ሱረቱ Az-Zumar الزمر
75 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 59
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ تَنزِيلُ ٱلْكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَكِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy1. የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّآ أَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ فَٱعْبُدِ ٱللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ ٱلدِّينَ
Amharic Translation - Africa Academy2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት የተሞላ ሲሆን አወረድነው:: አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَا لِلَّهِ ٱلدِّينُ ٱلْخَالِصُ وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءَ مَا نَعْبُدُهُمْ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلْفَىٰٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ فِى مَا هُمْ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى مَنْ هُوَ كَٰذِبٌ كَفَّارٌ
Amharic Translation - Africa Academy3. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት ለአላህ ብቻ ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት ሁሉ «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን በማሰብ እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።» ይላሉ:: አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታምንና ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّوْ أَرَادَ ٱللَّهُ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا لَّٱصْطَفَىٰ مِمَّا يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ سُبْحَٰنَهُۥ هُوَ ٱللَّهُ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّارُ
Amharic Translation - Africa Academy4. አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር:: ጥራት ተገባው:: እርሱ አሸናፊውና ብቸኛው አንዱ አላህ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بِٱلْحَقِّ يُكَوِّرُ ٱلَّيْلَ عَلَى ٱلنَّهَارِ وَيُكَوِّرُ ٱلنَّهَارَ عَلَى ٱلَّيْلِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ كُلٌّ يَجْرِى لِأَجَلٍ مُّسَمًّى أَلَا هُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفَّٰرُ
Amharic Translation - Africa Academy5. አላህ ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ሌሊቱንም በቀን ላይ ይጠቀልላል:: ቀኑንም በሌሊት ላይ እንዲሁ ይጠቀልላል:: ጸሐይንና ጨረቃንም ገራ:: ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እርሱ አሸናፊዉና መሀሪው ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَٰحِدَةٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ ٱلْأَنْعَٰمِ ثَمَٰنِيَةَ أَزْوَٰجٍ يَخْلُقُكُمْ فِى بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمْ خَلْقًا مِّنۢ بَعْدِ خَلْقٍ فِى ظُلُمَٰتٍ ثَلَٰثٍ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ ٱلْمُلْكُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy6. (ሰዎች ሆይ!) ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ:: ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን ፈጠረ:: ለእናንተም ከግመልና ከዳልጋ ከብት፤ ከፍየልና ከበግ ስምንት አይነቶችን (ጥንዶችን) አወረደ:: በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ በሶስት ጨለማዎች ውስጥ ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል፤ ይህን ያደረገው ጌታችሁ አላህ ነው:: ስልጣኑም የእርሱ ብቻ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِن تَكْفُرُوا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِىٌّ عَنكُمْ وَلَا يَرْضَىٰ لِعِبَادِهِ ٱلْكُفْرَ وَإِن تَشْكُرُوا۟ يَرْضَهُ لَكُمْ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُم مَّرْجِعُكُمْ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ إِنَّهُۥ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
