وَيَقُولُونَ لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْهِ ءَايَةٌ مِّن رَّبِّهِۦ فَقُلْ إِنَّمَا ٱلْغَيْبُ لِلَّهِ فَٱنتَظِرُوٓا۟ إِنِّى مَعَكُم مِّنَ ٱلْمُنتَظِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም?» ይላሉ:: «ሩቅ ነገር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: እናንተም ተጠባበቁ እኔም ከናንተው ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