ሱረቱ Ad-Dukhaan الدخان
59 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 64
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ حمٓ
Amharic Translation - Africa Academy1. ሓ፤ ሚይም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْكِتَٰبِ ٱلْمُبِينِ
Amharic Translation - Africa Academy2. ሁሉን ነገር አብራሪ በሆነው መጽሐፍ እንምላለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ فِى لَيْلَةٍ مُّبَٰرَكَةٍ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy3. እኛ ቁርኣኑን በዚያች በተባረከችው ሌሊት ውስጥ አወረድነው:: እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy4. በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይለያል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْرًا مِّنْ عِندِنَآ إِنَّا كُنَّا مُرْسِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy5. ከእኛ ዘንድ የሆነ ትዕዛዝ ሲሆን አወረድነው:: እኛ መልዕክተኞችን ላኪዎች ነበርንና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኞች) ከጌታህ በሆነው ችሮታ (ተላኩ)። እነሆ እርሱ(አላህ) የሚባለዉን ሁሉ ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَآ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy7. የሰማያት፤ የምድር እና በመካከላቸው ያሉ ነገሮች ሁሉ ጌታ ከሆነው (ተላኩ)። የምታረጋግጡ እንደሆናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መሆኑን እወቁ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ رَبُّكُمْ وَرَبُّ ءَابَآئِكُمُ ٱلْأَوَّلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy8. ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም። ህያው ያደርጋል። ህይወትም ይነሳል። ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ هُمْ فِى شَكٍّ يَلْعَبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy9. በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲሆኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱرْتَقِبْ يَوْمَ تَأْتِى ٱلسَّمَآءُ بِدُخَانٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ( ሰዎችን) የሚሸፍን በሆነ ግልጽ ጭስ ሰማይ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَغْشَى ٱلنَّاسَ هَٰذَا عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy11.ሰዎችን ይሸፍናል ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَّبَّنَا ٱكْشِفْ عَنَّا ٱلْعَذَابَ إِنَّا مُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. ጌታችን ሆይ! ክእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን:: እኛ ትክክለኛ አማኞች ነንና (ይላሉ::)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَنَّىٰ لَهُمُ ٱلذِّكْرَىٰ وَقَدْ جَآءَهُمْ رَسُولٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy13. አስረጂ መልዕክተኛ የመጣላቸው እና በአላህ የካዱ ሲሆኑ (ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ تَوَلَّوْا۟ عَنْهُ وَقَالُوا۟ مُعَلَّمٌ مَّجْنُونٌ
Amharic Translation - Africa Academy14. ከዚያም «ከሰው የተስተማረ እብድ ነው» ያሉ ሲሆኑ ከእርሱ ዞሩ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا كَاشِفُوا۟ ٱلْعَذَابِ قَلِيلًا إِنَّكُمْ عَآئِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy15. እኛ ቅጣትን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን። እናንተ ግን ወደ ክህደታችሁ በእርግጥ አንደገና ተመላሾች ናችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ نَبْطِشُ ٱلْبَطْشَةَ ٱلْكُبْرَىٰٓ إِنَّا مُنتَقِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy16. ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን እኛ ተበቃዮች ነን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ فَتَنَّا قَبْلَهُمْ قَوْمَ فِرْعَوْنَ وَجَآءَهُمْ رَسُولٌ كَرِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy17. ከእነርሱ በፊት የፈርዖንን ህዝቦች በእርግጥ ሞከርን:: ክቡር መልዕክተኛም መጣላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَنْ أَدُّوٓا۟ إِلَىَّ عِبَادَ ٱللَّهِ إِنِّى لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy18. «የአላህን ባሮች ወደ እኔ አድርሱ (ለኔ ስጡኝ):: እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَن لَّا تَعْلُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِنِّىٓ ءَاتِيكُم بِسُلْطَٰنٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy19. «በአላህም ላይ ላትኮሩ። እኔ ግልጽ የሆነን አስረጂ ያመጣሁላችሁ ነኝና በማለት መጣላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنِّى عُذْتُ بِرَبِّى وَرَبِّكُمْ أَن تَرْجُمُونِ