Amharic Translation - Africa Academy7. በአላህ ብትክዱ አላህ ከናንተ የተብቃቃ ነው:: ለባሪያዎቹም ክህደትን አይወድም፤ ብታመሰግኑም እርሱን ይወድላችኋል:: ማንኛይቱም ኃጢአትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያም የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ብቻ ነው:: ትሰሩት የነበራችሁትንም ሁሉ ይነግራችኋል:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያሉትን ሁሉ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا مَسَّ ٱلْإِنسَٰنَ ضُرٌّ دَعَا رَبَّهُۥ مُنِيبًا إِلَيْهِ ثُمَّ إِذَا خَوَّلَهُۥ نِعْمَةً مِّنْهُ نَسِىَ مَا كَانَ يَدْعُوٓا۟ إِلَيْهِ مِن قَبْلُ وَجَعَلَ لِلَّهِ أَندَادًا لِّيُضِلَّ عَن سَبِيلِهِۦ قُلْ تَمَتَّعْ بِكُفْرِكَ قَلِيلًا إِنَّكَ مِنْ أَصْحَٰبِ ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy8. የሰውን ልጅ ጉዳት ባገኘው ጊዜ ወደ እርሱ ተመላሽ ሆኖ ጌታወን ይጠራል:: ከዚያም ከእርሱ ዘንድ ጸጋን በሰጠው ጊዜ ያንን ከዚያ በፊት ወደ እርሱ ይጸልይበት የነበረውን መከራ ይረሳል:: ከመንገዱ ለማሳሳትም ለአላህ ባላንጣዎችን ያደርጋል:: ለእንዲህ አይነቱ ሰው «በክህደት ጥቂትን ተጣቀም፤ አንተ በእርግጥ ከእሳት ጓዶች ነህ።» በለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمَّنْ هُوَ قَٰنِتٌ ءَانَآءَ ٱلَّيْلِ سَاجِدًا وَقَآئِمًا يَحْذَرُ ٱلْـَٔاخِرَةَ وَيَرْجُوا۟ رَحْمَةَ رَبِّهِۦ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَٱلَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ የመጨረሻይቱን ዓለም ቅጣት የሚፈራ የጌታውንም ችሮታ የሚከጅል ሲሆን በሌሊት ሰዓቶችም ሰጋጅና ቋሚ ሆኖ ለጌታው የሚገዛ ሰው (እንደ ተስፋ ቢሱ ከሓዲ ነውን? በለው።) «እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው:: የሚገሰፁት ባለ አእምሮዎች ብቻ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰعِبَادِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ رَبَّكُمْ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ فِى هَٰذِهِ ٱلدُّنْيَا حَسَنَةٌ وَأَرْضُ ٱللَّهِ وَٰسِعَةٌ إِنَّمَا يُوَفَّى ٱلصَّٰبِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ
Amharic Translation - Africa Academy10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ጌታችሁ) «እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ለነዚያ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው፡፡ የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው» (ይላል) በላቸው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ ٱللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ ٱلدِّينَ
Amharic Translation - Africa Academy11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል: «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ያጠራሁ ሆኜ እንድገዛው ታዘዝኩ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأُمِرْتُ لِأَنْ أَكُونَ أَوَّلَ ٱلْمُسْلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy12. «የሙስሊሞች መጀመሪያ እንድሆን ታዘዝኩ» በል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنِّىٓ أَخَافُ إِنْ عَصَيْتُ رَبِّى عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلِ ٱللَّهَ أَعْبُدُ مُخْلِصًا لَّهُۥ دِينِى
Amharic Translation - Africa Academy14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በል: «አላህን ሃይማኖቴን ለእርሱ ያጠራሁ ሆኜ እገዛዋለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱعْبُدُوا۟ مَا شِئْتُم مِّن دُونِهِۦ قُلْ إِنَّ ٱلْخَٰسِرِينَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ وَأَهْلِيهِمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ أَلَا ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْخُسْرَانُ ٱلْمُبِينُ
Amharic Translation - Africa Academy15. «ከእርሱ ሌላ የሻችሁትን ተገዙ:: ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሳኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ሰዎች ሆይ! አስተዉሉ:: ግልጽ ከሳራ ማለት ይህ ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَهُم مِّن فَوْقِهِمْ ظُلَلٌ مِّنَ ٱلنَّارِ وَمِن تَحْتِهِمْ ظُلَلٌ ذَٰلِكَ يُخَوِّفُ ٱللَّهُ بِهِۦ عِبَادَهُۥ يَٰعِبَادِ فَٱتَّقُونِ
