caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Alaq العلق

19 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 1

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٱقْرَأْ بِٱسْمِ رَبِّكَ ٱلَّذِى خَلَقَ

Amharic Translation - Africa Academy1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ (ሁሉንም ነገር) በፈጠረ ጌታህ ስም (ጀምርና) አንብብ! {1}

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ مِنْ عَلَقٍ

Amharic Translation - Africa Academy2. ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱقْرَأْ وَرَبُّكَ ٱلْأَكْرَمُ

Amharic Translation - Africa Academy3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንብብ! ጌታህም በጣም ቸር ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِى عَلَّمَ بِٱلْقَلَمِ

Amharic Translation - Africa Academy4. ያ በብዕር ያስተማረ (ጌታ)፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

Amharic Translation - Africa Academy5. የሰውን ልጅ ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ (ጌታ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّآ إِنَّ ٱلْإِنسَٰنَ لَيَطْغَىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy6. በእውነቱ የሰው ልጅ ወሰንን ያልፋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَن رَّءَاهُ ٱسْتَغْنَىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy7. ራሱን የተብቃቃ ሆኖ በማየቱ ምክንያት

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلرُّجْعَىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy8. መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَرَءَيْتَ ٱلَّذِى يَنْهَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy9. ያንን የሚከለክለውን አየህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَبْدًا إِذَا صَلَّىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy10. ባሪያን በሰገደ ጊዜ (የሚከለክለውን):

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَرَءَيْتَ إِن كَانَ عَلَى ٱلْهُدَىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy11. እስቲ ንገረኝ (ተከልካዩ ባሪያየ) በትክክል መንገድ ላይ ቢሆን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ أَمَرَ بِٱلتَّقْوَىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy12. ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ ምን እንደሚሆን አየህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَرَءَيْتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy13. እስቲ ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና ከእምነት ቢሸሽ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ يَعْلَم بِأَنَّ ٱللَّهَ يَرَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy14. አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّا لَئِن لَّمْ يَنتَهِ لَنَسْفَعًۢا بِٱلنَّاصِيَةِ

Amharic Translation - Africa Academy15. ይታቀብ፤ የማይከለከል ከሆነ አናቱን ይዘን አንጎትተዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نَاصِيَةٍ كَٰذِبَةٍ خَاطِئَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy16. ያቺን ውሸታምና ስህተተኛ የሆነችውን አናቱን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلْيَدْعُ نَادِيَهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy17. ሸንጎውንም ይጥራ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَنَدْعُ ٱلزَّبَانِيَةَ

Amharic Translation - Africa Academy18. እኛም ዘበኞቻችንን እንጠራለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَٱسْجُدْ وَٱقْتَرِب

Amharic Translation - Africa Academy19. በጭራሽ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ለሚል ከሓዲ አትታዘዘው፤ ስገድ፤ ወደ አላህም ተቃረብ። {1}

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70