ሱረቱ Hud هود
123 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 52
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓر كِتَٰبٌ أُحْكِمَتْ ءَايَٰتُهُۥ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy1.አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤. ይህ ቁርኣን አናቅጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ፤ ጥበበኛና ውስጠ አዋቂ ከሆነው (አምላክ) ዘንድ የተወረደ መጽሐፍ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَّا تَعْبُدُوٓا۟ إِلَّا ٱللَّهَ إِنَّنِى لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy2. መልዕክተኛው (እንዲህ በሚልበት ሰዎች ሆይ! ): «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ ዘንድ የተላኩ አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنِ ٱسْتَغْفِرُوا۟ رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوٓا۟ إِلَيْهِ يُمَتِّعْكُم مَّتَٰعًا حَسَنًا إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى وَيُؤْتِ كُلَّ ذِى فَضْلٍ فَضْلَهُۥ وَإِن تَوَلَّوْا۟ فَإِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ كَبِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy3. (እንዲህም በሚልበት ሰዎች ሆይ! ): «ጌታችሁን ምህረት ለምኑት:: ከዚያ ወደ እርሱ ተመለሱ:: እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋል:: ለትሩፋት ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳዉን) ይሰጠዋል:: ብትሸሹም እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَى ٱللَّهِ مَرْجِعُكُمْ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy4. «መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَآ إِنَّهُمْ يَثْنُونَ صُدُورَهُمْ لِيَسْتَخْفُوا۟ مِنْهُ أَلَا حِينَ يَسْتَغْشُونَ ثِيَابَهُمْ يَعْلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعْلِنُونَ إِنَّهُۥ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
Amharic Translation - Africa Academy5. ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ! እነርሱ ከእርሱ ከአላህ ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ:: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ! ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትንም ሆነ የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል:: እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا مِن دَآبَّةٍ فِى ٱلْأَرْضِ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ رِزْقُهَا وَيَعْلَمُ مُسْتَقَرَّهَا وَمُسْتَوْدَعَهَا كُلٌّ فِى كِتَٰبٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy6. በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለና ማረፊያዋንም ሆነ መርጊያዋን የሚያውቅ ቢሆን እንጂ:: ሁሉም ነገር ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ وَكَانَ عَرْشُهُۥ عَلَى ٱلْمَآءِ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا وَلَئِن قُلْتَ إِنَّكُم مَّبْعُوثُونَ مِنۢ بَعْدِ ٱلْمَوْتِ لَيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy7. አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ነው:: ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር:: የትኛችሁ ስራችሁ ያማረ መሆኑ ይፈትናችሁ ዘንድ ፈጠራችሁ:: «እናንተ ከሞት በኋላ በእርግጥ ተቀስቃሾች ናችሁ» ብትልም። እነዚያ የካዱት «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَئِنْ أَخَّرْنَا عَنْهُمُ ٱلْعَذَابَ إِلَىٰٓ أُمَّةٍ مَّعْدُودَةٍ لَّيَقُولُنَّ مَا يَحْبِسُهُۥٓ أَلَا يَوْمَ يَأْتِيهِمْ لَيْسَ مَصْرُوفًا عَنْهُمْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ
Amharic Translation - Africa Academy8. ቅጣቱንም ለተቆጠሩ ጥቂት ጊዜያቶች ብናቆይላቸው «ከመውረድ የሚከለክለው ምንድን ነው?» ይላሉ:: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ:: በሚመጣባቸው ቀን ከእነርሱ ላይ ተመላሽ አይደለም:: በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩትም ቅጣት በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَئِنْ أَذَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ مِنَّا رَحْمَةً ثُمَّ نَزَعْنَٰهَا مِنْهُ إِنَّهُۥ لَيَـُٔوسٌ كَفُورٌ
Amharic Translation - Africa Academy9. ሰውንም ከችሮታችን ብናቀምሰውና ከዚያ ብንወስድበት እርሱ ተስፋ ቆራጭና ክህደተ ብርቱ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَئِنْ أَذَقْنَٰهُ نَعْمَآءَ بَعْدَ ضَرَّآءَ مَسَّتْهُ لَيَقُولَنَّ ذَهَبَ ٱلسَّيِّـَٔاتُ عَنِّىٓ إِنَّهُۥ لَفَرِحٌ فَخُورٌ
Amharic Translation - Africa Academy10. ካገኘችዉም ችግር በኋላ ጸጋዎቻችንን ብናቀምሰው «ችግሮች ከእኔ ላይ ተወገዱ።» ይላል:: አያመሰግንም:: እርሱ ተደሳችና ጉረኛ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا ٱلَّذِينَ صَبَرُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ كَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያ የታገሱና መልካም ሥራዎችንም የሰሩ ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَعَلَّكَ تَارِكٌۢ بَعْضَ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيْكَ وَضَآئِقٌۢ بِهِۦ صَدْرُكَ أَن يَقُولُوا۟ لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْهِ كَنزٌ أَوْ جَآءَ مَعَهُۥ مَلَكٌ إِنَّمَآ أَنتَ نَذِيرٌ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ وَكِيلٌ
Amharic Translation - Africa Academy12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይ (የሀብት) ድልብ ለምን አልተወረደም? ወይም ከእርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም?» ማለታቸውን በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊሆን ይፈራልሃል:: አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ (ወኪል) ተጠባባቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ يَقُولُونَ ٱفْتَرَىٰهُ قُلْ فَأْتُوا۟ بِعَشْرِ سُوَرٍ مِّثْلِهِۦ مُفْتَرَيَٰتٍ وَٱدْعُوا۟ مَنِ ٱسْتَطَعْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «ቁርኣንን ቀጣጠፈው» ይላሉን? «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን አስር የተቀጣጠፉ ምዕራፎች እስቲ አምጡ:: ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ረዳት ጥሩ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِلَّمْ يَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ فَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّمَآ أُنزِلَ بِعِلْمِ ٱللَّهِ وَأَن لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. ለእናንተ ምላሽ ካልሰጧችሁ «(ጣዖት አምላኪያን ሆይ!) የተወረደው በአላህ እውቀት ብቻ መሆኑንና ከእርሱ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም እወቁ:: እናም አትሰልሙምን?» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَٰلَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ
