶ እንደሆነ ዋሸች:: እርሱም ከእውነተኞቹ ነው።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا رَءَا قَمِيصَهُۥ قُدَّ مِن دُبُرٍ قَالَ إِنَّهُۥ مِن كَيْدِكُنَّ إِنَّ كَيْدَكُنَّ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy28. ቀሚሱንም ከበስተኋላ ተቀዶ ባየ ጊዜ አለ: «እርሱ የተናገርሽው ከተንኮላችሁ ነው። የእንናንተ የሴቶች ተንኮል በእርግጥ ብርቱ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُوسُفُ أَعْرِضْ عَنْ هَٰذَا وَٱسْتَغْفِرِى لِذَنۢبِكِ إِنَّكِ كُنتِ مِنَ ٱلْخَاطِـِٔينَ

Amharic Translation - Africa Academy29. «ዩሱፍ ሆይ! አንተም ከዚህ ወሬ ተከልከል:: አንቺም ለኃጢአትሽ ማርታን ለምኝ። አንቺ ከስሕተተኞቹ ሆነሻልና።» አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ نِسْوَةٌ فِى ٱلْمَدِينَةِ ٱمْرَأَتُ ٱلْعَزِيزِ تُرَٰوِدُ فَتَىٰهَا عَن نَّفْسِهِۦ قَدْ شَغَفَهَا حُبًّا إِنَّا لَنَرَىٰهَا فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy30. በከተማው ያሉ ሴቶችም «የዐዚዝ ሚስት ሰራተኛዋን ከነፍሱ ታባብለዋለች:: በእውነቱ ፍቅሩ ልቧን መቷታል:: እኛ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ሆና በእርግጥ እናያታለን።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا سَمِعَتْ بِمَكْرِهِنَّ أَرْسَلَتْ إِلَيْهِنَّ وَأَعْتَدَتْ لَهُنَّ مُتَّكَـًٔا وَءَاتَتْ كُلَّ وَٰحِدَةٍ مِّنْهُنَّ سِكِّينًا وَقَالَتِ ٱخْرُجْ عَلَيْهِنَّ فَلَمَّا رَأَيْنَهُۥٓ أَكْبَرْنَهُۥ وَقَطَّعْنَ أَيْدِيَهُنَّ وَقُلْنَ حَٰشَ لِلَّهِ مَا هَٰذَا بَشَرًا إِنْ هَٰذَآ إِلَّا مَلَكٌ كَرِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy31. እርሷም ሐሜታቸውን በሰማች ጊዜ ወደነሱ ላከችባቸው:: ግብዣንም ለእነርሱ አዘጋጀችላቸው:: ለያንዳንዳቸዉም ቢላዋን ሰጠችና «በእነርሱም ላይ ውጣ።» አለችው:: እነርሱም በተመለከቱት ጊዜ በጣም አደነቁት:: እጆቻቸዉንም ቆረጡ። «ለአላህ ጥራት ይገባው:: ይህ ሰው አይደለም:: ይህ የተከበረ መልአክ እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَتْ فَذَٰلِكُنَّ ٱلَّذِى لُمْتُنَّنِى فِيهِ وَلَقَدْ رَٰوَدتُّهُۥ عَن نَّفْسِهِۦ فَٱسْتَعْصَمَ وَلَئِن لَّمْ يَفْعَلْ مَآ ءَامُرُهُۥ لَيُسْجَنَنَّ وَلَيَكُونًا مِّنَ ٱلصَّٰغِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy32. በዚህ ጊዜ «ይህ እኮ ነው ያ በእርሱ ፍቅር ያማችሁኝ ሰው:: በእርግጥም ከነፍሱ አባባልኩት ግና እርሱ እንቢ አለ:: ወደፊትም የማዘውን ነገር ባይሠራ በእርግጥ ይታሰራል ከወራዶቹም ይሆናል።» አለች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ ٱلسِّجْنُ أَحَبُّ إِلَىَّ مِمَّا يَدْعُونَنِىٓ إِلَيْهِ وَإِلَّا تَصْرِفْ عَنِّى كَيْدَهُنَّ أَصْبُ إِلَيْهِنَّ وَأَكُن مِّنَ ٱلْجَٰهِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy33. «ጌታዬ ሆይ! ወደ እርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ ነው:: ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደ እነርሱ እዘነበላለሁ:: ከስሕተተኞቹም እሆናለሁ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱسْتَجَابَ لَهُۥ رَبُّهُۥ فَصَرَفَ عَنْهُ كَيْدَهُنَّ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy34. ጌታዉም ጸሎቱን ተቀበለው፤ ተንኮላቸውንም ከእርሱ መለሰለት:: እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ بَدَا لَهُم مِّنۢ بَعْدِ مَا رَأَوُا۟ ٱلْـَٔايَٰتِ لَيَسْجُنُنَّهُۥ حَتَّىٰ حِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy35. ከዚያም ማስረጃዎችን ካዩ በኋላ እስከ ጊዜ ድረስ እንዲያስሩት ለእነርሱ ታያቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَدَخَلَ مَعَهُ ٱلسِّجْنَ فَتَيَانِ قَالَ أَحَدُهُمَآ إِنِّىٓ أَرَىٰنِىٓ أَعْصِرُ خَمْرًا وَقَالَ ٱلْـَٔاخَرُ إِنِّىٓ أَرَىٰنِىٓ أَحْمِلُ فَوْقَ رَأْسِى خُبْزًا تَأْكُلُ ٱلطَّيْرُ مِنْهُ نَبِّئْنَا بِتَأْوِيلِهِۦٓ إِنَّا نَرَىٰكَ مِنَ ٱلْمُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy36. ከእሱም ጋር ሁለት ወጣቶች እስር ቤቱ ገቡ:: አንደኛቸው «እኔ በሕልሜ የወይን ጠጅን ስጠምቅ አየሁ።» አለ:: ሌላው ደግሞ «እኔ በራሴ ላይ ቂጣን ተሸክሜ ከእሱ በራሪ አሞራ ስትበላ አየሁ ፍችውን ንገረን እኛ ከአሳማሪዎች ሁነህ እናይሃለንና።» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لَا يَأْتِيكُمَا طَعَامٌ تُرْزَقَانِهِۦٓ إِلَّا نَبَّأْتُكُمَا بِتَأْوِيلِهِۦ قَبْلَ أَن يَأْتِيَكُمَا ذَٰلِكُمَا مِمَّا عَلَّمَنِى رَبِّىٓ إِنِّى تَرَكْتُ مِلَّةَ قَوْمٍ لَّا يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَهُم بِٱلْـَٔاخِرَةِ هُمْ كَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy37. ዩሱፍም አለ: «ማንኛዉም የምትሰጡት ምግብ ለእናንተ ከመምጣቱ በፊት ፍችውን የምነግራችሁ ቢሆን እንጂ አይመጣላችሁም:: ይህ ጉዳይ ጌታዬ ካሳወቀኝ ነገር ነው:: እኔም በአላህ የማያምኑትንና በመጨረሻይቱ ዓለም ከሓዲያን የሆኑ ሕዝቦችን ሃይማኖት ትቻለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتَّبَعْتُ مِلَّةَ ءَابَآءِىٓ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ مَا كَانَ لَنَآ أَن نُّشْرِكَ بِٱللَّهِ مِن شَىْءٍ ذَٰلِكَ مِن فَضْلِ ٱللَّهِ عَلَيْنَا وَعَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy38. «የአባቶቼንም የኢብራሂምን፤ የኢስሐቅንና የያዕቁብን ሃይማኖት ተከትያለሁ:: ለእኛ በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም:: ያ አለማጋራት በእኛ ላይና በሰዎች ላይ የአላህ ችሮታ ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰصَٰحِبَىِ ٱلسِّجْنِ ءَأَرْبَابٌ مُّتَفَرِّقُونَ خَيْرٌ أَمِ ٱللَّهُ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّارُ

Amharic Translation - Africa Academy39. «የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን ወይስ አሸናፊውና አንዱ አላህ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِهِۦٓ إِلَّآ أَسْمَآءً سَمَّيْتُمُوهَآ أَنتُمْ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلْطَٰنٍ إِنِ ٱلْحُكْمُ إِلَّا لِلَّهِ أَمَرَ أَلَّا تَعْبُدُوٓا۟ إِلَّآ إِيَّاهُ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلْقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy40. «ከእርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ አማልክት ብላችሁ የጠራችኋቸውን ስሞች እንጂ አትገዙም። አላህ በእርሷ ምንም አስረጂ አላወረደም። ፍርዱ የአላህ እንጂ ሌላ አይደለም:: እርሱን እንጂ ሌላን እንዳትገዙም አዟል:: ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰصَٰحِبَىِ ٱلسِّجْنِ أَمَّآ أَحَدُكُمَا فَيَسْقِى رَبَّهُۥ خَمْرًا وَأَمَّا ٱلْـَٔاخَرُ فَيُصْلَبُ فَتَأْكُلُ ٱلطَّيْرُ مِن رَّأْسِهِۦ قُضِىَ ٱلْأَمْرُ ٱلَّذِى فِيهِ تَسْتَفْتِيَانِ

Amharic Translation - Africa Academy41. «የአስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! አንደኛችሁማ ንጉሡን ጠጅ ያጠጣል። ሌላውም ይሰቀላል:: ከራሱም በራሪ አሞራ ትበላለች:: ያ ፍቹን የምትጠይቁት ነገር ተፈጸመ።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ لِلَّذِى ظَنَّ أَنَّهُۥ نَاجٍ مِّنْهُمَا ٱذْكُرْنِى عِندَ رَبِّكَ فَأَنسَىٰهُ ٱلشَّيْطَٰنُ ذِكْرَ رَبِّهِۦ فَلَبِثَ فِى ٱلسِّجْنِ بِضْعَ سِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy42. ለዚያም ከሁለቱ እርሱ የሚድን መሆኑን ለተጠራጠረው እጌታህ ዘንድ አስታውሰኝ አለው፡፡ ጌታውንም ከማስታወስ ሰይጣን አስረሳው፡፡ ለጥቂት ዓመታትም በወህኒ ቤቱ ውስጥ ቆየ፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلْمَلِكُ إِنِّىٓ أَرَىٰ سَبْعَ بَقَرَٰتٍ سِمَانٍ يَأْكُلُهُنَّ سَبْعٌ عِجَافٌ وَسَبْعَ سُنۢبُلَٰتٍ خُضْرٍ وَأُخَرَ يَابِسَٰتٍ يَٰٓأَيُّهَا ٱلْمَلَأُ أَفْتُونِى فِى رُءْيَٰىَ إِن كُنتُمْ لِلرُّءْيَا تَعْبُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy43. ንጉሡም «እኔ ሰባት የሰቡ ላሞችን ሰባት የከሱ ላሞች ሲበሉዋቸው፤ ሰባት ለምለም ዘለላዎችም ሌሎች ሰባት ደረቆችን ስብርብር ሲያደርጉ በሕልሜ አየሁ:: እናንተ ታላላቅ ሰዎች ሆይ! ሕልም መፍታት የምታውቁ ከሆናችሁ ሕልሜን ፍቱልኝ።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ أَضْغَٰثُ أَحْلَٰمٍ وَمَا نَحْنُ بِتَأْوِيلِ ٱلْأَحْلَٰمِ بِعَٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy44. «ሕልሞችህ ቅዠቶች ናቸው:: እኛም የሕልሞችን ፍች አዋቂዎች አይደለንም።» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلَّذِى نَجَا مِنْهُمَا وَٱدَّكَرَ بَعْدَ أُمَّةٍ أَنَا۠ أُنَبِّئُكُم بِتَأْوِيلِهِۦ فَأَرْسِلُونِ

Amharic Translation - Africa Academy45. ያም ከሁለቱ መካከል የዳነውና ከብዙ ጊዜ በኋላ ዩሱፍን ያስታወሰው ሰው «እኔ ፍቹን እነግራችኋለሁና ላኩኝ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُوسُفُ أَيُّهَا ٱلصِّدِّيقُ أَفْتِنَا فِى سَبْعِ بَقَرَٰتٍ سِمَانٍ يَأْكُلُهُنَّ سَبْعٌ عِجَافٌ وَسَبْعِ سُنۢبُلَٰتٍ خُضْرٍ وَأُخَرَ يَابِسَٰتٍ لَّعَلِّىٓ أَرْجِعُ إِلَى ٱلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy46. «አንተ እውነተኛው ዩሱፍ ሆይ! ሰባትን የሰቡ ላሞች ሰባት ከሲታዎች ላሞች ሲበሏቸው፤ ሰባትን ለምለም ዘለላዎችም ሌሎች ሰባት ደረቆች በእነርሱ ላይ ስብርብር ሲያደርጉ ያየን ሰው ሕልም ፍች እስቲ ተችልን:: ያውቁ ዘንድ ወደ ሰዎቹ ልመለስ እከጅላለሁና።