Amharic Translation - Africa Academy20. «እኔ እንዳትወግሩኝ በጌታዬና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن لَّمْ تُؤْمِنُوا۟ لِى فَٱعْتَزِلُونِ
Amharic Translation - Africa Academy21. «በእኔም ባታምኑ ራቁኝ። ተውኝ።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَدَعَا رَبَّهُۥٓ أَنَّ هَٰٓؤُلَآءِ قَوْمٌ مُّجْرِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy22. «ቀጥሎም እነዚህ አመጸኞች ህዝቦች ናቸው (አጥፋቸው)።» ሲል ጌታውን ለመነ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَسْرِ بِعِبَادِى لَيْلًا إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy23. (ጌታዉም አለ) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ሂድ። እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتْرُكِ ٱلْبَحْرَ رَهْوًا إِنَّهُمْ جُندٌ مُّغْرَقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy24. «ባህሩንም የተከፈተ ሆኖ ተወው፤ እነርሱ የሚሰምጡ ሰራዊት ናቸውና» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَمْ تَرَكُوا۟ مِن جَنَّٰتٍ وَعُيُونٍ
Amharic Translation - Africa Academy25. ከአትክልቶችና ከምንጮች ብዙ ነገሮችን ትተው ሄዱ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَزُرُوعٍ وَمَقَامٍ كَرِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy26. ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَعْمَةٍ كَانُوا۟ فِيهَا فَٰكِهِينَ
Amharic Translation - Africa Academy27. በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ትተው ሞቱ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَٰلِكَ وَأَوْرَثْنَٰهَا قَوْمًا ءَاخَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy28. ነገሩ ልክ እንደዚህ ሆነ፤ ለሌሎች ህዝቦች አወረስናትም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَا بَكَتْ عَلَيْهِمُ ٱلسَّمَآءُ وَٱلْأَرْضُ وَمَا كَانُوا۟ مُنظَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy29. ሰማይና ምድር በእነርሱ ላይ አላለቀሱም:: የሚቆዩም አልነበሩም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ نَجَّيْنَا بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ مِنَ ٱلْعَذَابِ ٱلْمُهِينِ
Amharic Translation - Africa Academy30. የኢስራኢል ልጆችን ከዚያ አዋራጅ ከሆነው ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مِن فِرْعَوْنَ إِنَّهُۥ كَانَ عَالِيًا مِّنَ ٱلْمُسْرِفِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. ከፈርዖን እርሱ (ፈርዖውን) የኮራ ከወሰን አላፊዎችም አንዱ ነበርና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدِ ٱخْتَرْنَٰهُمْ عَلَىٰ عِلْمٍ عَلَى ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy32. ከማወቅም ጋር ከዓለም ህዝቦች መካከል በእርግጥ መረጥናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَءَاتَيْنَٰهُم مِّنَ ٱلْـَٔايَٰتِ مَا فِيهِ بَلَٰٓؤٌا۟ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy33. ከተአምራቶችም በውስጡ ግልጽ የሆነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَيَقُولُونَ
Amharic Translation - Africa Academy34. እነዚህ (የመካ ካሓዲያን) በእርግጥ ይላሉ:
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنْ هِىَ إِلَّا مَوْتَتُنَا ٱلْأُولَىٰ وَمَا نَحْنُ بِمُنشَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy35. «እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ (ሌላ) አይደለችም። እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأْتُوا۟ بِـَٔابَآئِنَآ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy36. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ አባቶቻችንን እስቲ አምጡልን።» (ይላሉ)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَهُمْ خَيْرٌ أَمْ قَوْمُ تُبَّعٍ وَٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ أَهْلَكْنَٰهُمْ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ مُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy37. እነርሱ በላጮች ናቸውን? ወይስ የቱበዕ ህዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? እነርሱን አጠፋናቸው። እነርሱ አመጸኞች ነበሩ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا خَلَقْنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا لَٰعِبِينَ