Amharic Translation - Africa Academy15. ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሁሉ ሥራዎቻቸውን ምንዳዋን በእርሷ ውስጥ ወደ እነርሱ እንሞላላቸዋለን:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ إِلَّا ٱلنَّارُ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا۟ فِيهَا وَبَٰطِلٌ مَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy16. እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከእሳት በስተቀር የሌላቸው ናቸው:: የሰሩትም ሥራ በእርሷ ውስጥ ተበላሸ:: በቅርቢቱ ዓለም ይሰሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّهِۦ وَيَتْلُوهُ شَاهِدٌ مِّنْهُ وَمِن قَبْلِهِۦ كِتَٰبُ مُوسَىٰٓ إِمَامًا وَرَحْمَةً أُو۟لَٰٓئِكَ يُؤْمِنُونَ بِهِۦ وَمَن يَكْفُرْ بِهِۦ مِنَ ٱلْأَحْزَابِ فَٱلنَّارُ مَوْعِدُهُۥ فَلَا تَكُ فِى مِرْيَةٍ مِّنْهُ إِنَّهُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكَ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy17. ከጌታው ዘንድ አስረጅ የደረሰውንና ከእርሱም የሆነ መስካሪ የሚከተለው ከቁርኣን በፊትም ለሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲሆን የመሰከረለት (ሰውና) የቅርቢቱን ህይወት እንደሚሻው (ሰው) ነውን? እነዚያ በእርሱ (ቁርኣን) ያምናሉ:: ከአህዛቦቹ በእርሱ የሚክድ ሰው ሁሉ መመለሻው እሳት ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: እሱ ከጌታህ ዘንድ የሆነ እውነት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أُو۟لَٰٓئِكَ يُعْرَضُونَ عَلَىٰ رَبِّهِمْ وَيَقُولُ ٱلْأَشْهَٰدُ هَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ كَذَبُوا۟ عَلَىٰ رَبِّهِمْ أَلَا لَعْنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy18. በአላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ በጌታቸው ላይ ይቀረባሉ:: መስካሪዎቹም «እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹት ናቸው።» ይላሉ:: «አስተዉሉ! የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ብቻ ይሁን።» ይባላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا وَهُم بِٱلْـَٔاخِرَةِ هُمْ كَٰفِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy19. እነርሱም እነዚያ ከአላህ መንገድ ሰዎችን የሚከለክሉ የአላህን መንገድ መጥመሟንም የሚሹት ናቸው:: እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከሓዲያን ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ لَمْ يَكُونُوا۟ مُعْجِزِينَ فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا كَانَ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِنْ أَوْلِيَآءَ يُضَٰعَفُ لَهُمُ ٱلْعَذَابُ مَا كَانُوا۟ يَسْتَطِيعُونَ ٱلسَّمْعَ وَمَا كَانُوا۟ يُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy20. እነዚያም በምድር ውስጥ ከአላህ የሚያመልጡ አልነበሩም:: ከአላህ ሌላ ለእነርሱ ረዳቶች አልነበሯቸዉም:: ለእነርሱ ቅጣቱ ይደራረብላቸዋል:: እውነትን መስማትን የሚችሉ አልነበሩም:: የሚያዩም አልነበሩም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy21. እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር የጠፋባቸው ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا جَرَمَ أَنَّهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ هُمُ ٱلْأَخْسَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy22. እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም በጣም ከሳሪዎቹ ለመሆናቸው ጥርጥር የለዉም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَأَخْبَتُوٓا۟ إِلَىٰ رَبِّهِمْ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy23. እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸዉም የተዋረዱት እነዚያ የገነት ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَثَلُ ٱلْفَرِيقَيْنِ كَٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْأَصَمِّ وَٱلْبَصِيرِ وَٱلسَّمِيعِ هَلْ يَسْتَوِيَانِ مَثَلًا أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy24. የሁለቱ ክፍሎች ምሳሌ አይኑ የማያይ አይነ ስውር፤ ጆሮው የማይሰማ ደንቆሮ ሰውና አይኑ የሚያይ ጆሮው የሚሰማ ሰው ብጤ ነው:: ሁለቱ በምሳሌነት ይስተካከላሉን? አትገሰጹንም?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِۦٓ إِنِّى لَكُمْ نَذِيرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy25. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ ላክንና አላቸዉም: «እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَن لَّا تَعْبُدُوٓا۟ إِلَّا ٱللَّهَ إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ أَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy26. «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ። እኔ ለእናንተ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقَالَ ٱلْمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن قَوْمِهِۦ مَا نَرَىٰكَ إِلَّا بَشَرًا مِّثْلَنَا وَمَا نَرَىٰكَ ٱتَّبَعَكَ إِلَّا ٱلَّذِينَ هُمْ أَرَاذِلُنَا بَادِىَ ٱلرَّأْىِ وَمَا نَرَىٰ لَكُمْ عَلَيْنَا مِن فَضْلٍۭ بَلْ نَظُنُّكُمْ كَٰذِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy27. ከህዝቦቹም መካከል እነዚያ የካዱት መሪዎች «ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም:: እነዚያም እነርሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም:: ለእናንተም በእኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም:: ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰقَوْمِ أَرَءَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّى وَءَاتَىٰنِى رَحْمَةً مِّنْ عِندِهِۦ فَعُمِّيَتْ عَلَيْكُمْ أَنُلْزِمُكُمُوهَا وَأَنتُمْ لَهَا كَٰرِهُونَ
Amharic Translation - Africa Academy28. እርሱም አላቸው: «ህዝቦቼ ሆይ! እስቲ ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ሆኜ ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝና በእናንተ ላይ ግን ይህች እውነታ ብትደበቅባችሁ እናንተ ለእርሷ ጠይዎች ስትሆኑ እርሷን በመቀበል እናስገድዳችኋለንን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَٰقَوْمِ لَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مَالًا إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّهُم مُّلَٰقُوا۟ رَبِّهِمْ وَلَٰكِنِّىٓ أَرَىٰكُمْ قَوْمًا تَجْهَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy29. «ህዝቦቼ ሆይ! በእርሱ የተላክሁበትን በማድረስ ላይ ገንዘብን አልጠይቃችሁም:: ምንዳዬ ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም:: እኔም እነዚያን በአላህ ያመኑትን ከአጠገቤ አባራሪ አይደለሁም:: እነርሱ ከጌታቸው ጋር የሚገናኙ ናቸውና:: ግን እኔም የምትሳሳቱ ህዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَٰقَوْمِ مَن يَنصُرُنِى مِنَ ٱللَّهِ إِن طَرَدتُّهُمْ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy30. «ህዝቦቼ ሆይ! ባባርራቸው ከአላህ ቅጣት የሚያድነኝ ማን ነው? አትገሰጹምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ إِنِّى مَلَكٌ وَلَآ أَقُولُ لِلَّذِينَ تَزْدَرِىٓ أَعْيُنُكُمْ لَن يُؤْتِيَهُمُ ٱللَّهُ خَيْرًا ٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا فِىٓ أَنفُسِهِمْ إِنِّىٓ إِذًا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. «ለናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አሉ:: ሩቅንም አውቃለሁ አልላችሁም:: እኔም መልአክ ነኝ አልላችሁም:: ለእነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው አላህ ደግ ነገርን እምነትን አይሰጣቸዉም አልልም:: አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር አዋቂ ነው:: እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰنُوحُ قَدْ جَٰدَلْتَنَا فَأَكْثَرْتَ جِدَٰلَنَا فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy32. «ኑህ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን:: እኛን መከራከርህንም አበዛህ:: ከእውነተኞቹም ከሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው እስቲ።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِنَّمَا يَأْتِيكُم بِهِ ٱللَّهُ إِن شَآءَ وَمَآ أَنتُم بِمُعْجِزِينَ
