ٱللَّهُ يَبْسُطُ ٱلرِّزْقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقْدِرُ وَفَرِحُوا۟ بِٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ إِلَّا مَتَٰعٌ
Amharic Translation - Africa Academy26. አላህ ለሚሻው ሁሉ ሲሳይን ያሰፋል:: ለሚሻውም ያጠባል:: ከሓዲያን በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ:: የቅርቢቱም ሕይወት ከመጨረሻይቱ አንጻር ትንሽ መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ (ከሓዲዎች) በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱ አንጻር (ትንሽ) መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም፡፡