caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yunus፣ አንቀጽ 3

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 51 · 10:3

إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ إِذْنِهِۦ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ የፈጠራቸው አላህ ነው:: ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲሆን (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ ከእርሱ በጎ ፈቃድ በኋላ ቢሆን እንጂ አንድም አማላጅ የለም:: እነሆ ይህ አላህ ጌታችሁ ነው:: እናም በትክክል ተገዙት:: አትገሰጹምን?
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲኾን በዐርሹ ላይ (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) ተደላደለ፡፡ ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አላህ ጌታችሁ ነውና ተገዙት፤ አትገሰጹምን
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70