caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Az-Zukhruf الزخرف

89 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 63

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ حمٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. ሓ፤ሚም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْكِتَٰبِ ٱلْمُبِينِ

Amharic Translation - Africa Academy2. ገላጭ በሆነው መጽሐፍ እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا جَعَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. እኛ ታውቁ ዘንድ ቁርኣንን በዐረብኛ ቋንቋ አደረግነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّهُۥ فِىٓ أُمِّ ٱلْكِتَٰبِ لَدَيْنَا لَعَلِىٌّ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy4. እርሱም እኛ ዘንድ በመጽሐፎቹ እናት (መሰረት) ውስጥ ያለ፤ እርግጥ ከፍተኛ ማዕረግ ያለውና በጥበብ የተሞላ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَنَضْرِبُ عَنكُمُ ٱلذِّكْرَ صَفْحًا أَن كُنتُمْ قَوْمًا مُّسْرِفِينَ

Amharic Translation - Africa Academy5. ድንበር አላፊዎች ህዝቦች በመሆናችሁ ምክኒያት ቁርኣኑን ከማውረድ ከናንተ ማገድን እናግዳለንን? (አናግድም)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَمْ أَرْسَلْنَا مِن نَّبِىٍّ فِى ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy6. በፊተኞቹም ህዝቦች ውስጥ ከነብያት መካከል ብዙን ልከናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا يَأْتِيهِم مِّن نَّبِىٍّ إِلَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy7. ከነብይም አንድንም የሚመጣላቸው አልነበረም በእርሱ ይቀልዱበት (ያፌዙበት) የነበሩ ቢሆን እንጂ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَهْلَكْنَآ أَشَدَّ مِنْهُم بَطْشًا وَمَضَىٰ مَثَلُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy8. ከእነርሱም በሀይል ይበልጥ የበረቱትን አጥፍተናል:: የፊተኞቹም አጠፋፍ ምሳሌ አልፏል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ لَيَقُولُنَّ خَلَقَهُنَّ ٱلْعَزِيزُ ٱلْعَلِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን ማን ፈጠራቸው?» ብለህ ብትጠይቃቸው «ያ ሁሉን አሸናፊዉና ሁሉን አዋቂው ጌታ ነው የፈጠራቸው» ይላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلْأَرْضَ مَهْدًا وَجَعَلَ لَكُمْ فِيهَا سُبُلًا لَّعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. አላህ ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ በእርሷም ውስጥ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ መንገዶችን ያደረገላችሁ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِى نَزَّلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءًۢ بِقَدَرٍ فَأَنشَرْنَا بِهِۦ بَلْدَةً مَّيْتًا كَذَٰلِكَ تُخْرَجُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. ያም ከሰማይ ውሃን በልክ ያወረደላችሁ ነው። በእርሱም (በውሀው) የሞተችውን አገር ህያው አደረግን:: (ሰዎች ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ከየመቃብሮቻችሁ ትወጣለችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَزْوَٰجَ كُلَّهَا وَجَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلْفُلْكِ وَٱلْأَنْعَٰمِ مَا تَرْكَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy12. ያም የፍጡር ዓይነቶችን ሁሉ (ጥንድ) አድርጎ የፈጠረ ለእናንተም ከመርከቦችና ከቤት እንሰሳዎች መካከል የምትጋልቧቸውን ያደረገላችሁ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِتَسْتَوُۥا۟ عَلَىٰ ظُهُورِهِۦ ثُمَّ تَذْكُرُوا۟ نِعْمَةَ رَبِّكُمْ إِذَا ٱسْتَوَيْتُمْ عَلَيْهِ وَتَقُولُوا۟ سُبْحَٰنَ ٱلَّذِى سَخَّرَ لَنَا هَٰذَا وَمَا كُنَّا لَهُۥ مُقْرِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy13. በጀርባዎቻቸው ላይ እንድትደላደሉ ከዚያም በእርሱ ላይ በተደላደላችሁ ጊዜ የጌታችሁን ጸጋ እንድታስታውሱ፤ እንድትሉም «ይህንን የማንችለው ስንሆን ለእኛ ያገራልን ጌታ ጥራት ተገባው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا لَمُنقَلِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን አላህ ተመላሾች