Amharic Translation - Africa Academy33. አላቸውም: «እርሱን የሚያመጣባችሁ አላህ የፈለገ ከሆነ ብቻ ነው። እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا يَنفَعُكُمْ نُصْحِىٓ إِنْ أَرَدتُّ أَنْ أَنصَحَ لَكُمْ إِن كَانَ ٱللَّهُ يُرِيدُ أَن يُغْوِيَكُمْ هُوَ رَبُّكُمْ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy34. «እናንተም አላህ ሊያጠማችሁ ፈልጎ ከሆነ ልመክራችሁ ብፈልግም ምክሬ አይጠቅማችሁም:: እርሱ ጌታችሁ ነው:: ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ يَقُولُونَ ٱفْتَرَىٰهُ قُلْ إِنِ ٱفْتَرَيْتُهُۥ فَعَلَىَّ إِجْرَامِى وَأَنَا۠ بَرِىٓءٌ مِّمَّا تُجْرِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? (ሙሐመድ ሆይ) «ብቀጥፈው ኃጢአቴ ቅጣቱ በእኔ ላይ ነው:: እኔም ከምታጠፉት ጥፋት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأُوحِىَ إِلَىٰ نُوحٍ أَنَّهُۥ لَن يُؤْمِنَ مِن قَوْمِكَ إِلَّا مَن قَدْ ءَامَنَ فَلَا تَبْتَئِسْ بِمَا كَانُوا۟ يَفْعَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy36. ወደ ኑህም (እንዲህ በሚል) ተወረደ: «እነሆ ከህዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር ወደፊት ሌሎች አያምኑም:: ይሠሩትም በነበሩት ክህደት አትዘን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱصْنَعِ ٱلْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا وَلَا تُخَٰطِبْنِى فِى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓا۟ إِنَّهُم مُّغْرَقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy37. «በጥበቃችንና በትዕዛዛችን ሆነህ መርከቢቱን ሥራ። በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ። እነርሱ በእርግጥ የሚሰምጡ ናቸውና።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَصْنَعُ ٱلْفُلْكَ وَكُلَّمَا مَرَّ عَلَيْهِ مَلَأٌ مِّن قَوْمِهِۦ سَخِرُوا۟ مِنْهُ قَالَ إِن تَسْخَرُوا۟ مِنَّا فَإِنَّا نَسْخَرُ مِنكُمْ كَمَا تَسْخَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy38. ከወገኖቹም መሪዎቹ በእርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር በእርሱ ላይ እየተሳለቁበት መርከቢቱን ይሠራል። አላቸውም: «በእኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን በእናንተ እንሳለቅባችኋለን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ مَن يَأْتِيهِ عَذَابٌ يُخْزِيهِ وَيَحِلُّ عَلَيْهِ عَذَابٌ مُّقِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy39. «የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በእርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን ማንነት ወደ ፊት ታውቃላችሁ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَمْرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ قُلْنَا ٱحْمِلْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ ٱثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ ٱلْقَوْلُ وَمَنْ ءَامَنَ وَمَآ ءَامَنَ مَعَهُۥٓ إِلَّا قَلِيلٌ
Amharic Translation - Africa Academy40. ትዕዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በመርከቧ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን።» አልነው:: ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱرْكَبُوا۟ فِيهَا بِسْمِ ٱللَّهِ مَجْر۪ىٰهَا وَمُرْسَىٰهَآ إِنَّ رَبِّى لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy41. «‹መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው።› እያላችሁ በእርሷ ተሳፈሩ:: ጌታዬ መሓሪና አዛኝ ነውና።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهِىَ تَجْرِى بِهِمْ فِى مَوْجٍ كَٱلْجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ٱبْنَهُۥ وَكَانَ فِى مَعْزِلٍ يَٰبُنَىَّ ٱرْكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy42. እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ እነርሱን ይዛቸው የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት።) ኑህም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከእኛ ጋር ተሳፈር። ከከሓዲያንም አትሁን።» ሲል ጠራው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ سَـَٔاوِىٓ إِلَىٰ جَبَلٍ يَعْصِمُنِى مِنَ ٱلْمَآءِ قَالَ لَا عَاصِمَ ٱلْيَوْمَ مِنْ أَمْرِ ٱللَّهِ إِلَّا مَن رَّحِمَ وَحَالَ بَيْنَهُمَا ٱلْمَوْجُ فَكَانَ مِنَ ٱلْمُغْرَقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy43. ልጁም «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ።» አለ:: አባቱም «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም:: እርሱ ብቻ ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር።» አለው:: ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ:: ልጁም ከሰማጮች ሆነ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقِيلَ يَٰٓأَرْضُ ٱبْلَعِى مَآءَكِ وَيَٰسَمَآءُ أَقْلِعِى وَغِيضَ ٱلْمَآءُ وَقُضِىَ ٱلْأَمْرُ وَٱسْتَوَتْ عَلَى ٱلْجُودِىِّ وَقِيلَ بُعْدًا لِّلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy44. ተባለም «ምድር ሆይ! ዉሃሽን ዋጪ:: ሰማይ ሆይ! ዝናብሽን ያዢ።» ውሃዉም ሠረገ:: ቅጣቱም ተፈጸመ:: ጁዲይ በሚባለም ተራራ ላይ መርከቢቱ ተደላደለች:: «ለከሓዲያን ጥፋት ተገባቸው (ጥፉ)።» ተባለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَادَىٰ نُوحٌ رَّبَّهُۥ فَقَالَ رَبِّ إِنَّ ٱبْنِى مِنْ أَهْلِى وَإِنَّ وَعْدَكَ ٱلْحَقُّ وَأَنتَ أَحْكَمُ ٱلْحَٰكِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy45. ኑህም ጌታውን- «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ አንዱ ነው:: ቃል ኪዳንህም እውነት ነው:: አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነህ።» በማለት ጠየቀ (ተጣራ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰنُوحُ إِنَّهُۥ لَيْسَ مِنْ أَهْلِكَ إِنَّهُۥ عَمَلٌ غَيْرُ صَٰلِحٍ فَلَا تَسْـَٔلْنِ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌ إِنِّىٓ أَعِظُكَ أَن تَكُونَ مِنَ ٱلْجَٰهِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy46. አላህም «ኑህ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም:: እርሱ መልካም ያልሆነ ስራ ነው:: በእርሱ እውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ:: እኔ ከአላዋቂዎች እንዳትሆን እገስጽሃለሁ።» አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ إِنِّىٓ أَعُوذُ بِكَ أَنْ أَسْـَٔلَكَ مَا لَيْسَ لِى بِهِۦ عِلْمٌ وَإِلَّا تَغْفِرْ لِى وَتَرْحَمْنِىٓ أَكُن مِّنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy47. «ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ እውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ:: ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قِيلَ يَٰنُوحُ ٱهْبِطْ بِسَلَٰمٍ مِّنَّا وَبَرَكَٰتٍ عَلَيْكَ وَعَلَىٰٓ أُمَمٍ مِّمَّن مَّعَكَ وَأُمَمٌ سَنُمَتِّعُهُمْ ثُمَّ يَمَسُّهُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy48. «ኑህ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ህዝቦች ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ወደ ምድር ውረድ:: ከነሱው ዘሮች የሆኑ ህዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን:: ከዚያም ከእኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይደርስባቸዋል።» ተባለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلْغَيْبِ نُوحِيهَآ إِلَيْكَ مَا كُنتَ تَعْلَمُهَآ أَنتَ وَلَا قَوْمُكَ مِن قَبْلِ هَٰذَا فَٱصْبِرْ إِنَّ ٱلْعَٰقِبَةَ لِلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ዘገባ ከሩቁ ወሬዎች መካከል ወደ አንተ ያወረድነው ነው:: አንተም ሆንክ ህዝቦችህ ከዚህ በፊት የምታውቁት አልነበራችሁም:: ታገሥ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ብቻ ናትና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا قَالَ يَٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُۥٓ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا مُفْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy50. ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን:: አላቸው፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: እናንተ ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰقَوْمِ لَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَى ٱلَّذِى فَطَرَنِىٓ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy51. «ህዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይም ምንዳን አልጠይቃችሁም:: ምንዳዬ በዚያ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም:: አታውቁምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَٰقَوْمِ ٱسْتَغْفِرُوا۟ رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوٓا۟ إِلَيْهِ يُرْسِلِ ٱلسَّمَآءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا وَيَزِدْكُمْ قُوَّةً إِلَىٰ قُوَّتِكُمْ وَلَا تَتَوَلَّوْا۟ مُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy52. «ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: ከዚያ ወደ እርሱ ተጸጸቱ:: ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና:: ወደ ኃይላችሁም ሀይልን ይጨምርላችኋል:: አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ::»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰهُودُ مَا جِئْتَنَا بِبَيِّنَةٍ وَمَا نَحْنُ بِتَارِكِىٓ ءَالِهَتِنَا عَن قَوْلِكَ وَمَا نَحْنُ لَكَ بِمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy53. እነርሱም አሉ፡- «ሁድ ሆይ! በአስረጂ አልመጣህልንም:: እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም:: እኛም ላንተ ትክክለኛ አማኞች አይደለንም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِن نَّقُولُ إِلَّا ٱعْتَرَىٰكَ بَعْضُ ءَالِهَتِنَا بِسُوٓءٍ قَالَ إِنِّىٓ أُشْهِدُ ٱللَّهَ وَٱشْهَدُوٓا۟ أَنِّى بَرِىٓءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy54. «ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር በዕብደት ለክፈውሃል እንጂ ሌላን አንልም።» አሉ:: እርሱም አላቸው: «እኔ አላህን አስመሰክራለሁ:: ከምታጋሩትም እኔ ንጹህ መሆኔን መስክሩ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مِن دُونِهِۦ فَكِيدُونِى جَمِيعًا ثُمَّ لَا تُنظِرُونِ
Amharic Translation - Africa Academy55. «ከእርሱ ሌላ አማልክትን ከምታጋሩት ንጹህ ነኝ። ሁላችሁም ሆናችሁ ተንኮልን ሥሩብኝ ከዚያ አታቆዩኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنِّى تَوَكَّلْتُ عَلَى ٱللَّهِ رَبِّى وَرَبِّكُم مَّا مِن دَآبَّةٍ إِلَّا هُوَ ءَاخِذٌۢ بِنَاصِيَتِهَآ إِنَّ رَبِّى عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy56. «እኔ ጌታዬና ጌታችሁ በሆነው በአላህ ላይ ብቻ ተመካሁ:: በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም እርሱ አናትዋን የያዛት ብትሆን እንጂ:: ጌታዬ (ቃሉም ሥራዉም) በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقَدْ أَبْلَغْتُكُم مَّآ أُرْسِلْتُ بِهِۦٓ إِلَيْكُمْ وَيَسْتَخْلِفُ رَبِّى قَوْمًا غَيْرَكُمْ وَلَا تَضُرُّونَهُۥ شَيْـًٔا إِنَّ رَبِّى عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ حَفِيظٌ
Amharic Translation - Africa Academy57. «ብትዞሩም ወደ እናንተ የተላኩበትን ነገር በእርግጥ አድርሼላችኋለሁ:: ጌታዬም ሌላን ህዝብ ይተካል:: ምንም አትጎዱትም:: ጌታዬ በሁሉ ነገር ላይ ተጠባባቂ ነውና።» አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا جَآءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا هُودًا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَنَجَّيْنَٰهُم مِّنْ عَذَابٍ غَلِيظٍ
Amharic Translation - Africa Academy58. ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሁድንና እነዚያን ከእሱጋ ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን:: ከብርቱ ቅጣትም አዳናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتِلْكَ عَادٌ جَحَدُوا۟ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمْ وَعَصَوْا۟ رُسُلَهُۥ وَٱتَّبَعُوٓا۟ أَمْرَ كُلِّ جَبَّارٍ عَنِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy59. ይህ ነገድ ዓድ ነው:: በጌታቸው ታዐምራት ካዱ:: መልዕክተኞቹንም አመጹ:: የኃያል ሞገደኛን ሁሉ ትዕዛዝም ተከተሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأُتْبِعُوا۟ فِى هَٰذِهِ ٱلدُّنْيَا لَعْنَةً وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ أَلَآ إِنَّ عَادًا كَفَرُوا۟ رَبَّهُمْ أَلَا بُعْدًا لِّعَادٍ قَوْمِ هُودٍ
Amharic Translation - Africa Academy60. በዚች በቅርቢቱ ዓለምም እርግማን እንዲከተላቸው ተደረጉ:: በትንሳኤም ቀን እንደዚሁ:: አስተውሉ! ዓዶች ጌታቸውን ካዱ። አስተውሉ! የሁድ ህዝቦች ለሆኑት ዓዶች ከእዝነት መራቅ ይገባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَٰلِحًا قَالَ يَٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُۥ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلْأَرْضِ وَٱسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَٱسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوٓا۟ إِلَيْهِ إِنَّ رَبِّى قَرِيبٌ مُّجِيبٌ
