caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yunus፣ አንቀጽ 90

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 51 · 10:90

وَجَٰوَزْنَا بِبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱلْبَحْرَ فَأَتْبَعَهُمْ فِرْعَوْنُ وَجُنُودُهُۥ بَغْيًا وَعَدْوًا حَتَّىٰٓ إِذَآ أَدْرَكَهُ ٱلْغَرَقُ قَالَ ءَامَنتُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱلَّذِىٓ ءَامَنَتْ بِهِۦ بَنُوٓا۟ إِسْرَٰٓءِيلَ وَأَنَا۠ مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy90. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሳለፍናቸው:: ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው:: የመስመጥ አደጋ ባገኘውም ጊዜ «አመንኩ:: እነሆ ከዚያ የእሥራኤል ልጆች ካመኑበት አምላክ በስተቀር ሌላ የእውነት አምላክ የለም:: እኔም ከታዛዦቹ (ሙስሊሞች) አንዱ ነኝ።» አለ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70