caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Yunus፣ አንቀጽ 15

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 51 · 10:15

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَاتُنَا بَيِّنَٰتٍ قَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا ٱئْتِ بِقُرْءَانٍ غَيْرِ هَٰذَآ أَوْ بَدِّلْهُ قُلْ مَا يَكُونُ لِىٓ أَنْ أُبَدِّلَهُۥ مِن تِلْقَآئِ نَفْسِىٓ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ إِنِّىٓ أَخَافُ إِنْ عَصَيْتُ رَبِّى عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን ግልጽ ሆነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት (የማይሹት) ሰዎች «ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው።» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም:: ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ አልከተልም:: እኔ በጌታዬ ትዕዛዝ ላይ ባምጽ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአንቀጾቻችንም ግልጽ ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው ይላሉ፡፡ እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም፡፡ ወደ እኔ የሚወርደውን እንጂ አልከተልም፡፡ እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70