Amharic Translation - Africa Academy61. ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን። «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም:: እርሱ በምድር ፈጠራችሁ:: በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ:: ምህረቱንም ለምኑት:: ከዚያም ወደ እርሱ ተመለሱ:: ጌታዬ ለሁሉም ቅርብና ለለመነው ተቀባይ ነውና።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰصَٰلِحُ قَدْ كُنتَ فِينَا مَرْجُوًّا قَبْلَ هَٰذَآ أَتَنْهَىٰنَآ أَن نَّعْبُدَ مَا يَعْبُدُ ءَابَآؤُنَا وَإِنَّنَا لَفِى شَكٍّ مِّمَّا تَدْعُونَآ إِلَيْهِ مُرِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy62. እነርሱም «ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ መሪ ልትሆን በእርግጥ የምትከጀል የነበርክ ስትሆን:: አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን? እኛም ወደሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰقَوْمِ أَرَءَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّى وَءَاتَىٰنِى مِنْهُ رَحْمَةً فَمَن يَنصُرُنِى مِنَ ٱللَّهِ إِنْ عَصَيْتُهُۥ فَمَا تَزِيدُونَنِى غَيْرَ تَخْسِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy63. ሷሊህም አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! እስቲ ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ ቅጣት የሚያድነኝ ማነው? ከማጥፋትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَٰقَوْمِ هَٰذِهِۦ نَاقَةُ ٱللَّهِ لَكُمْ ءَايَةً فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِىٓ أَرْضِ ٱللَّهِ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ قَرِيبٌ
Amharic Translation - Africa Academy64. «ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ለእናንተ ታዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት:: ተዋትም በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ:: በክፉም አትንኳት። ቅርብ የሆነ ቅጣት ያገኛችኋልና።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَعَقَرُوهَا فَقَالَ تَمَتَّعُوا۟ فِى دَارِكُمْ ثَلَٰثَةَ أَيَّامٍ ذَٰلِكَ وَعْدٌ غَيْرُ مَكْذُوبٍ
Amharic Translation - Africa Academy65. ወግተው ገደሏትም ሷሊህም «በሀገራችሁም ሶስትን ቀናት ብቻ ተጠቀሙ ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው።» አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا جَآءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا صَٰلِحًا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَمِنْ خِزْىِ يَوْمِئِذٍ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ ٱلْقَوِىُّ ٱلْعَزِيزُ
Amharic Translation - Africa Academy66. እናም ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከእሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳንን:: ከዚያም ቀን ውርደት አዳንናቸው:: ጌታህ ብርቱውና ሁሉን አሸናፊው ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَخَذَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ ٱلصَّيْحَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دِيَٰرِهِمْ جَٰثِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy67. እነዚያን የበደሉትንም ከባድ ጩኸት ያዛቸው:: በየቤቶቻቸዉም ውስጥ የተንበረከኩ ሙት በድን ሆነው አደሩ(አነጉ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَأَن لَّمْ يَغْنَوْا۟ فِيهَآ أَلَآ إِنَّ ثَمُودَا۟ كَفَرُوا۟ رَبَّهُمْ أَلَا بُعْدًا لِّثَمُودَ
Amharic Translation - Africa Academy68. በእርሷ ውስጥ እንዳልኖሩ ሆኑ:: አስተውሉ! ሠሙዶች ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ:: አስተውሉ! ለሠሙዶች ከአላህ እዝነት መራቅ ተገባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ جَآءَتْ رُسُلُنَآ إِبْرَٰهِيمَ بِٱلْبُشْرَىٰ قَالُوا۟ سَلَٰمًا قَالَ سَلَٰمٌ فَمَا لَبِثَ أَن جَآءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ
Amharic Translation - Africa Academy69. መልዕክተኞቻችንም ወደ ኢብራሂም በልጅ መውለድ ብስራት መጡለትና ሰላም አሉት:: እሱም ሰላም አላቸው:: ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا رَءَآ أَيْدِيَهُمْ لَا تَصِلُ إِلَيْهِ نَكِرَهُمْ وَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً قَالُوا۟ لَا تَخَفْ إِنَّآ أُرْسِلْنَآ إِلَىٰ قَوْمِ لُوطٍ
Amharic Translation - Africa Academy70. እጆቻቸዉም ወደ ምግቡ የማይደርሱ መሆናቸውን ባየ ጊዜ ተግባራቸው እንግዳ ሆነበት:: ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው:: «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ህዝቦች ተልከናልና።» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱمْرَأَتُهُۥ قَآئِمَةٌ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَٰهَا بِإِسْحَٰقَ وَمِن وَرَآءِ إِسْحَٰقَ يَعْقُوبَ
Amharic Translation - Africa Academy71. ሚስቱም ቁማ ነበርና ሳቀች:: እናም በኢስሓቅ አበሰርናት:: ከኢስሐቅም በኋላ በልጁ በየዕቁብ አበሰርናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَتْ يَٰوَيْلَتَىٰٓ ءَأَلِدُ وَأَنَا۠ عَجُوزٌ وَهَٰذَا بَعْلِى شَيْخًا إِنَّ هَٰذَا لَشَىْءٌ عَجِيبٌ
Amharic Translation - Africa Academy72. እርሷም «ዋልኝ እኔ አሮጊት ይህም ባለቤቴ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን? ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው።» አለች።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ ٱللَّهِ رَحْمَتُ ٱللَّهِ وَبَرَكَٰتُهُۥ عَلَيْكُمْ أَهْلَ ٱلْبَيْتِ إِنَّهُۥ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy73. «በአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን? :: የአላህ እዝነትና በረከት በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን:: እሱ ምስጉንና ለጋሽ ነውና።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا ذَهَبَ عَنْ إِبْرَٰهِيمَ ٱلرَّوْعُ وَجَآءَتْهُ ٱلْبُشْرَىٰ يُجَٰدِلُنَا فِى قَوْمِ لُوطٍ
Amharic Translation - Africa Academy74. ከኢብራሂም ፍራቻው በሄደለትና ብስራት በመጣችለት ጊዜ በሉጥ ህዝቦች ነገር ይከራከረን ጀመር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ إِبْرَٰهِيمَ لَحَلِيمٌ أَوَّٰهٌ مُّنِيبٌ
Amharic Translation - Africa Academy75. ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ፤ አልቃሻ (እጅግ የሚማፀን) እና መላሳ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓإِبْرَٰهِيمُ أَعْرِضْ عَنْ هَٰذَآ إِنَّهُۥ قَدْ جَآءَ أَمْرُ رَبِّكَ وَإِنَّهُمْ ءَاتِيهِمْ عَذَابٌ غَيْرُ مَرْدُودٍ