ነን» እንድትሉ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلُوا۟ لَهُۥ مِنْ عِبَادِهِۦ جُزْءًا إِنَّ ٱلْإِنسَٰنَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy15. ከባሮቹም መካከል ለእርሱ ክፋይን (የተወሰነን) ብቻ አደረጉለት:: ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمِ ٱتَّخَذَ مِمَّا يَخْلُقُ بَنَاتٍ وَأَصْفَىٰكُم بِٱلْبَنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy16. አላህ ከሚፈጥረው ፍጡር መካከል ሴቶች ልጆችን ብቻ ለይቶ የራሱ ልጅ አድርጎ ያዘን? (ከዚያም) እናንተን በወንዶች ልጆች መረጣችሁን? (አይደለም)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِمَا ضَرَبَ لِلرَّحْمَٰنِ مَثَلًا ظَلَّ وَجْهُهُۥ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy17. አንዳቸዉም ለአር-ረህማን ምሳሌ ባደረገው ነገር (በሴት ልጅ) በተበሰረ ጊዜ በቁጭት የተሞላ ሆኖ ፊቱ ጥቁር ይሆናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَمَن يُنَشَّؤُا۟ فِى ٱلْحِلْيَةِ وَهُوَ فِى ٱلْخِصَامِ غَيْرُ مُبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy18. በጌጣጌጥ ተከልሶ እንዲያድግ የሚደረገውን ክፍል እርሱም ከደካማነቱ የተነሳ በክርክር የማያብራራውን ፍጡር ለይተው ለአላህ ያደርጋሉን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلُوا۟ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ ٱلَّذِينَ هُمْ عِبَٰدُ ٱلرَّحْمَٰنِ إِنَٰثًا أَشَهِدُوا۟ خَلْقَهُمْ سَتُكْتَبُ شَهَٰدَتُهُمْ وَيُسْـَٔلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. እነዚያን የአር-ረሕማን ቅን ባሮች የሆኑትን መላእክትንም ሴቶች አደረጓቸው። ለመሆኑ እነርሱ መላእክት ሲፈጠሩ አብረው ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትፃፋለች:: ስለ እርሷም ይጠየቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوا۟ لَوْ شَآءَ ٱلرَّحْمَٰنُ مَا عَبَدْنَٰهُم مَّا لَهُم بِذَٰلِكَ مِنْ عِلْمٍ إِنْ هُمْ إِلَّا يَخْرُصُونَ

Amharic Translation - Africa Academy20. «አር-ረሕማንም በፈለገ ኖሮ ባልተገዛናቸው ነበር» አሉ። ለእነርሱም በዚህ ምንም እውቀት የላቸዉም፤ እነርሱ የሚዋሹ ህዝቦች እንጂ ሌላ አይደሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ ءَاتَيْنَٰهُمْ كِتَٰبًا مِّن قَبْلِهِۦ فَهُم بِهِۦ مُسْتَمْسِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. ከእርሱ (ቁርኣን) በፊት መጽሐፍን ሰጠናቸውና እሱን አጥብቀው የያዙ ናቸውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ قَالُوٓا۟ إِنَّا وَجَدْنَآ ءَابَآءَنَا عَلَىٰٓ أُمَّةٍ وَإِنَّا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُّهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy22. ከቶውንም «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘናቸው:: እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተመሪዎች ነን» አሉ እንጂ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ مَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ فِى قَرْيَةٍ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتْرَفُوهَآ إِنَّا وَجَدْنَآ ءَابَآءَنَا عَلَىٰٓ أُمَّةٍ وَإِنَّا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُّقْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነገሩ ልክ እንደዚህ ነው:: ከበፊትም በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስፈራሪን አላክንም ቅምጥሎቿ «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘን:: እኛም ፈለጎቻቸውን ተከታዩች ነን» ያሉ ቢሆኑ እንጂ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَٰلَ أَوَلَوْ جِئْتُكُم بِأَهْدَىٰ مِمَّا وَجَدتُّمْ عَلَيْهِ ءَابَآءَكُمْ قَالُوٓا۟ إِنَّا بِمَآ أُرْسِلْتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy24. አስፈራሪው «አባቶቻችሁን በእርሱ ላይ ካገኛችሁበት ይበልጥ ቀጥተኛው ሃይማኖት ባመጣላችሁም?» ቢላቸው «እኛ በተላካችሁበት ነገር (ሀይማኖት) ከሓዲያን ነን» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱنتَقَمْنَا مِنْهُمْ فَٱنظُرْ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُكَذِّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy25. ከእነርሱም ተበቀልን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተባባዮች መጨረሻ እንዴት እንደነበር ተመልከት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ قَالَ إِبْرَٰهِيمُ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦٓ إِنَّنِى بَرَآءٌ مِّمَّا تَعْبُدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂምም ለአባቱና ለህዝቦቹ «እኔ ከምትገዙት ጣኦታት ሁሉ ንጹህ ነኝ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا ٱلَّذِى فَطَرَنِى فَإِنَّهُۥ سَيَهْدِينِ