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ تَزْرَعُونَ سَبْعَ سِنِينَ دَأَبًا فَمَا حَصَدتُّمْ فَذَرُوهُ فِى سُنۢبُلِهِۦٓ إِلَّا قَلِيلًا مِّمَّا تَأْكُلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy47. እርሱም አለ: «ሰባትን የተከታተሉ ዓመታት ትዘራላችሁ ያጨዳችሁትንም ሁሉ ከምትበሉት ጥቂት በስተቀር በዘለላው ውስጥ ተውት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ يَأْتِى مِنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ سَبْعٌ شِدَادٌ يَأْكُلْنَ مَا قَدَّمْتُمْ لَهُنَّ إِلَّا قَلِيلًا مِّمَّا تُحْصِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. «ከዚያም ከነዚያ በኋላ ካደለባችሁት ጥቂት ሲቀር ለእነርሱ ያደለባችሁትን ሁሉ የሚበሉ ሰባት የችግር ዓመታት ይመጣሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ يَأْتِى مِنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ عَامٌ فِيهِ يُغَاثُ ٱلنَّاسُ وَفِيهِ يَعْصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy49. «ከዚያ ከእነዚያ በኋላ ሰዎቹ በእርሱ ዝናብ የሚያገኙበትና በእርሱም ወይንን የሚጨምቁበት ዓመት ይመጣል።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلْمَلِكُ ٱئْتُونِى بِهِۦ فَلَمَّا جَآءَهُ ٱلرَّسُولُ قَالَ ٱرْجِعْ إِلَىٰ رَبِّكَ فَسْـَٔلْهُ مَا بَالُ ٱلنِّسْوَةِ ٱلَّٰتِى قَطَّعْنَ أَيْدِيَهُنَّ إِنَّ رَبِّى بِكَيْدِهِنَّ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy50. ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ።» አለ። መልእክተኛዉም ወደ ዩሱፍ በመጣ ጊዜ ዩሱፍ: «ወደ ጌታህ ተመለስና የእነዚያን እጆቻቸውን የቆረጡትን ሴቶች ሁኔታ ጠይቀው ጌታዬ ተንኮላቸውን አዋቂ ነውና።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ مَا خَطْبُكُنَّ إِذْ رَٰوَدتُّنَّ يُوسُفَ عَن نَّفْسِهِۦ قُلْنَ حَٰشَ لِلَّهِ مَا عَلِمْنَا عَلَيْهِ مِن سُوٓءٍ قَالَتِ ٱمْرَأَتُ ٱلْعَزِيزِ ٱلْـَٰٔنَ حَصْحَصَ ٱلْحَقُّ أَنَا۠ رَٰوَدتُّهُۥ عَن نَّفْسِهِۦ وَإِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy51. ንጉሡም «ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው። «ለአላህ ጥራት ይገባው በእርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገር አላወቅንም (አላየንም)።» አሉት። የዐዚዝ ሚስትም አለች: «አሁን እውነቱ ተገለጸ እኔ አባበልኩት እርሱም ከእውነተኞቹ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ لِيَعْلَمَ أَنِّى لَمْ أَخُنْهُ بِٱلْغَيْبِ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى كَيْدَ ٱلْخَآئِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy52. «ይህ ጌታዬ ሩቅ ሆኖ ሳለ ያልከዳሁት መሆኔንና አላህም የከዳተኞችን ተንኮል የማያቃና መሆኑን እንዲያውቅ ነው።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أُبَرِّئُ نَفْسِىٓ إِنَّ ٱلنَّفْسَ لَأَمَّارَةٌۢ بِٱلسُّوٓءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّىٓ إِنَّ رَبِّى غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy53. «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም:: ነፍስ ሁሉ ጌታዬ ያዘነላት (የጠበቃት) ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና:: ጌታዬ በጣም መሐሪና አዛኝ ነው።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلْمَلِكُ ٱئْتُونِى بِهِۦٓ أَسْتَخْلِصْهُ لِنَفْسِى فَلَمَّا كَلَّمَهُۥ قَالَ إِنَّكَ ٱلْيَوْمَ لَدَيْنَا مَكِينٌ أَمِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy54. ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ ለራሴ የግሌ አደርገዋለሁና።» አለ። ባናገረዉም ጊዜ «አንተ ዛሬ እኛ ዘንድ ባለሟልና ታማኝ ነህ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ ٱجْعَلْنِى عَلَىٰ خَزَآئِنِ ٱلْأَرْضِ إِنِّى حَفِيظٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy55. «በምድር ግምጃ ቤቶች ላይ ሹም አድርገኝ እኔ ጠባቂ አዋቂ ነኝና።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِى ٱلْأَرْضِ يَتَبَوَّأُ مِنْهَا حَيْثُ يَشَآءُ نُصِيبُ بِرَحْمَتِنَا مَن نَّشَآءُ وَلَا نُضِيعُ أَجْرَ ٱلْمُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy56. እንደዚሁም ለዩሱፍ በምድር ላይ ከእርሷ በፈለገው ስፍራ የሚሰፍር ሲሆን አስመቸነው:: በችሮታችን የምንሻውን ሰው እንለያለን። የበጎ ሠሪዎችንም ዋጋ አናጠፋም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَأَجْرُ ٱلْـَٔاخِرَةِ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَكَانُوا۟ يَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy57. የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَآءَ إِخْوَةُ يُوسُفَ فَدَخَلُوا۟ عَلَيْهِ فَعَرَفَهُمْ وَهُمْ لَهُۥ مُنكِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy58. የዩሱፍ ወንድሞችም መጡ በእርሱም ላይ ገቡ:: እነርሱም እርሱን የሳቱት ሲሆኑ አወቃቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا جَهَّزَهُم بِجَهَازِهِمْ قَالَ ٱئْتُونِى بِأَخٍ لَّكُم مِّنْ أَبِيكُمْ أَلَا تَرَوْنَ أَنِّىٓ أُوفِى ٱلْكَيْلَ وَأَنَا۠ خَيْرُ ٱلْمُنزِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy59. ጉዳያቸውን ፈጽሞ ስንቃቸውንም ባዘጋጀላቸው ጊዜ አለ: «ከአባታችሁ በኩል የሆነውን ወንድማችሁን አምጡልኝ እኔ ከአስተናጋጆች ሁሉ በላጭ ስሆን ስፍርን የምሞላ መሆኔን አታዩምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِن لَّمْ تَأْتُونِى بِهِۦ فَلَا كَيْلَ لَكُمْ عِندِى وَلَا تَقْرَبُونِ

