caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yunus፣ አንቀጽ 61

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 51 · 10:61

وَمَا تَكُونُ فِى شَأْنٍ وَمَا تَتْلُوا۟ مِنْهُ مِن قُرْءَانٍ وَلَا تَعْمَلُونَ مِنْ عَمَلٍ إِلَّا كُنَّا عَلَيْكُمْ شُهُودًا إِذْ تُفِيضُونَ فِيهِ وَمَا يَعْزُبُ عَن رَّبِّكَ مِن مِّثْقَالِ ذَرَّةٍ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَا فِى ٱلسَّمَآءِ وَلَآ أَصْغَرَ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكْبَرَ إِلَّا فِى كِتَٰبٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛዉም ነገር ላይ አትሆንም፤ ከእርሱም ከቁርኣን ትንሽም አታነብም፤ ማንኛውንም ሥራ አንተም ሆንክ ሰዎቹ አትሠሩም፤ በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ተግባር ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ :: በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳን ከጌታህ እውቀት አይርቅም:: ከዚያም ያነሰም ሆነ የተለቀ ነገር በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ የለም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛውም ነገር ላይ አትሆንም፣ ከርሱም ከቁርኣን አታነብም፣ ማንኛውንም ሥራ (አንተም ሰዎቹም) አትሠሩም በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ፡፡ በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል ከጌታህ (ዕውቀት) አይርቅም፡፡ ከዚያም ያነሰ የተለቀም የለም፤ በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70