caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yunus፣ አንቀጽ 71

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 51 · 10:71

وَٱتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ نُوحٍ إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِۦ يَٰقَوْمِ إِن كَانَ كَبُرَ عَلَيْكُم مَّقَامِى وَتَذْكِيرِى بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَعَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلْتُ فَأَجْمِعُوٓا۟ أَمْرَكُمْ وَشُرَكَآءَكُمْ ثُمَّ لَا يَكُنْ أَمْرُكُمْ عَلَيْكُمْ غُمَّةً ثُمَّ ٱقْضُوٓا۟ إِلَىَّ وَلَا تُنظِرُونِ

Amharic Translation - Africa Academy71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኑህንም ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው:: ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውሱ «ህዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙን ጊዜ መቆየቴ የአላህንም ተዓምራት ለእናንተ ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆንባችሁም በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ:: ነገራችሁንም ከምታጋሯቸው ጣኦታት ጋር ሆናችሁ እስቲ ቁረጡ:: ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን ግለጹት:: ከዚያም የሻችሁትን ወደ እኔ አድርሱ:: ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየኑሕንም ወሬ በእነሱ ላይ አንብብላቸው፡፡ ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙ ጊዜ መቆየቴ በአላህም ተዓምራት ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆን፤ በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ፡፡ ነገራችሁንም ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ጋር ሆናችሁ ቁረጡ፡፡ ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን (ግለጹት)፡፡ ከዚያም (የሻችሁትን) ወደእኔ አድርሱ፡፡ ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70