وَإِذَآ أَذَقْنَا ٱلنَّاسَ رَحْمَةً مِّنۢ بَعْدِ ضَرَّآءَ مَسَّتْهُمْ إِذَا لَهُم مَّكْرٌ فِىٓ ءَايَاتِنَا قُلِ ٱللَّهُ أَسْرَعُ مَكْرًا إِنَّ رُسُلَنَا يَكْتُبُونَ مَا تَمْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎች ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን ምቾትን ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነርሱ በተዓምራቶቻችን በማላገጥ ተንኮል ይኖራቸዋል:: «አላህ ቅጣቱ ፈጣን ነው።» በላቸው። መልዕክተኞቻችን የምታሴሩትን ነገር ሁሉ በእርግጥ ይጽፋሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሰዎችንም ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን (ዝናብና ምቾትን) ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነሱ በተዓምራቶቻችን (በማላገጥ) ተንኮል ይኖራቸዋል፡፡ አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን ነገር በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው፡፡