أَكَانَ لِلنَّاسِ عَجَبًا أَنْ أَوْحَيْنَآ إِلَىٰ رَجُلٍ مِّنْهُمْ أَنْ أَنذِرِ ٱلنَّاسَ وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَنَّ لَهُمْ قَدَمَ صِدْقٍ عِندَ رَبِّهِمْ قَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎችን (ከሓዲያንን) አስፈራራ፤ እነዚያን ያመኑትን ደግሞ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መሆኑን አብስር» በማለት ከእነርሱ መካከል ወደ ሆነ አንድ ሰው ራዕይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ሆነባቸውን? ከሓዲያን «ይህ (ሰው) ግልጽ ድግምተኛ ነው።» አሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ሰዎችን አስፈራራ፡፡ እነዚያንም ያመኑትን ለእነሱ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን አብስር» በማለት ከነርሱው ወደ ኾነ አንድ ሰው ራእይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ኾነባቸውን ከሓዲዎቹ፡- «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምተኛ ነው» አሉ፡፡