Amharic Translation - Africa Academy16. ለእነርሱ ከበላያቸው ከእሳት የሆኑ ድርብርብ ጥላዎች አሏቸው:: ከስራቸዉም እንዲሁ:: ይህ አላህ ባሮቹን እንዲጠነቀቁ በእርሱ ያስፈራራበታል:: ባሮቼ ሆይ! ስለዚህ ፍሩኝ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ ٱجْتَنَبُوا۟ ٱلطَّٰغُوتَ أَن يَعْبُدُوهَا وَأَنَابُوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ لَهُمُ ٱلْبُشْرَىٰ فَبَشِّرْ عِبَادِ
Amharic Translation - Africa Academy17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም ጣዖታትን ከመገዛት የራቁ እና ወደ አላህ የዞሩ ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ብስራት አላቸው። ስለዚህ ባሮቼን አብስር፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَسْتَمِعُونَ ٱلْقَوْلَ فَيَتَّبِعُونَ أَحْسَنَهُۥٓ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ هَدَىٰهُمُ ٱللَّهُ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمْ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy18. እነዚያን ንግግርን የሚያዳምጡትንና መልካምን የሚከተሉትን (ባሮቼን አብስር)፤ እነዚያ አላህ ወደ ቀናው መንገድ የመራቸው ናቸው። እነዚያም እነርሱ ባለ አእምሮዎቹ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمَنْ حَقَّ عَلَيْهِ كَلِمَةُ ٱلْعَذَابِ أَفَأَنتَ تُنقِذُ مَن فِى ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy19. በእርሱ ላይ የቅጣት ቃል የተረጋገጠችበትን (ትመራዋለህን?) አንተ በእሳት ውስጥ ያለን ታድናለህን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَٰكِنِ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ رَبَّهُمْ لَهُمْ غُرَفٌ مِّن فَوْقِهَا غُرَفٌ مَّبْنِيَّةٌ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ وَعْدَ ٱللَّهِ لَا يُخْلِفُ ٱللَّهُ ٱلْمِيعَادَ
Amharic Translation - Africa Academy20. ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ፤ ለእነርሱም ከበላያቸው የታነጹ ሰገነቶች ያሏቸው ሰገነቶች ከስሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ አሏቸው:: (ይህንን) አላህ ቃል ገባላቸው፤ አላህም ቃሉን አያፈርስም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَسَلَكَهُۥ يَنَٰبِيعَ فِى ٱلْأَرْضِ ثُمَّ يُخْرِجُ بِهِۦ زَرْعًا مُّخْتَلِفًا أَلْوَٰنُهُۥ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَىٰهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَجْعَلُهُۥ حُطَٰمًا إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَذِكْرَىٰ لِأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን እንዳወረደና በምድር ውስጥ ምንጮች አድርጎ እንዳስገባው አላየህምን? ከዚያም በእርሱ ብዙ አይነቶች የሆኑ የተለያዩ አዝመራዎችን ያወጣበታል:: ከዚያም ይደርቃል:: ገርጥቶም ታየዋለህ:: ከዚያ ስብርብር ያደርገዋል፤ በዚህ ውስጥ ለባለ አእምሮዎች ግሳፄ አለበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمَن شَرَحَ ٱللَّهُ صَدْرَهُۥ لِلْإِسْلَٰمِ فَهُوَ عَلَىٰ نُورٍ مِّن رَّبِّهِۦ فَوَيْلٌ لِّلْقَٰسِيَةِ قُلُوبُهُم مِّن ذِكْرِ ٱللَّهِ أُو۟لَٰٓئِكَ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy22. አላህ ደረቱን ለእስልምና ያሰፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የሆነ ሰው (ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን?) ልቦቻቸዉም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወየውላቸው፤ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ نَزَّلَ أَحْسَنَ ٱلْحَدِيثِ كِتَٰبًا مُّتَشَٰبِهًا مَّثَانِىَ تَقْشَعِرُّ مِنْهُ جُلُودُ ٱلَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ ثُمَّ تَلِينُ جُلُودُهُمْ وَقُلُوبُهُمْ إِلَىٰ ذِكْرِ ٱللَّهِ ذَٰلِكَ هُدَى ٱللَّهِ يَهْدِى بِهِۦ مَن يَشَآءُ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنْ هَادٍ
