إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًا وَعْدَ ٱللَّهِ حَقًّا إِنَّهُۥ يَبْدَؤُا۟ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ لِيَجْزِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ بِٱلْقِسْطِ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَهُمْ شَرَابٌ مِّنْ حَمِيمٍ وَعَذَابٌ أَلِيمٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَكْفُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4. (ሰዎች ሆይ!) የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ብቻ ነው:: ይህም የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው:: እርሱ መፍጠርን ይጀምራል:: ከዚያም እነዚያ ያመኑትንና መልካም የሠሩትን ሰዎች በትክክል ይመነዳ ዘንድ ፍጡራንን ከሞት በኋላ ህያው ያደርጋል:: እነዚያ የካዱት ክፍሎች ግን በክህደታቸው ምክንያት የፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሁላችሁም ኾናችሁ መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው፡፡ (ይህም) የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው፤ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፡፡ ከዚያም እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሠሩትን በትክክል ይመነዳ ዘንድ ይመልሰዋል፡፡ እነዚያ የካዱትም ይክዱት በነበሩት ነገር ለነርሱ ከፈላ ውሃ የኾነ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