Amharic Translation - Africa Academy38. ሰማያትና ምድርን በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا خَلَقْنَٰهُمَآ إِلَّا بِٱلْحَقِّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy39. ሁለቱንም በቁምነገር እንጂ አልፈጠርናቸዉም:: ግን አብዛሀኞቻቸው አያውቀዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ يَوْمَ ٱلْفَصْلِ مِيقَٰتُهُمْ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy40. የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ لَا يُغْنِى مَوْلًى عَن مَّوْلًى شَيْـًٔا وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy41. ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይረዱበት ቀን ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا مَن رَّحِمَ ٱللَّهُ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy42. አላህ ያዘነለትና ያመነ ብቻ ሲቀር:: (እርሱ ይረዳል) እርሱ (አላህ) ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ شَجَرَتَ ٱلزَّقُّومِ
Amharic Translation - Africa Academy43. የዘቁም ዛፍ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
طَعَامُ ٱلْأَثِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy44. የኃጢአተኞች ምግብ ናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَٱلْمُهْلِ يَغْلِى فِى ٱلْبُطُونِ
Amharic Translation - Africa Academy45. እሱም ልክ እንደ ዘይት አተላ በሆዶች ውስጥ ይፈላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَغَلْىِ ٱلْحَمِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy46. እንደገነፈለ ውሃ አፈላል የሚፈላ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خُذُوهُ فَٱعْتِلُوهُ إِلَىٰ سَوَآءِ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy47. ያዙትና ወደ ገሀነም መካከል (ውስጥ) በሀይል ጎትቱት (ገፍትሩት)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ صُبُّوا۟ فَوْقَ رَأْسِهِۦ مِنْ عَذَابِ ٱلْحَمِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy48. ከዚያም በራሱ ላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذُقْ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْكَرِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy49. (ይባላልም) «ቅመስ አንተ አሸናፊው፤ ክቡር የነበርክ ነህና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ هَٰذَا مَا كُنتُم بِهِۦ تَمْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy50. «ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلْمُتَّقِينَ فِى مَقَامٍ أَمِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy51. ጥንቁቆች በእርግጥ በደህናማ መኖሪያ ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فِى جَنَّٰتٍ وَعُيُونٍ
Amharic Translation - Africa Academy52. በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَلْبَسُونَ مِن سُندُسٍ وَإِسْتَبْرَقٍ مُّتَقَٰبِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy53. ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሆነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَٰلِكَ وَزَوَّجْنَٰهُم بِحُورٍ عِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy54. ነገሩ ልክ እንደዚህ ነው። ዓይናማዎች የሆኑን ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَدْعُونَ فِيهَا بِكُلِّ فَٰكِهَةٍ ءَامِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy55. በእርሷ ውስጥም የተማመኑ ሆነው ከፍራፍሬ ሁሉ ያዛሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا يَذُوقُونَ فِيهَا ٱلْمَوْتَ إِلَّا ٱلْمَوْتَةَ ٱلْأُولَىٰ وَوَقَىٰهُمْ عَذَابَ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy56. የፊተኛይቱን ሞት እንጂ ዳግመኛ በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም:: የገሀነምንም ቅጣት አላህ ጠብቋቸዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَضْلًا مِّن رَّبِّكَ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ይህም ) ከጌታህ (አላህ) የሆነ ትሩፋት ሲሆን ይህም እርሱ ታላቁ እድል ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِنَّمَا يَسَّرْنَٰهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣኑንም በቋንቋህ ያገራነው ህዝቦች ይገነዘቡት ዘንድ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱرْتَقِبْ إِنَّهُم مُّرْتَقِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy59. ተጠባበቅ:: እነርሱም ተጠባባቂዎች ናቸውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→