Amharic Translation - Africa Academy23. አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን ተመሳሳይ ተደጋጋሚ የሆነን መጽሐፍ (ቁርኣንን) አወረደ:: ከእርሱ ግሳፄ የእነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ:: ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ ተስፋ ማስታወስ ይለዝባሉ:: ይህ የአላህ መምሪያ ነው፤ በእርሱ የሚሻዉን ሰው ይመራበታል። አላህም የሚያጠመውን ሰው ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَمَن يَتَّقِى بِوَجْهِهِۦ سُوٓءَ ٱلْعَذَابِ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَقِيلَ لِلظَّٰلِمِينَ ذُوقُوا۟ مَا كُنتُمْ تَكْسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy24. በትንሳኤ ቀን ክፉን ቅጣት በፊቱ የሚመክት ሰው (ከቅጣቱ እንደዳነው ነውን?) ለበዳዮችም «ትሰሩት የነበራችሁን ቅጣትን ቅመሱ» ይባላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَأَتَىٰهُمُ ٱلْعَذَابُ مِنْ حَيْثُ لَا يَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባበሉ:: ቅጣቱም ከማያውቁት በኩል መጣባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَذَاقَهُمُ ٱللَّهُ ٱلْخِزْىَ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَلَعَذَابُ ٱلْـَٔاخِرَةِ أَكْبَرُ لَوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy26. አላህም በቅርቢቱ ሕይወት ውርደትን አቀመሳቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም ትልቅ ነው:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ አያስተባብሉም ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ضَرَبْنَا لِلنَّاسِ فِى هَٰذَا ٱلْقُرْءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٍ لَّعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ከየምሳሌው ሁሉ በእርግጥ አብራራን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُرْءَانًا عَرَبِيًّا غَيْرَ ذِى عِوَجٍ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy28. መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን (አብራራነው):: ሊጠነቀቁ ይከጀላልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا رَّجُلًا فِيهِ شُرَكَآءُ مُتَشَٰكِسُونَ وَرَجُلًا سَلَمًا لِّرَجُلٍ هَلْ يَسْتَوِيَانِ مَثَلًا ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy29. አላህ በእርሱ ተጨቃጫቂዎች የሆኑ ተጋሪዎች ያሉትን ባሪያና ለአንድ ሰው ብቻ ንጹህ የሆነን ባሪያ ለሚያጋራና በአንድነት ለሚያምን ሰው ምሳሌ አደረገ። በምሳሌ ይስተካካላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّكَ مَيِّتٌ وَإِنَّهُم مَّيِّتُونَ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ إِنَّكُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ عِندَ رَبِّكُمْ تَخْتَصِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy31 ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ቀን እጌታችሁ ዘንድ ትከራከራላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن كَذَبَ عَلَى ٱللَّهِ وَكَذَّبَ بِٱلصِّدْقِ إِذْ جَآءَهُۥٓ أَلَيْسَ فِى جَهَنَّمَ مَثْوًى لِّلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy32. በአላህ ላይም ከዋሸ እውነቱንም በመጣለት ጊዜ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው? በገሀነም ውስጥ ለከሓዲያን መኖሪያ የለምን? (አለ እንጂ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِى جَآءَ بِٱلصِّدْقِ وَصَدَّقَ بِهِۦٓ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy33. ያም በእውነት የመጣውና በእርሱ ያመነዉም እነዚያ እነርሱ አላህን ፈሪዎቹ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَهُم مَّا يَشَآءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy34. ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሚሹት (የሚፈልጉት) ሁሉ አላቸው:: ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِيُكَفِّرَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ أَسْوَأَ ٱلَّذِى عَمِلُوا۟ وَيَجْزِيَهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ ٱلَّذِى كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. አላህ ያንን በስህተት የሰሩትን መጥፎ ስራ ከእነርሱ ሊሰርዝላቸውና በዚያም ይሰሩት በነበሩት መልካም ስራ ምንዳቸውን ሊመነዳቸው ይህንን አደረገ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَيْسَ ٱللَّهُ بِكَافٍ عَبْدَهُۥ وَيُخَوِّفُونَكَ بِٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنْ هَادٍ