Amharic Translation - Africa Academy27. «ከዚያ ከፈጠረኝ በስተቀር ማንንም አልገዛም:: አላህንማ በእርግጥ ይመራኛልና ብቻውን አመልከዋለሁ» ባለ ጊዜ የነበረውን አስታውስ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلَهَا كَلِمَةًۢ بَاقِيَةً فِى عَقِبِهِۦ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy28. በዝርዮቹም ውስጥ ወደ አላህ ይመለሱ ዘንድ (በአንድ አምላክ) ማመንን ቀሪ ቃል አደረጋት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ مَتَّعْتُ هَٰٓؤُلَآءِ وَءَابَآءَهُمْ حَتَّىٰ جَآءَهُمُ ٱلْحَقُّ وَرَسُولٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁን እነዚህን ቁረይሾችንም አባቶቻቸውንም ቁርኣንንና ገላጭ መልዕክተኛ እስካመጣላቸው ድረስ አጣቀምኳቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا جَآءَهُمُ ٱلْحَقُّ قَالُوا۟ هَٰذَا سِحْرٌ وَإِنَّا بِهِۦ كَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy30. እውነት በመጣላቸው ጊዜም «ይህ ያመጣሀው ድግምት ነው። እኛም በእርሱ ከሓዲያን ነን።» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوا۟ لَوْلَا نُزِّلَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ عَلَىٰ رَجُلٍ مِّنَ ٱلْقَرْيَتَيْنِ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy31. ይህም «ቁርኣን በሁለቱ ከተሞች በአንዱ በሚኖር ታላቅ ሰው ላይ አይወርድም ኖሯልን?» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَهُمْ يَقْسِمُونَ رَحْمَتَ رَبِّكَ نَحْنُ قَسَمْنَا بَيْنَهُم مَّعِيشَتَهُمْ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَرَفَعْنَا بَعْضَهُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَٰتٍ لِّيَتَّخِذَ بَعْضُهُم بَعْضًا سُخْرِيًّا وَرَحْمَتُ رَبِّكَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ የጌታህን ስጦታ ያከፋፍላሉን? እኛ በቅርቢቱ ሕይወት እንኳን ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል:: ከፊላቸዉም ከፊሉን አገልጋይ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ (በሀብት) አበለጥን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህም ጸጋ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْلَآ أَن يَكُونَ ٱلنَّاسُ أُمَّةً وَٰحِدَةً لَّجَعَلْنَا لِمَن يَكْفُرُ بِٱلرَّحْمَٰنِ لِبُيُوتِهِمْ سُقُفًا مِّن فِضَّةٍ وَمَعَارِجَ عَلَيْهَا يَظْهَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy33. ሰዎችም (በክህደት) ላይ አንድ ህዝብ የሚሆኑ ባልነበሩ ኖሮ በአል-ረህማን ለሚክዱ ሰዎች ሁሉ (በዚህች ዓለም) ለቤቶቻቸው የብር ጣራዎች፤ የሚወጣጡባቸውም የብር መሰላሎች፤ ባደረግንላቸው ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِبُيُوتِهِمْ أَبْوَٰبًا وَسُرُرًا عَلَيْهَا يَتَّكِـُٔونَ

Amharic Translation - Africa Academy34. ለቤቶቻቸው የብር በሮች፤ ለሚደገፉባቸዉም የብር አልጋዎች፤(ባደረግንላቸው ነበር)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَزُخْرُفًا وَإِن كُلُّ ذَٰلِكَ لَمَّا مَتَٰعُ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةُ عِندَ رَبِّكَ لِلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy35. የወርቅ ጌጥንም ባደረግንላቸው ነበር። ይህም ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጣቀሚያ እንጂ ሌላ አይደለም:: ጠፊ ነው:: መጨረሻይቱም አገር በጌታህ ዘንድ ለጥንቁቆች ብቻ ናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَعْشُ عَن ذِكْرِ ٱلرَّحْمَٰنِ نُقَيِّضْ لَهُۥ شَيْطَٰنًا فَهُوَ لَهُۥ قَرِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy36. (በቁርኣን ከተወሳው) ከአል-ረሕማን ግሳጼ የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን። ስለዚህ እርሱ ለእርሱ የሁልግዜ ቁራኛው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّهُمْ لَيَصُدُّونَهُمْ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُم مُّهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy37. እነርሱም (ተደናባሪዎቹ) ሁሉ ወደ ትክክለኛው መንገድ ተመሪዎች መሆናቸውን የሚያስቡ ሲሆኑ እነርሱ (ሰይጣናት) ከቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ያግዷቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَنَا قَالَ يَٰلَيْتَ بَيْنِى وَبَيْنَكَ بُعْدَ ٱلْمَشْرِقَيْنِ فَبِئْسَ ٱلْقَرِينُ

Amharic Translation - Africa Academy38. (በትንሳኤ) ወደ እኛ በመጣ ጊዜ «(ቁራኛዬ ሆይ) በእኔና ባንተ መካከል የምስራቅና የምዕራብ ርቀት በኖረ ዋ ምኞቴ! ምን የከፋ ቁራኛ ነህ።» ይላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَن يَنفَعَكُمُ ٱلْيَوْمَ إِذ ظَّلَمْتُمْ أَنَّكُمْ فِى ٱلْعَذَابِ مُشْتَرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy39. (ከሓዲያን ሆይ!) ስለ በደላችሁም ዛሬ እናንተ በቅጣት ተጋሪዎች መሆናችሁ አይጠቅማችሁም (ይባላሉ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَأَنتَ تُسْمِعُ ٱلصُّمَّ أَوْ تَهْدِى ٱلْعُمْىَ وَمَن كَانَ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ደንቆሮዎችን ታሰማለህን? ወይስ እውሮችንና በግልጽ ጥመት ውስጥ የሆኑ ሰዎችን ትመራለህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِمَّا نَذْهَبَنَّ بِكَ فَإِنَّا مِنْهُم مُّنتَقِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ቅጣታቸውን ሳታይ ብንወስድህ እኛ ከእነርሱ ተበቃዮች ነን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ نُرِيَنَّكَ ٱلَّذِى وَعَدْنَٰهُمْ فَإِنَّا عَلَيْهِم مُّقْتَدِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy42. ወይም ያንን የቀጠርናቸውን ብናሳይህ እኛ በእነርሱ ቅጣት ላይ ቻይዎች ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱسْتَمْسِكْ بِٱلَّذِىٓ أُوحِىَ إِلَيْكَ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ:: አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّهُۥ لَذِكْرٌ لَّكَ وَلِقَوْمِكَ وَسَوْفَ تُسْـَٔلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ (ቁርኣን) ላንተም ሆነ ለህዝቦችህ ታላቅ ክብር ነው:: ወደፊተም ከርሱ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَسْـَٔلْ مَنْ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رُّسُلِنَآ أَجَعَلْنَا مِن دُونِ ٱلرَّحْمَٰنِ ءَالِهَةً يُعْبَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞችም ካንተ በፊት የላክናቸው ከአር-ረሕማን ሌላ የሚገዙዋቸው የሆነን አማልክት አድርገን እንደሆነ (ተከታዮቻቸውን) ጠይቃቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦ فَقَالَ إِنِّى رَسُولُ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም በተዓምራታችን ወደ ፈርዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን:: «እኔ የዓለማቱ ጌታ መልዕክተኛ ነኝ» አላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَآءَهُم بِـَٔايَٰتِنَآ إِذَا هُم مِّنْهَا يَضْحَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy47. በተዓምራታችን በመጣላቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ በእርሷ ይስቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا نُرِيهِم مِّنْ ءَايَةٍ إِلَّا هِىَ أَكْبَرُ مِنْ أُخْتِهَا وَأَخَذْنَٰهُم بِٱلْعَذَابِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. ከተዓምራት አንዲትንም እናሳያቸዉም እርሷ ከብጤዋ በጣም የበለጠች ብትሆን እንጅ። ከክህደታቸው ይመለሱም ዘንድ በቅጣት ያዝናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوا۟ يَٰٓأَيُّهَ ٱلسَّاحِرُ ٱدْعُ لَنَا رَبَّكَ بِمَا عَهِدَ عِندَكَ إِنَّنَا لَمُهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy49. አንተ ድግምተኛ ሆይ! «ጌታህን አንተ ዘንድ ቃል በገባልህ ለእኛ ለምንልን እኛ (ቅጣቱን ቢያነሳልን) ተመሪዎች ነን» አሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا كَشَفْنَا عَنْهُمُ ٱلْعَذَابَ إِذَا هُمْ يَنكُثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy50. ስቃዩን ከእነርሱ ላይ በገለጥንም ጊዜ ወዲያውኑ ቃልኪዳናቸውን ያፈርሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَادَىٰ فِرْعَوْنُ فِى قَوْمِهِۦ قَالَ يَٰقَوْمِ أَلَيْسَ لِى مُلْكُ مِصْرَ وَهَٰذِهِ ٱلْأَنْهَٰرُ تَجْرِى مِن تَحْتِىٓ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy51. ፈርዖንም በህዝቦቹ ውስጥ ተጣራ። (እንዲህ) አለም: «ህዝቦቼ ሆይ! የሚስር (ግብጽ) ግዛት የእኔ አይደለምን? እነዚህም ጅረቶች ከስሬ የሚፈሱ ሲሆኑ የእኔ አይደሉምን? አትመለከቱምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ أَنَا۠ خَيْرٌ مِّنْ هَٰذَا ٱلَّذِى هُوَ مَهِينٌ وَلَا يَكَادُ يُبِينُ

Amharic Translation - Africa Academy52. «በእውነት እኔ ከዚያ ያ እርሱ ወራዳ ጉዳዩንም በደንብ ሊገልጽ የማይችል ከሆነው ሰው በላጭ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَوْلَآ أُلْقِىَ عَلَيْهِ أَسْوِرَةٌ مِّن ذَهَبٍ أَوْ جَآءَ مَعَهُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ مُقْتَرِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy53. «እርሱ ላይ የወርቅ አንባሮች ለምን አልተጣሉበትም? ወይም መላዕክት ከእርሱ ጋር ተቆራኝተው ለምን አልመጡም?» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱسْتَخَفَّ قَوْمَهُۥ فَأَطَاعُوهُ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمًا فَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy54. ህዝቦቹንም አቄላቸው:: ታዘዙትም:: እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّآ ءَاسَفُونَا ٱنتَقَمْنَا مِنْهُمْ فَأَغْرَقْنَٰهُمْ أَجْمَعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy55. ባስቆጡንም ጊዜ ከእነርሱ ተበቀልን:: ሁሉንም አሰመጥናቸውም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَجَعَلْنَٰهُمْ سَلَفًا وَمَثَلًا لِّلْـَٔاخِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy56. በጥፋት ቀዳሚዎችና ለኋለኞች መቀጣጫ ምሳሌም አደረግናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا ضُرِبَ ٱبْنُ مَرْيَمَ مَثَلًا إِذَا قَوْمُكَ مِنْهُ يَصِدُّونَ

Amharic Translation - Africa Academy57. የመርየም ልጅ ዒሳ ምሳሌ በተደረገ ጊዜ ህዝቦችህ (ከሀዲያኑ) ወዲያውኑ ከእርሱ ሌሎችን ያግዳሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوٓا۟ ءَأَٰلِهَتُنَا خَيْرٌ أَمْ هُوَ مَا ضَرَبُوهُ لَكَ إِلَّا جَدَلًۢا بَلْ هُمْ قَوْمٌ خَصِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy58. «አማልክቶቻችን ይበልጣሉን? ወይስ እርሱ ይበልጣል?» አሉም:: ለክርክር እንጅ ላንተ (እርሱን) ምሳሌ አላደረጉትም:: በእውነት እነርሱ ክርክረ ብርቱ ህዝቦች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَٰهُ مَثَلًا لِّبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy59. እርሱ (ዒሳ) በእርሱ ላይ የለገስንለት ለኢስራኢል ልጆችም ተዐምር ያደረግነው አገልጋይ ባሪያችን እንጂ ሌላ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ نَشَآءُ لَجَعَلْنَا مِنكُم مَّلَٰٓئِكَةً فِى ٱلْأَرْضِ يَخْلُفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy60. ብንፈልግም ኖሮ በምድር ላይ በእናንተ ምትክ መላዕክትን ባደረግን ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّهُۥ لَعِلْمٌ لِّلسَّاعَةِ فَلَا تَمْتَرُنَّ بِهَا وَٱتَّبِعُونِ هَٰذَا صِرَٰطٌ مُّسْتَقِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱም (ዒሳ) ለስዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው:: በእርሷም አትጠራጠሩ:: ተከተሉኝም:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يَصُدَّنَّكُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ إِنَّهُۥ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy62. ሰይጣንም አያግዳችሁ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمَّا جَآءَ عِيسَىٰ بِٱلْبَيِّنَٰتِ قَالَ قَدْ جِئْتُكُم بِٱلْحِكْمَةِ وَلِأُبَيِّنَ لَكُم بَعْضَ ٱلَّذِى تَخْتَلِفُونَ فِيهِ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy63. ዒሳ ግልፅ ተዓምራታችንን ይዞ በመጣ ጊዜ «በእርግጥ በጥበብ መጣሁላችሁ:: የዚያንም የምትለያዩበትን ጉዳይ ከፊሉን ለእናንተ ላብራራላችሁ መጣሁ:: እናም አላህን ፍሩ:: ታዘዙኝም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ هَٰذَا صِرَٰطٌ مُّسْتَقِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy64. «አላህ ጌታዬ ጌታችሁም ነውና በብቸኝነት ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው::» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱخْتَلَفَ ٱلْأَحْزَابُ مِنۢ بَيْنِهِمْ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْ عَذَابِ يَوْمٍ أَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy65. ከመካከላቸዉም አህዛቦቹ ተለያዩ:: ለእነዚያም ለበደሉት ህዝቦች ከአሳማሚ ቀን ቅጣት ወዮላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا ٱلسَّاعَةَ أَن تَأْتِيَهُم بَغْتَةً وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy66. ሰዓቲቱን እነርሱ የማያውቁ ሆነው በድንገት ልትመጣባቸው እንጂ (ሌላ) ይጠባበቃሉን?::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلْأَخِلَّآءُ يَوْمَئِذٍۭ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy67. አላህን የሚፈሩ ሰዎች ብቻ ሲቀሩ ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰعِبَادِ لَا خَوْفٌ عَلَيْكُمُ ٱلْيَوْمَ وَلَآ أَنتُمْ تَحْزَنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy68. (አላህም ለነርሱ) «ባሮቼ ሆይ! ዛሬ ቀን በእናንተ ላይ ምንም ፍርሀት የለባችሁም:: እናንተም የምታዝኑ አይደላችሁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُوا۟ مُسْلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy69. «እነዚያ በአናቅጻችን ያመኑና ፍጹም ታዛዦች የነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱدْخُلُوا۟ ٱلْجَنَّةَ أَنتُمْ وَأَزْوَٰجُكُمْ تُحْبَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. (ባሮቼ ሆይ!) « እናንተም ሚስቶቻችሁም ገነትን ግቡ ትደሰታላችሁ (ትከበራላችሁ)።» ይባላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُطَافُ عَلَيْهِم بِصِحَافٍ مِّن ذَهَبٍ وَأَكْوَابٍ وَفِيهَا مَا تَشْتَهِيهِ ٱلْأَنفُسُ وَتَلَذُّ ٱلْأَعْيُنُ وَأَنتُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy71. ከወርቅ የሆኑ ሰፋፊ ዝርግ ሳህኖችና ኩባያዎች በእነርሱ ላይ እንዲዞሩ ይደረጋሉ። በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት ዓይኖችም የሚደስቱበት ሁሉ አለ:: እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتِلْكَ ٱلْجَنَّةُ ٱلَّتِىٓ أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy72. ይህም ያ ስትሰሩት በነበራችሁት ዋጋ የተሰጣችኋት ገነት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَكُمْ فِيهَا فَٰكِهَةٌ كَثِيرَةٌ مِّنْهَا تَأْكُلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy73. ለእናንተ በውስጧ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁና ከእርሷም እንደልባችሁ ትበላላችሁ ይባላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْمُجْرِمِينَ فِى عَذَابِ جَهَنَّمَ خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy74. አመጸኞች በገሀነም ስቃይ ውስጥ በእርግጥ ዘወታሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يُفَتَّرُ عَنْهُمْ وَهُمْ فِيهِ مُبْلِسُونَ

Amharic Translation - Africa Academy75. ከእነርሱም ቅጣት በፍጹም አይቀለልላቸዉም:: እነርሱም በእርሱ ውስጥ ተስፋ ቆራጮች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا ظَلَمْنَٰهُمْ وَلَٰكِن كَانُوا۟ هُمُ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy76. አልበደልናቸዉም:: በዳዮቹ ግን እነርሱው ብቻ ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَادَوْا۟ يَٰمَٰلِكُ لِيَقْضِ عَلَيْنَا رَبُّكَ قَالَ إِنَّكُم مَّٰكِثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy77. «ማሊክ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ (በሞት) ይፍረድ።» እያሉ ይጣራሉም:: ይላቸዋልም: «እናንተ (በቅጣት ውስጥ) ለዘላለም ነዋሪዎች ናችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ جِئْنَٰكُم بِٱلْحَقِّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَكُمْ لِلْحَقِّ كَٰرِهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy78. «እውነተኛውን መንገድ በእርግጥ አመጣንላችሁ:: ግን አብዛኞቻችሁ እውነትን ጠይዎች ነበራችሁ» ይባላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ أَبْرَمُوٓا۟ أَمْرًا فَإِنَّا مُبْرِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy79. ይልቁንም (በነብዩ ላይ) በማደም ነገርን አጠነከሩን? እኛም ተንኮላቸውን ወደ እነርሱ በመመለስ አጠንካሪዎች ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ يَحْسَبُونَ أَنَّا لَا نَسْمَعُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَىٰهُم بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيْهِمْ يَكْتُبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy80. ወይም እኛ ሚስጥራቸውንና ውይይታቸውን የማንሰማ መሆናችንን ያስባሉን? ነገሩ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም:: መልዕክተኞቻችን እነርሱ ዘንድ ናቸው:: የሚሉትን ሁሉ ይጽፋሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ إِن كَانَ لِلرَّحْمَٰنِ وَلَدٌ فَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْعَٰبِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለአር-ረሕማን ልጅ (የለዉም እንጂ) ቢኖረው እኔ ለልጁ የተገዢዎች መጀመሪያ ነኝ» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سُبْحَٰنَ رَبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ رَبِّ ٱلْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy82. የሰማያት፤ የምድርና የዙፋኑ ጌታ ከሓዲያን ስለ እሱ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَذَرْهُمْ يَخُوضُوا۟ وَيَلْعَبُوا۟ حَتَّىٰ يُلَٰقُوا۟ يَوْمَهُمُ ٱلَّذِى يُوعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን ይስፈራሩበት የነበሩትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ በስህተታቸው ውስጥ ይዋኙ ተዋቸው :: ይጫዎቱም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى فِى ٱلسَّمَآءِ إِلَٰهٌ وَفِى ٱلْأَرْضِ إِلَٰهٌ وَهُوَ ٱلْحَكِيمُ ٱلْعَلِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy84. እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባው በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባው ብቸኛ አምላክ ነው:: እርሱም ጥበበኛውና ሁሉን አዋቂው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَبَارَكَ ٱلَّذِى لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَعِندَهُۥ عِلْمُ ٱلسَّاعَةِ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy85. ያም የሰማያት፤ የምድርና በመካከላቸው ያለው ሁሉ ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነው አምላክ ላቀ:: የሰዓቲቱም የመምጫዋ ዘመን ዕውቀት በእርሱ ዘንድ ብቻ ነው:: ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يَمْلِكُ ٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِهِ ٱلشَّفَٰعَةَ إِلَّا مَن شَهِدَ بِٱلْحَقِّ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy86. እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸው አማልክት ሁሉ እነርሱ ትክክለኛውን የሚያውቁ ሆነው በእውነት ከመሰከሩት ክፍሎች በስተቀር ምልጃ አይችሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَهُمْ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ فَأَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማን እንደ ፈጠራቸው ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ:: ታዲያ (ከትክክለኛው እምነት) ወዴት ይዞራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقِيلِهِۦ يَٰرَبِّ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ قَوْمٌ لَّا يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy88. (ነብዩ) ጌታዬ ሆይ! እነዚህ የማያምኑ ህዝቦች ናቸው የማለቱም እውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱصْفَحْ عَنْهُمْ وَقُلْ سَلَٰمٌ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: «ነገሬ ስላም ነው» በልም:: ወደፊትም የሚመጣባቸውን ሲደርስ ያውቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70