Amharic Translation - Africa Academy76. (እነርሱም አሉት): «ኢብራሂም ሆይ! ይህን ክርክር ተው:: እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ መጥቷል:: እነርሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا جَآءَتْ رُسُلُنَا لُوطًا سِىٓءَ بِهِمْ وَضَاقَ بِهِمْ ذَرْعًا وَقَالَ هَٰذَا يَوْمٌ عَصِيبٌ
Amharic Translation - Africa Academy77. መልዕክተኞቻችንም ወደ ሉጥ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ምክንያት አዘነ:: ልቡም በእነርሱ ተጨነቀ:: «ይህ ብርቱ ቀን ነዉ።» አለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَآءَهُۥ قَوْمُهُۥ يُهْرَعُونَ إِلَيْهِ وَمِن قَبْلُ كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ قَالَ يَٰقَوْمِ هَٰٓؤُلَآءِ بَنَاتِى هُنَّ أَطْهَرُ لَكُمْ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَلَا تُخْزُونِ فِى ضَيْفِىٓ أَلَيْسَ مِنكُمْ رَجُلٌ رَّشِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy78. ህዝቦቹም ወደ እርሱ እየተጣደፉ መጡና ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር:: «ህዝቦቼ ሆይ! እነዚህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው:: ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው:: አግቧቸው እናም አላህን ፍሩ:: በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከናንተ ውስጥ አንድ ቅን ሰው እንኳን የለምን?» አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ لَقَدْ عَلِمْتَ مَا لَنَا فِى بَنَاتِكَ مِنْ حَقٍّ وَإِنَّكَ لَتَعْلَمُ مَا نُرِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy79. «ከሴቶች ልጆችህ እኛ ምንም ጉዳይ የሌለን መሆኑን በትክክል ታውቃለህ:: አንተም የምንሻውን በእርግጥ ታውቃለህ።» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ لَوْ أَنَّ لِى بِكُمْ قُوَّةً أَوْ ءَاوِىٓ إِلَىٰ رُكْنٍ شَدِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy80. «በእናንተ ላይ ኃይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር)።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰلُوطُ إِنَّا رُسُلُ رَبِّكَ لَن يَصِلُوٓا۟ إِلَيْكَ فَأَسْرِ بِأَهْلِكَ بِقِطْعٍ مِّنَ ٱلَّيْلِ وَلَا يَلْتَفِتْ مِنكُمْ أَحَدٌ إِلَّا ٱمْرَأَتَكَ إِنَّهُۥ مُصِيبُهَا مَآ أَصَابَهُمْ إِنَّ مَوْعِدَهُمُ ٱلصُّبْحُ أَلَيْسَ ٱلصُّبْحُ بِقَرِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy81. «ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነን:: ህዝቦች ወደ አንተ በክፉ አይደርሱብህም:: ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሂድ:: ከናንተም አንድም ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ሚስትህ ብቻ ስትቀር:: እነሆ እርሷንማ እነርሱን የሚያገኛቸው ስቃይ ሁሉ ያገኛታልና:: ቀጠሯቸው ንጋቱ ላይ ነው:: ንጋቱ ቅርብ አይደለምን?» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا جَآءَ أَمْرُنَا جَعَلْنَا عَٰلِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهَا حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ مَّنضُودٍ
Amharic Translation - Africa Academy82. እናም ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ከተማይቱን ላይዋን ከታችዋ አድርገን ገለበጥናት:: ተከታታይም የሆነን የሸክላ ድንጋይ በእርሷ ላይ አዘነብንባት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مُّسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَ وَمَا هِىَ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ بِبَعِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy83. ከጌታህ ዘንድ ምልክት የተደረገባት ስትሆን (አዘነብናት)። እርሷም (መንደሯ) ከበደለኞቹ ህዝቦች ሩቅ አይደለችም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا قَالَ يَٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُۥ وَلَا تَنقُصُوا۟ ٱلْمِكْيَالَ وَٱلْمِيزَانَ إِنِّىٓ أَرَىٰكُم بِخَيْرٍ وَإِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ مُّحِيطٍ
Amharic Translation - Africa Academy84. ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን:: አላቸውም: «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም:: ስፍርንና ሚዛንን አታጉሉ:: እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ:: እኔም በእናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَٰقَوْمِ أَوْفُوا۟ ٱلْمِكْيَالَ وَٱلْمِيزَانَ بِٱلْقِسْطِ وَلَا تَبْخَسُوا۟ ٱلنَّاسَ أَشْيَآءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا۟ فِى ٱلْأَرْضِ مُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy85. «ህዝቦቼ ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ:: ሰዎችን መብቶቻቸውን አታጓድሉባቸው:: በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَقِيَّتُ ٱللَّهِ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيْكُم بِحَفِيظٍ
Amharic Translation - Africa Academy86. «አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው:: ትክክለኛ አማኞች እንደ ሆናችሁ አላህ በሰጣችሁ ውደዱ። እኔም መካሪ እንጂ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰشُعَيْبُ أَصَلَوٰتُكَ تَأْمُرُكَ أَن نَّتْرُكَ مَا يَعْبُدُ ءَابَآؤُنَآ أَوْ أَن نَّفْعَلَ فِىٓ أَمْوَٰلِنَا مَا نَشَٰٓؤُا۟ إِنَّكَ لَأَنتَ ٱلْحَلِيمُ ٱلرَّشِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy87. «ሹዐይብ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚገዙትን ጣኦታት እንድንተው ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መሥራትን እንድንተው ታዝሃለችን? አንተ በእርግጥ ታጋሹ ቅኑው አንተ ነህና።» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰقَوْمِ أَرَءَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّى وَرَزَقَنِى مِنْهُ رِزْقًا حَسَنًا وَمَآ أُرِيدُ أَنْ أُخَالِفَكُمْ إِلَىٰ مَآ أَنْهَىٰكُمْ عَنْهُ إِنْ أُرِيدُ إِلَّا ٱلْإِصْلَٰحَ مَا ٱسْتَطَعْتُ وَمَا تَوْفِيقِىٓ إِلَّا بِٱللَّهِ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ
Amharic Translation - Africa Academy88. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ እስቲ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን? የከለከልኳችሁንም ነገር በመፈጸም ልለያችሁ አልሻም:: በተቻለኝ ያህል ማበጀትን እንጂ አልሻም:: ለደግ ሥራ መታደሌ በአላህ ፈቃድ ብቻ እንጂ በሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ወደ እርሱም እመለሳለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَٰقَوْمِ لَا يَجْرِمَنَّكُمْ شِقَاقِىٓ أَن يُصِيبَكُم مِّثْلُ مَآ أَصَابَ قَوْمَ نُوحٍ أَوْ قَوْمَ هُودٍ أَوْ قَوْمَ صَٰلِحٍ وَمَا قَوْمُ لُوطٍ مِّنكُم بِبَعِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy89. «ወገኖቼ ሆይ! እኔን መከራከራችሁ የኑህን ህዝቦች ወይም የሁድን ህዝቦች ወይም የሷሊህን ህዝቦች ያገኛቸው ቅጣት ብጤ አይነት እንዲያገኛችሁ አይገፋፋችሁ:: የሉጥም ህዝቦች ከናንተ ሩቅ አይደሉም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱسْتَغْفِرُوا۟ رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوٓا۟ إِلَيْهِ إِنَّ رَبِّى رَحِيمٌ وَدُودٌ
