وَٱلَّذِينَ كَسَبُوا۟ ٱلسَّيِّـَٔاتِ جَزَآءُ سَيِّئَةٍۭ بِمِثْلِهَا وَتَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ مَّا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنْ عَاصِمٍ كَأَنَّمَآ أُغْشِيَتْ وُجُوهُهُمْ قِطَعًا مِّنَ ٱلَّيْلِ مُظْلِمًا أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. እነዚያ ኃጢአቶችን የሠሩት ደግሞ ኃጢአቲቱን የሚመጥን ቅጣት አለባቸው:: ውርደትም ትሸፍናቸዋለች :: እነርሱ ከአላህ ቅጣት ጠባቂ የላቸዉም:: ፊቶቻቸው በድቅድቅ ጨለማ ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይሆናሉ:: እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእነዚያም ኃጢአቶችን ለሠሩት የኃጢኣቲቱ ቅጣት በብጤዋ አለቻቸው፡፡ ውርደትም ትሸፍናቸዋለች፡፡ ለእነሱ ከአላህ (ቅጣት) ጠባቂ የላቸውም፡፡ ፊቶቻቸው ከጨለመ ሌሊት ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይኾናሉ፡፡ እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው፡፡