caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yunus፣ አንቀጽ 10

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 51 · 10:10

دَعْوَىٰهُمْ فِيهَا سُبْحَٰنَكَ ٱللَّهُمَّ وَتَحِيَّتُهُمْ فِيهَا سَلَٰمٌ وَءَاخِرُ دَعْوَىٰهُمْ أَنِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy10. በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው የሚሆነው «ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ።» ማለት ብቻ ነው:: በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው:: የመጨረሻ ጸሎታቸዉም «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው።» ማለት ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት) ነው፡፡ በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይሁን (ማለት) ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70