Amharic Translation - Africa Academy90. «ጌታችሁንም ምህረት ለምኑት ከዚያ ወደ እርሱ ተመለሱ። ጌታዬ አዛኝና ወዳድ ነውና።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰشُعَيْبُ مَا نَفْقَهُ كَثِيرًا مِّمَّا تَقُولُ وَإِنَّا لَنَرَىٰكَ فِينَا ضَعِيفًا وَلَوْلَا رَهْطُكَ لَرَجَمْنَٰكَ وَمَآ أَنتَ عَلَيْنَا بِعَزِيزٍ
Amharic Translation - Africa Academy91. «ሹዐይብ ሆይ! ከምትለው ነገር ብዙውን አናውቀዉም (አይገባንም):: እኛም አንተን በኛ ውስጥ ደከማ ሆነህ እናይሃለን:: ጎሶችህም ባልኖሩ ኖሮ በወገርንህ ነበር:: አንተም በእኛ ላይ የተከበርክ አይደለህም።» አሉት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰقَوْمِ أَرَهْطِىٓ أَعَزُّ عَلَيْكُم مِّنَ ٱللَّهِ وَٱتَّخَذْتُمُوهُ وَرَآءَكُمْ ظِهْرِيًّا إِنَّ رَبِّى بِمَا تَعْمَلُونَ مُحِيطٌ
Amharic Translation - Africa Academy92. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ? ጎሳዎቼ በእናንተ ላይ ከአላህ ይልቅ የከበሩ ናቸውን? አላህን ከኋላችሁ ወደ ጀርባ አደረጋችሁት:: ጌታዬ በምትሠሩት ሁሉ ከባቢ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَٰقَوْمِ ٱعْمَلُوا۟ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمْ إِنِّى عَٰمِلٌ سَوْفَ تَعْلَمُونَ مَن يَأْتِيهِ عَذَابٌ يُخْزِيهِ وَمَنْ هُوَ كَٰذِبٌ وَٱرْتَقِبُوٓا۟ إِنِّى مَعَكُمْ رَقِيبٌ
Amharic Translation - Africa Academy93. «ህዝቦቼ ሆይ! በችሎታችሁ ልክ ሥሩ እኔ ሠሪ ነኝ። የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትንና እርሱ ውሸታም የሆነው ማን እንደ ሆነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ:: ጠብቁም እኔም ከናንተ ጋር ተጠባባቂ ነኝና።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا جَآءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا شُعَيْبًا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ بِرَحْمَةٍ مِّنَّا وَأَخَذَتِ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ ٱلصَّيْحَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دِيَٰرِهِمْ جَٰثِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy94. ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሹዐይብንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን:: እነዚያን የበደሉትንም (የጂብሪል) ጩኸት ያዘቻቸው። በየቤቶቻቸዉም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَأَن لَّمْ يَغْنَوْا۟ فِيهَآ أَلَا بُعْدًا لِّمَدْيَنَ كَمَا بَعِدَتْ ثَمُودُ
Amharic Translation - Africa Academy95. በእርሷ ውስጥ እንዳልነበሩ ሆኑ:: አስተዉሉ! ሠሙድ ከአላህ እዝነት እንደራቀች መድየንም ትራቅ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلْطَٰنٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy96. ሙሳንም በታዐምራቶቻችንና በግልጽ ብርሃን በእርግጥ ላክነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦ فَٱتَّبَعُوٓا۟ أَمْرَ فِرْعَوْنَ وَمَآ أَمْرُ فِرْعَوْنَ بِرَشِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academyወደ ፈርዖንና ወደስዎቹ ላክነው፡፡የፈርዖንን ነገር ህዝቦቹ ተከተሉ፡፡ የፈርዖን ነገር ቀጥተኛ አል ነበረም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَقْدُمُ قَوْمَهُۥ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فَأَوْرَدَهُمُ ٱلنَّارَ وَبِئْسَ ٱلْوِرْدُ ٱلْمَوْرُودُ
Amharic Translation - Africa Academyበትንሳኤ ቀን ህዝቦቹን ይቀድማል፡፡ ከዚያም ወደ አሳት ያወርዳቸዋል፡፡ የሚገቡትም አገባብ ምንኛ ከፋ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأُتْبِعُوا۟ فِى هَٰذِهِۦ لَعْنَةً وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ بِئْسَ ٱلرِّفْدُ ٱلْمَرْفُودُ
Amharic Translation - Africa Academy99. በዚችም በቅርቢቱ ዓለም እርግማንን አስከተልናቸው:: በትንሳኤም ቀን እንደዚሁ። የተሰጡት ስጦታ ምንኛ ከፋ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلْقُرَىٰ نَقُصُّهُۥ عَلَيْكَ مِنْهَا قَآئِمٌ وَحَصِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከላይ የተነገረው ከከተሞቹ ወሬዎች የተወሰነው ነው:: ባንተ ላይ እንተርከዋለን:: ከእርሷ ቋሚና እጭድም የሆነ አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا ظَلَمْنَٰهُمْ وَلَٰكِن ظَلَمُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ فَمَآ أَغْنَتْ عَنْهُمْ ءَالِهَتُهُمُ ٱلَّتِى يَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مِن شَىْءٍ لَّمَّا جَآءَ أَمْرُ رَبِّكَ وَمَا زَادُوهُمْ غَيْرَ تَتْبِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy101. እኛም አልበደልናቸዉም:: ግን ነፍሶቻቸውን በደሉ:: የጌታህ ጉዳይ በመጣ ጊዜ እነዚያ ከአላህ ሌላ የሚገዟቸው አማልክቶቻቸው ሁሉ በምንም አላዳኗቸዉም:: ከማክሰርም በስተቀር ምንም አልጨመሩላቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَذَٰلِكَ أَخْذُ رَبِّكَ إِذَآ أَخَذَ ٱلْقُرَىٰ وَهِىَ ظَٰلِمَةٌ إِنَّ أَخْذَهُۥٓ أَلِيمٌ شَدِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት የከተሞችን ሰዎች በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ ልክ እንደዚህ ነው:: ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚና ብርቱ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لِّمَنْ خَافَ عَذَابَ ٱلْـَٔاخِرَةِ ذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّجْمُوعٌ لَّهُ ٱلنَّاسُ وَذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّشْهُودٌ
Amharic Translation - Africa Academy103. በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ:: ይህ የትንሳኤ ቀን ሰዎች በእርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው:: ይህ የሚጣዱት ቀን ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا نُؤَخِّرُهُۥٓ إِلَّا لِأَجَلٍ مَّعْدُودٍ
Amharic Translation - Africa Academy104. ይህንን ቀን ለተቆጠረም (ለተወሰነ) ጊዜ እንጂ አናቆየዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ يَأْتِ لَا تَكَلَّمُ نَفْسٌ إِلَّا بِإِذْنِهِۦ فَمِنْهُمْ شَقِىٌّ وَسَعِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy105. በሚመጣ ቀን ማንኛዉም ነፍስ በእርሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትናገርም:: ከእነርሱም መናጢም (እድለቢስ) እድለኛም አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَمَّا ٱلَّذِينَ شَقُوا۟ فَفِى ٱلنَّارِ لَهُمْ فِيهَا زَفِيرٌ وَشَهِيقٌ
Amharic Translation - Africa Academy106. እነዚያ ያመጹትማ በእሳት ውስጥ ናቸው:: ለእነርሱ በእርሷ ውስጥ ማናፋትና መንሰቅሰቅ አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَٰلِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلْأَرْضُ إِلَّا مَا شَآءَ رَبُّكَ إِنَّ رَبَّكَ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከፈለገው በስተቀር ሰማያትና ምድር እስከዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ በእሳት ውስጥ ይኖራሉ:: ጌታህ የሚፈልገውን ሠሪ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَمَّا ٱلَّذِينَ سُعِدُوا۟ فَفِى ٱلْجَنَّةِ خَٰلِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلْأَرْضُ إِلَّا مَا شَآءَ رَبُّكَ عَطَآءً غَيْرَ مَجْذُوذٍ
