قُلْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَكُمُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ فَمَنِ ٱهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِى لِنَفْسِهِۦ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا وَمَآ أَنَا۠ عَلَيْكُم بِوَكِيلٍ
Amharic Translation - Africa Academy108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ:: በእርሱ የተመራም የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው:: የተሳሳተም የሚሳሳተው ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: እኔ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«እናንተ ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ (በእርሱ) የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በራሱ ላይ ነው፡፡ እኔም በእናንተ ላይ ተጠባበቂ አይደለሁም» በላቸው፡፡