Amharic Translation - Africa Academy60. «እርሱንም ባታመጡልኝ። እኔ ዘንድ ለእናንተ ስፍር የላችሁም:: አትቀርቡኝምም።» አለ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ سَنُرَٰوِدُ عَنْهُ أَبَاهُ وَإِنَّا لَفَٰعِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. «ስለ እርሱ አባቱን በጥብቅ እንጠይቃለን፤ እኛም ይህንን በእርግጥ ሰሪዎች ነን።» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ لِفِتْيَٰنِهِ ٱجْعَلُوا۟ بِضَٰعَتَهُمْ فِى رِحَالِهِمْ لَعَلَّهُمْ يَعْرِفُونَهَآ إِذَا ٱنقَلَبُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَهْلِهِمْ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy62. ለአሽከሮቹም፡- «ወደ ቤተሰቦቻቸው በተመለሱ ጊዜ ሸቀጣቸውን (ገንዘባቸውን) ያውቋት ዘንድ በየጓዞቻቸው ውስጥ አድርጉላቸው ሊመለሱ ይከጀላልና።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا رَجَعُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَبِيهِمْ قَالُوا۟ يَٰٓأَبَانَا مُنِعَ مِنَّا ٱلْكَيْلُ فَأَرْسِلْ مَعَنَآ أَخَانَا نَكْتَلْ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ

Amharic Translation - Africa Academy63. ወደ አባታቸዉም በተመለሱ ጊዜ፡- «አባታችን ሆይ! (ወንድማችንን እስከምንወስድ) ስፍር ከኛ ተከልክሏል። ስለዚህ ወንድማችንን ከእኛ ጋር ላከው፤ ይሰፈርልናልና እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን።» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ هَلْ ءَامَنُكُمْ عَلَيْهِ إِلَّا كَمَآ أَمِنتُكُمْ عَلَىٰٓ أَخِيهِ مِن قَبْلُ فَٱللَّهُ خَيْرٌ حَٰفِظًا وَهُوَ أَرْحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy64. «ከአሁን በፊት በወንድሙ ላይ እንዳመንኳችሁ እንጂ በእርሱ ላይ አምናችኋለሁን? አላህም በጠባቂነት ከሁሉ የበለጠ ነው:: እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا فَتَحُوا۟ مَتَٰعَهُمْ وَجَدُوا۟ بِضَٰعَتَهُمْ رُدَّتْ إِلَيْهِمْ قَالُوا۟ يَٰٓأَبَانَا مَا نَبْغِى هَٰذِهِۦ بِضَٰعَتُنَا رُدَّتْ إِلَيْنَا وَنَمِيرُ أَهْلَنَا وَنَحْفَظُ أَخَانَا وَنَزْدَادُ كَيْلَ بَعِيرٍ ذَٰلِكَ كَيْلٌ يَسِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy65. እቃቸውንም በከፈቱ ጊዜ ሸቀጣቸውን ወደ እነርሱ ተመልሶ አገኙት። «አባታችን ሆይ! ምን እንፈልጋለን? ይህች ሸቀጣችን ናት ወደ እኛ ተመልሳልናለች እንረዳባታለን:: ለቤተሰቦቻችንም እንሸምታለን። ወንድማችንንም እንጠብቃለን:: የአንድ ግመልን ጭነትም እንጨምራለን:: ይህ በንጉሱ ላይ ቀላል ስፍር ነው።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لَنْ أُرْسِلَهُۥ مَعَكُمْ حَتَّىٰ تُؤْتُونِ مَوْثِقًا مِّنَ ٱللَّهِ لَتَأْتُنَّنِى بِهِۦٓ إِلَّآ أَن يُحَاطَ بِكُمْ فَلَمَّآ ءَاتَوْهُ مَوْثِقَهُمْ قَالَ ٱللَّهُ عَلَىٰ مَا نَقُولُ وَكِيلٌ

Amharic Translation - Africa Academy66. «ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን በእርግጥ የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃልኪዳን (መተማመኛ) እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ ጋር ፈጽሞ አልከዉም።» አላቸው። መተማመኛቸውንም በሰጡ ጊዜ «አላህ በምንለው ሁሉ ላይ ዋስ ነው።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ يَٰبَنِىَّ لَا تَدْخُلُوا۟ مِنۢ بَابٍ وَٰحِدٍ وَٱدْخُلُوا۟ مِنْ أَبْوَٰبٍ مُّتَفَرِّقَةٍ وَمَآ أُغْنِى عَنكُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن شَىْءٍ إِنِ ٱلْحُكْمُ إِلَّا لِلَّهِ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَعَلَيْهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُتَوَكِّلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy67. አለም፡- «ልጆቼ ሆይ! በአንድ በር አትግቡ:: ግን በተለያዩ በሮች ግቡ:: ከአላህም ፍርድ በምንም አልጠቅማችሁም (አልመልስላችሁም)። ፍርዱ የአላህ እንጂ የሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ተመኪዎችም ሁሉ በእርሱ ላይ ብቻ ይመኩ።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا دَخَلُوا۟ مِنْ حَيْثُ أَمَرَهُمْ أَبُوهُم مَّا كَانَ يُغْنِى عَنْهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن شَىْءٍ إِلَّا حَاجَةً فِى نَفْسِ يَعْقُوبَ قَضَىٰهَا وَإِنَّهُۥ لَذُو عِلْمٍ لِّمَا عَلَّمْنَٰهُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy68. አባታቸው ካዘዛቸው ስፍራ በገቡ ጊዜ ከአላህ ፍርድ ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከለክልላቸው አልነበረም:: ግን በየዕቁብ ነፍስ ውስጥ የነበረች ጉዳይ ናት:: ፈጸማት። እርሱም ስላሳወቅነው የእውቀት ባለቤት ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا دَخَلُوا۟ عَلَىٰ يُوسُفَ ءَاوَىٰٓ إِلَيْهِ أَخَاهُ قَالَ إِنِّىٓ أَنَا۠ أَخُوكَ فَلَا تَبْتَئِسْ بِمَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy69. በዩሱፍ ላይ በገቡ ጊዜም ወንድሙን ወደ እርሱ አስጠጋውና «እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ:: ይሰሩት በነበሩትም ሁሉ አትበሳጭ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَهَّزَهُم بِجَهَازِهِمْ جَعَلَ ٱلسِّقَايَةَ فِى رَحْلِ أَخِيهِ ثُمَّ أَذَّنَ مُؤَذِّنٌ أَيَّتُهَا ٱلْعِيرُ إِنَّكُمْ لَسَٰرِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. እቃቸውን ባዘጋጀላቸው ጊዜ ዋንጫይቱን በወንድሙ እቃ ውስጥ አደረገና ከዚያ «እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በእርግጥ ሌቦች ናችሁ።» ሲል ጠሪ ተጣራ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ وَأَقْبَلُوا۟ عَلَيْهِم مَّاذَا تَفْقِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy71. ወደ እነርሱ ዞረዉም: «ምንድን ጠፋችሁ?» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ نَفْقِدُ صُوَاعَ ٱلْمَلِكِ وَلِمَن جَآءَ بِهِۦ حِمْلُ بَعِيرٍ وَأَنَا۠ بِهِۦ زَعِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy72. «የንጉሱ መስፈሪያ ጠፍቶናል እርሱንም ላመጣ ሰው የአንድ ግመል ጭነት አለው። እኔም በእርሱ ተያዥ ነኝ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ تَٱللَّهِ لَقَدْ عَلِمْتُم مَّا جِئْنَا لِنُفْسِدَ فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا كُنَّا سَٰرِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy73. «በአላህ እንምላለን! በምድር ላይ ለማጥፋት እንዳልመጣን በእርግጥ አውቃችኋል ሌቦችም አልነበርንም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ فَمَا جَزَٰٓؤُهُۥٓ إِن كُنتُمْ كَٰذِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy74. «ውሸታሞች ብትሆኑስ ቅጣቱ ምንድን ነው?» አሏቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ جَزَٰٓؤُهُۥ مَن وُجِدَ فِى رَحْلِهِۦ فَهُوَ جَزَٰٓؤُهُۥ كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy75. «ቅጣቱ በየዕቁብ ሕግ እቃው በጓዙ ውስጥ የተገኘበት ሰው ራሱ ባሪያ ተደርጎ መውሰድ ነው። እርሱም ቅጣቱ ነው:: ልክ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبَدَأَ بِأَوْعِيَتِهِمْ قَبْلَ وِعَآءِ أَخِيهِ ثُمَّ ٱسْتَخْرَجَهَا مِن وِعَآءِ أَخِيهِ كَذَٰلِكَ كِدْنَا لِيُوسُفَ مَا كَانَ لِيَأْخُذَ أَخَاهُ فِى دِينِ ٱلْمَلِكِ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ نَرْفَعُ دَرَجَٰتٍ مَّن نَّشَآءُ وَفَوْقَ كُلِّ ذِى عِلْمٍ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy76. ምርመራውን ከወንድሙ እቃ በፊትም በእቃዎቻቸው ጀመረ:: ከዚያ ዋንጫይቱን ከወንድሙ እቃ ውስጥ አወጣት። ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ብልሃትን አስተማርነው:: አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሱ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባዉም ነበር:: የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን። ከእውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም አዋቂ አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ إِن يَسْرِقْ فَقَدْ سَرَقَ أَخٌ لَّهُۥ مِن قَبْلُ فَأَسَرَّهَا يُوسُفُ فِى نَفْسِهِۦ وَلَمْ يُبْدِهَا لَهُمْ قَالَ أَنتُمْ شَرٌّ مَّكَانًا وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا تَصِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy77. «እርሱ ቢሰርቅ ከአሁን በፊት የእርሱው ወንድም በእርግጥ ሰርቋል።» አሉ። ዩሱፍም ይህችን (አስቀያሚ ንግግር) በነፍሱ ውስጥ ደበቃት:: ለእነርሱም አልገለጣትም። በልቡ «እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው:: አላህ የምትሉትን ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ يَٰٓأَيُّهَا ٱلْعَزِيزُ إِنَّ لَهُۥٓ أَبًا شَيْخًا كَبِيرًا فَخُذْ أَحَدَنَا مَكَانَهُۥٓ إِنَّا نَرَىٰكَ مِنَ ٱلْمُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy78. «አንተ የተከበርከው ሆይ! ለእርሱ በእርግጥ ታላቅ ሽማግሌ አባት አለው:: ስለዚህ በእርሱ ስፍራ አንደኛችንን ያዝ:: እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ እናይሃለንና።» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِ أَن نَّأْخُذَ إِلَّا مَن وَجَدْنَا مَتَٰعَنَا عِندَهُۥٓ إِنَّآ إِذًا لَّظَٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy79. «ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ያገኘንበትን ሰው እንጂ ሌላን ከመያዝ በአላህ እንጠበቃለን:: እኛ ያን ባደረግን ጊዜ በእርግጥ በዳዮች ነን።