caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yunus፣ አንቀጽ 22

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 51 · 10:22

هُوَ ٱلَّذِى يُسَيِّرُكُمْ فِى ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ حَتَّىٰٓ إِذَا كُنتُمْ فِى ٱلْفُلْكِ وَجَرَيْنَ بِهِم بِرِيحٍ طَيِّبَةٍ وَفَرِحُوا۟ بِهَا جَآءَتْهَا رِيحٌ عَاصِفٌ وَجَآءَهُمُ ٱلْمَوْجُ مِن كُلِّ مَكَانٍ وَظَنُّوٓا۟ أَنَّهُمْ أُحِيطَ بِهِمْ دَعَوُا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ لَئِنْ أَنجَيْتَنَا مِنْ هَٰذِهِۦ لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy22. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው:: በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በእርሷ የተደሰቱ ሆነው መርከቦቹ በተንሻለሉ ጊዜ ሀይለኛ ነፋስ ትመጣባቸዋለች:: ከየስፍራዉም ማዕበል ይመጣባቸዋል:: እነርሱም ለጥፋት የተከበቡ መሆናቸውን ሲያረጋግጡ ያን ጊዜ አላህን «ከዚህች ጭንቀት ብታድነን ከአመስጋኞቹ እንሆናለን።» ሲሉ እምነታቸውን ለእርሱ ብቻ ፍጹም አድርገው ይለምኑታል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱ (አላህ) ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው፡፡ በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በርሷ የተደሰቱ ኾነው (መርከቦቹ) በተንሻለሉ ጊዜ ኀይለኛ ነፋስ ትመጣባታለች፡፡ ከየስፍራውም ማዕበል ይመጣባቸዋል፡፡ እነሱም (ለጥፋት) የተከበቡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ (ያን ጊዜ) አላህን ከዚህች (ጭንቀት) ብታድነን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን ሲሉ ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይለምኑታል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70