Amharic Translation - Africa Academy108. እነዚያ እድለኞቹማ ጌታ ከሻው በስተቀር ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሆነው በገነት ውስጥ ይኖራሉ:: የማያቋርጥ ስጦታን ተሰጡ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَا تَكُ فِى مِرْيَةٍ مِّمَّا يَعْبُدُ هَٰٓؤُلَآءِ مَا يَعْبُدُونَ إِلَّا كَمَا يَعْبُدُ ءَابَآؤُهُم مِّن قَبْلُ وَإِنَّا لَمُوَفُّوهُمْ نَصِيبَهُمْ غَيْرَ مَنقُوصٍ
Amharic Translation - Africa Academy109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከሓዲያን ከሚገዙት ጣኦት በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: አባቶቻቸው ከዚህ በፊት እንደሚገዙት እንጂ አይገዙም:: እኛም እነዚህን ፈንታቸውን የማይጓደል ሲሆን የምንሞላላቸው ነን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ فَٱخْتُلِفَ فِيهِ وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ لَقُضِىَ بَيْنَهُمْ وَإِنَّهُمْ لَفِى شَكٍّ مِّنْهُ مُرِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy110. ለሙሳም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው አሁን ይፈረድ ነበር:: እነርሱም ከእርሱ ከቁርኣን አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنَّ كُلًّا لَّمَّا لَيُوَفِّيَنَّهُمْ رَبُّكَ أَعْمَٰلَهُمْ إِنَّهُۥ بِمَا يَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy111. ሁሉንም ጌታህ ሥራዎቻቸውን ምንዳቸውን በእርግጥ ይሞላላቸዋል:: እርሱ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱسْتَقِمْ كَمَآ أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا۟ إِنَّهُۥ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy112. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደታዘዝከው ቀጥ በል። ካንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ። ወሰንንም አትለፉ። እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَرْكَنُوٓا۟ إِلَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ فَتَمَسَّكُمُ ٱلنَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِنْ أَوْلِيَآءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy113. ወደ እነዚያም ወደ በደሉት ህዝቦች አትዘንበሉ:: እሳት ትነካችኋለችና:: ከአላህ ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም ከዚያ አትረዱም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ طَرَفَىِ ٱلنَّهَارِ وَزُلَفًا مِّنَ ٱلَّيْلِ إِنَّ ٱلْحَسَنَٰتِ يُذْهِبْنَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ ذَٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّٰكِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy114. ሶላትንም በቀን ጫፍና ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም:: መልካም ሥራዎች ኃጢአቶችን ያስወግዳሉና:: ይህ ለተገሳጮች ሁሉ ግሳጼ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱصْبِرْ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy115. ታገስ አላህ የበጎ ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَوْلَا كَانَ مِنَ ٱلْقُرُونِ مِن قَبْلِكُمْ أُو۟لُوا۟ بَقِيَّةٍ يَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْفَسَادِ فِى ٱلْأَرْضِ إِلَّا قَلِيلًا مِّمَّنْ أَنجَيْنَا مِنْهُمْ وَٱتَّبَعَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مَآ أُتْرِفُوا۟ فِيهِ وَكَانُوا۟ مُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy116. ከናንተ በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት (ሰዎች) ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ሥራዎች ቅሪት ባለቤቶች ለምን አልነበሩም? ግን ከእነርሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ ከለከሉና ዳኑ:: እነዚያም የበደሉት ሰዎች አልከለከሉም። በእርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ አመጠኞችም ነበሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا كَانَ رَبُّكَ لِيُهْلِكَ ٱلْقُرَىٰ بِظُلْمٍ وَأَهْلُهَا مُصْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy117. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከተሞችን ባለቤቶቻቸው መልካም ሠሪዎች ሆነው ሳሉ በመበደል የሚያጠፋቸው አልነበረም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ شَآءَ رَبُّكَ لَجَعَلَ ٱلنَّاسَ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَلَا يَزَالُونَ مُخْتَلِفِينَ
Amharic Translation - Africa Academy118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሻ ኖሮ ሰዎችን ሁሉ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር። የተለያዩም ከመሆን አይወገዱም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا مَن رَّحِمَ رَبُّكَ وَلِذَٰلِكَ خَلَقَهُمْ وَتَمَّتْ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ ٱلْجِنَّةِ وَٱلنَّاسِ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy119. ጌታህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር ከመለያየት አይወገዱም:: ለዚሁም ነው የፈጠራቸው:: የጌታህ ቃልም «ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ።» በማለት ተፈጸመች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكُلًّا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy120. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቹም ዜናዎች ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናጸናበትን እንተርክልሀለን። በዚህችም ሱራ እውነቱ ነገር፣ ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሀል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقُل لِّلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ ٱعْمَلُوا۟ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمْ إِنَّا عَٰمِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy121. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያም ለማያምኑት (እንዲህ) በላቸው: «ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሥሩ:: እኛ ሠሪዎች ነን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱنتَظِرُوٓا۟ إِنَّا مُنتَظِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy122. «የራሳችሁን ውጤት ተጠባበቁ እኛ ተጠባባቂዎች ነንና።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِلَّهِ غَيْبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَإِلَيْهِ يُرْجَعُ ٱلْأَمْرُ كُلُّهُۥ فَٱعْبُدْهُ وَتَوَكَّلْ عَلَيْهِ وَمَا رَبُّكَ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy123. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰማያትና በምድር ያለው ሚስጥር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: ሁሉም ነገር ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል:: ስለዚህ እሱን ብቻ ተገዛው:: በእርሱም ላይ ብቻ ተመካ:: ጌታህም ከሚሰሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→