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا ٱسْتَيْـَٔسُوا۟ مِنْهُ خَلَصُوا۟ نَجِيًّا قَالَ كَبِيرُهُمْ أَلَمْ تَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ أَبَاكُمْ قَدْ أَخَذَ عَلَيْكُم مَّوْثِقًا مِّنَ ٱللَّهِ وَمِن قَبْلُ مَا فَرَّطتُمْ فِى يُوسُفَ فَلَنْ أَبْرَحَ ٱلْأَرْضَ حَتَّىٰ يَأْذَنَ لِىٓ أَبِىٓ أَوْ يَحْكُمَ ٱللَّهُ لِى وَهُوَ خَيْرُ ٱلْحَٰكِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy80. ከእርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ:: ታላቃቸውም አለ: «አባታችሁ በእናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መተማመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑንና ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለእኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የምስርን (የግብጽን) ምድር አልለይም:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱرْجِعُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَبِيكُمْ فَقُولُوا۟ يَٰٓأَبَانَآ إِنَّ ٱبْنَكَ سَرَقَ وَمَا شَهِدْنَآ إِلَّا بِمَا عَلِمْنَا وَمَا كُنَّا لِلْغَيْبِ حَٰفِظِينَ

Amharic Translation - Africa Academy81. «ወደ አባታችሁ ተመለሱ:: በሉትም: ‹አባታችን ሆይ ልጅህ ሰረቀ፤ ባወቅነዉም ነገር እንጂ አልመሰከርንም:: ሩቁንም ነገር ምስጢሩን አዋቂዎች አልነበርንም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَسْـَٔلِ ٱلْقَرْيَةَ ٱلَّتِى كُنَّا فِيهَا وَٱلْعِيرَ ٱلَّتِىٓ أَقْبَلْنَا فِيهَا وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy82. «‹ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን።›»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ بَلْ سَوَّلَتْ لَكُمْ أَنفُسُكُمْ أَمْرًا فَصَبْرٌ جَمِيلٌ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَأْتِيَنِى بِهِمْ جَمِيعًا إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy83. ያዕቁብም፡- «አይደለም። ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላቸሁና ሠራችሁት እንጂ:: እናም መልካም ትዕግስት ማድረግ አለብኝ:: እነርሱን ሁሉንም የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል:: እነሆ እርሱ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبْيَضَّتْ عَيْنَاهُ مِنَ ٱلْحُزْنِ فَهُوَ كَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy84. ከነርሱም ዞር አለና፡- «በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ:: ዓይኖቹም ከሐዘን የተነሳ ነጡ:: እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ تَٱللَّهِ تَفْتَؤُا۟ تَذْكُرُ يُوسُفَ حَتَّىٰ تَكُونَ حَرَضًا أَوْ تَكُونَ مِنَ ٱلْهَٰلِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy85. እነርሱም፡- «በአላህ እንምላለን! ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ إِنَّمَآ أَشْكُوا۟ بَثِّى وَحُزْنِىٓ إِلَى ٱللَّهِ وَأَعْلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy86. «ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው። ከአላህ በኩል የማታውቁትን ነገር እኔ አውቃለሁና።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰبَنِىَّ ٱذْهَبُوا۟ فَتَحَسَّسُوا۟ مِن يُوسُفَ وَأَخِيهِ وَلَا تَا۟يْـَٔسُوا۟ مِن رَّوْحِ ٱللَّهِ إِنَّهُۥ لَا يَا۟يْـَٔسُ مِن رَّوْحِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْقَوْمُ ٱلْكَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy87. «ልጆቼ ሆይ! ሂዱ ከዩሱፍና ከወንድሙም ወሬ ተመራመሩ:: ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ:: እነሆ ከአላህ እዝነት ከሓዲያን ህዝቦች እንጂ ማንም ተስፋ አይቆርጥም።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا دَخَلُوا۟ عَلَيْهِ قَالُوا۟ يَٰٓأَيُّهَا ٱلْعَزِيزُ مَسَّنَا وَأَهْلَنَا ٱلضُّرُّ وَجِئْنَا بِبِضَٰعَةٍ مُّزْجَىٰةٍ فَأَوْفِ لَنَا ٱلْكَيْلَ وَتَصَدَّقْ عَلَيْنَآ إِنَّ ٱللَّهَ يَجْزِى ٱلْمُتَصَدِّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy88. በእርሱም ላይ በገቡ ጊዜ: «አንተ የተከበርከው ሆይ! እኛንም ቤተሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን። እርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል:: ስፍርንም ለእኛ ሙላልን:: በእኛም ላይ መጽውት:: አላህ መጽዋቾችን ይመነዳልና።» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ هَلْ عَلِمْتُم مَّا فَعَلْتُم بِيُوسُفَ وَأَخِيهِ إِذْ أَنتُمْ جَٰهِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy89. «እናንተ የማታውቁ በነበራችሁ ጊዜ በዩሱፍና በወንድሙ ላይ የሠራችሁትን ግፍ አወቃችሁን?» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ أَءِنَّكَ لَأَنتَ يُوسُفُ قَالَ أَنَا۠ يُوسُفُ وَهَٰذَآ أَخِى قَدْ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَيْنَآ إِنَّهُۥ مَن يَتَّقِ وَيَصْبِرْ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ ٱلْمُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy90. «አንተ በእርግጥ አንተ ዩሱፍ ነህን?» አሉት። «አዎ እኔ በትክክል ዩሱፍ ነኝ:: ይህም ወንድሜ ነው:: አላህ በእኛ ላይ በእርግጥ ለገሰልን:: እነሆ የሚጠነቀቅና የሚታገስ ሰው አላህ ይክሰዋል:: አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ تَٱللَّهِ لَقَدْ ءَاثَرَكَ ٱللَّهُ عَلَيْنَا وَإِن كُنَّا لَخَٰطِـِٔينَ

Amharic Translation - Africa Academy91. «በአላህ እንምላለን! አላህ በእኛ ላይ በእርግጥ አበለጠህ፤ እኛም በእርግጥ አጥፊዎች ነበርን።» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لَا تَثْرِيبَ عَلَيْكُمُ ٱلْيَوْمَ يَغْفِرُ ٱللَّهُ لَكُمْ وَهُوَ أَرْحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy92. እርሱም አላቸው: «ዛሬ በእናንተ ላይ ምንም ወቀሳ የለባችሁም። አላህ ለእናንተ ይምራል። እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነውና።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱذْهَبُوا۟ بِقَمِيصِى هَٰذَا فَأَلْقُوهُ عَلَىٰ وَجْهِ أَبِى يَأْتِ بَصِيرًا وَأْتُونِى بِأَهْلِكُمْ أَجْمَعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy93. «ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ሂዱ:: በአባቴ ፊትም ጣሉት:: የሚያይ ሆኖ ይመጣልና:: ቤተሰቦቻችሁንም በሙሉ ሰብስባችሁ አምጡልኝ።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا فَصَلَتِ ٱلْعِيرُ قَالَ أَبُوهُمْ إِنِّى لَأَجِدُ رِيحَ يُوسُفَ لَوْلَآ أَن تُفَنِّدُونِ

Amharic Translation - Africa Academy94. ግመል ጫኞችም ከግብጽ በወጡ ጊዜ አባታቸው «እኔ የዩሱፍን ሽታ በእርግጥ አገኛለሁ:: ባታቄሉኝ ኖሮ ታምኑኝ ነበር።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ تَٱللَّهِ إِنَّكَ لَفِى ضَلَٰلِكَ ٱلْقَدِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy95. «በአላህ እንምላለን! አንተ በእርግጥ እስካሁንም በዚያው በቀድሞው ስህተትህ ውስጥ ነህ።» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّآ أَن جَآءَ ٱلْبَشِيرُ أَلْقَىٰهُ عَلَىٰ وَجْهِهِۦ فَٱرْتَدَّ بَصِيرًا قَالَ أَلَمْ أَقُل لَّكُمْ إِنِّىٓ أَعْلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy96. አብሳሪዉም በመጣ ጊዜ ቀሚሱን በፊቱ ላይ ጣለው፤ ወዲያዉም የሚያይ ሆነ:: «እኔ ለእናንተ ከአላህ በኩል የማታውቁትን አውቃለሁ አላልኳችሁም ነበርን?» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ يَٰٓأَبَانَا ٱسْتَغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَآ إِنَّا كُنَّا خَٰطِـِٔينَ

Amharic Translation - Africa Academy97. «አባታችን ሆይ! ለኃጢያቶቻችን ምሕረትን ለምንልን:: እኛ ጥፋተኞች ነበርንና።» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ سَوْفَ أَسْتَغْفِرُ لَكُمْ رَبِّىٓ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy98. «ወደ ፊት ለእናንተ ጌታዬን ምሕረትን እለምንላችኋለሁ:: እነሆ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا دَخَلُوا۟ عَلَىٰ يُوسُفَ ءَاوَىٰٓ إِلَيْهِ أَبَوَيْهِ وَقَالَ ٱدْخُلُوا۟ مِصْرَ إِن شَآءَ ٱللَّهُ ءَامِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy99. በዩሱፍ ላይም በገቡ ጊዜ ወላጆቹን ወደ እርሱ አስጠጋቸው፤ «በአላህም ፈቃድ ጥብቆች ስትሆኑ ሚስርን (ግብጽ) ግቡ።» አላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرَفَعَ أَبَوَيْهِ عَلَى ٱلْعَرْشِ وَخَرُّوا۟ لَهُۥ سُجَّدًا وَقَالَ يَٰٓأَبَتِ هَٰذَا تَأْوِيلُ رُءْيَٰىَ مِن قَبْلُ قَدْ جَعَلَهَا رَبِّى حَقًّا وَقَدْ أَحْسَنَ بِىٓ إِذْ أَخْرَجَنِى مِنَ ٱلسِّجْنِ وَجَآءَ بِكُم مِّنَ ٱلْبَدْوِ مِنۢ بَعْدِ أَن نَّزَغَ ٱلشَّيْطَٰنُ بَيْنِى وَبَيْنَ إِخْوَتِىٓ إِنَّ رَبِّى لَطِيفٌ لِّمَا يَشَآءُ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy100. ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው ለርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት። «አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፡፡ ጌታዬ በእርግጥ እውነት አደረጋት፡፡ ከወህኒ ቤትም ባወጣኝና ሰይጣንም በእኔና በወንድሞቼ መካከል ካበላሸ በኋላ እናንተን ከገጠር ባመጣችሁ ጊዜ በእርግጥ ለእኔ መልካም ዋለልኝ:: ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው:: እነሆ እርሱ አዋቂውና ጥበበኛው ነው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبِّ قَدْ ءَاتَيْتَنِى مِنَ ٱلْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِى مِن تَأْوِيلِ ٱلْأَحَادِيثِ فَاطِرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ أَنتَ وَلِىِّۦ فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ تَوَفَّنِى مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِى بِٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy101. «ጌታዬ ሆይ! ከንግስና በእርግጥ ሰጠኸኝ:: ከህልሞችም ፍች አስተማርከኝ:: የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ:: ሙስሊም ሆኜ ግደለኝ:: ወደ መልካም ሰሪዎችም አስጠጋኝ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلْغَيْبِ نُوحِيهِ إِلَيْكَ وَمَا كُنتَ لَدَيْهِمْ إِذْ أَجْمَعُوٓا۟ أَمْرَهُمْ وَهُمْ يَمْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ወደ አንተ የምናወርደው ሲሆን ከሩቅ ወሬዎች ነው:: አንተም እነርሱ በዩሱፍ ላይ የሚያሴሩ ሆነው ነገራቸውን በቆረጡ ጊዜ እነርሱ ዘንድ አብረህ አልነበርክም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَكْثَرُ ٱلنَّاسِ وَلَوْ حَرَصْتَ بِمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy103. አብዛኛዎቹ ሰዎች ለማመናቸው ብትጓጓም የሚያምኑ አይደሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا تَسْـَٔلُهُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቁርኣን ላይ ምንም ዋጋን አትጠይቃቸዉም:: እርሱ ለዓለማት ግሳጼ እንጂ ሌላ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَأَيِّن مِّنْ ءَايَةٍ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ يَمُرُّونَ عَلَيْهَا وَهُمْ عَنْهَا مُعْرِضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy105. በሰማያትና በምድር ካለችው ምልክት ብዙይቱ እነርሱ ከእርሷ ዘንጊዎች ሆነው በእርሷ ላይ ያልፋሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا يُؤْمِنُ أَكْثَرُهُم بِٱللَّهِ إِلَّا وَهُم مُّشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy106. አብዛኞቻቸዉም እነርሱ አጋሪዎች ሆነው እንጂ በአላህ አያምኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَأَمِنُوٓا۟ أَن تَأْتِيَهُمْ غَٰشِيَةٌ مِّنْ عَذَابِ ٱللَّهِ أَوْ تَأْتِيَهُمُ ٱلسَّاعَةُ بَغْتَةً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy107. ከአላህ ቅጣት ሽፋኝ አደጋ የምትመጣባቸው ወይም ሰዓቲቱ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ በድንገት የምትመጣባቸው መሆኑዋን አይፈሩምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ هَٰذِهِۦ سَبِيلِىٓ أَدْعُوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا۠ وَمَنِ ٱتَّبَعَنِى وَسُبْحَٰنَ ٱللَّهِ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ይህ መንገዴ ነው:: ወደ አላህ እጠራለሁ:: እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን:: ጥራትም ለአላህ ብቻ ይገባው:: እኔም ከአጋሪዎች አይደለሁም።» በል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِىٓ إِلَيْهِم مِّنْ أَهْلِ ٱلْقُرَىٰٓ أَفَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَلَدَارُ ٱلْـَٔاخِرَةِ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy109. ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደነርሱ ራዕይ የምናወርድላቸው የሆኑን ወንዶችን እንጂ አላክንም:: በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደሆነ አይመለከቱምን? የአኺራ ደስታ ለተጠነቀቁት ሰዎች ሁሉ በእርግጥ የተሻለች ናት:: አታውቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَا ٱسْتَيْـَٔسَ ٱلرُّسُلُ وَظَنُّوٓا۟ أَنَّهُمْ قَدْ كُذِبُوا۟ جَآءَهُمْ نَصْرُنَا فَنُجِّىَ مَن نَّشَآءُ وَلَا يُرَدُّ بَأْسُنَا عَنِ ٱلْقَوْمِ ٱلْمُجْرِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy110. መልዕክተኞች ተስፋ በቆረጡና እነርሱ በእርግጥ የተዋሹ መሆናቸውን በተጠራጠሩ ጊዜ እርዳታችን መጣላቸው:: ከዚያ እኛ የምንፈልገው ሰው እንዲድን ተደረገ:: ቅጣታችንም ከአመፀኞቹ ህዝቦች ላይ አይመለስም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ كَانَ فِى قَصَصِهِمْ عِبْرَةٌ لِّأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ مَا كَانَ حَدِيثًا يُفْتَرَىٰ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ كُلِّ شَىْءٍ وَهُدًى وَرَحْمَةً لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy111. በታሪካቸው ውስጥ ለአዕምሮ ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ መገሰጫ ነበረ:: ይህ ቁርኣን የሚቀጣጥፍ ወሬ አይደለም:: ይልቁንም ያንን በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ፤ ሁሉን ጉዳዮች ገላጭና ለሚያምኑ ህዝቦችም ሁሉ መሪ፤ ችሮታ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70