Amharic Translation - Africa Academy36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነዚያ ከእርሱ ሌላ በሆኑትም ጣኦታት ያስፈራሩሀል፤ አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን? አላህ የሚያጠመውን ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن يَهْدِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن مُّضِلٍّ أَلَيْسَ ٱللَّهُ بِعَزِيزٍ ذِى ٱنتِقَامٍ
Amharic Translation - Africa Academy37. አላህ የሚያቀናውንም ለእርሱ ምንም አጥማሚ የለዉም:: አላህ አሸናፊውና የመበቀል ባለቤት አይደለምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ قُلْ أَفَرَءَيْتُم مَّا تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ إِنْ أَرَادَنِىَ ٱللَّهُ بِضُرٍّ هَلْ هُنَّ كَٰشِفَٰتُ ضُرِّهِۦٓ أَوْ أَرَادَنِى بِرَحْمَةٍ هَلْ هُنَّ مُمْسِكَٰتُ رَحْمَتِهِۦ قُلْ حَسْبِىَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ يَتَوَكَّلُ ٱلْمُتَوَكِّلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል:: «ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ጣዖታት አያችሁን? እስቲ ንገሩኝ:: አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈልገኝ እነርሱም ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?» በላቸው:: «አላህ በቂዬ ነው:: በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ» በል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰقَوْمِ ٱعْمَلُوا۟ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمْ إِنِّى عَٰمِلٌ فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸውም: «ህዝቦቼ ሆይ! ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሁናችሁ ስሩ:: እኔም ባለሁበት ሁኔታ ላይ ሁኜ ሰሪ ነኝና:: ወደ ፊትም ትክክለኛው የቱ እንደነበር ታውቃላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَن يَأْتِيهِ عَذَابٌ يُخْزِيهِ وَيَحِلُّ عَلَيْهِ عَذَابٌ مُّقِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy40. «ያንን የሚያሳፍረው ቅጣት የሚመጣበትንና በእርሱ ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን ማንነት ታውቃላቸሁ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّآ أَنزَلْنَا عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ لِلنَّاسِ بِٱلْحَقِّ فَمَنِ ٱهْتَدَىٰ فَلِنَفْسِهِۦ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا وَمَآ أَنتَ عَلَيْهِم بِوَكِيلٍ
Amharic Translation - Africa Academy41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መጽሐፉን ባንተ ላይ ለሰዎች ጥቅም በእውነት አወረድነው:: እናም በሱ የተመራ ሰው ሁሉ ፋይዳው ለነፍሱ ነው:: የጠመመም ሰው ጉዳቱ ለራሱ ነው የሚጠመው:: አንተም ታስገድዳቸው ዘንድ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አይደለህም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا فَيُمْسِكُ ٱلَّتِى قَضَىٰ عَلَيْهَا ٱلْمَوْتَ وَيُرْسِلُ ٱلْأُخْرَىٰٓ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy42. አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል:: ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ በእንቅልፈ ጊዜ ይወስዳታል:: ከዚያም ያችን ሞትን የፈረደባትን ነፍስ ይይዛታል:: ሌላይቱን ደግሞ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ይለቃታል:: በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተአምራት አሉበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمِ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ شُفَعَآءَ قُلْ أَوَلَوْ كَانُوا۟ لَا يَمْلِكُونَ شَيْـًٔا وَلَا يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም ቁረይሾች ከአላህ ሌላ አማላጆችን ያዙ። «እነርሱ ምንም የማይችሉና ምንም የማያውቁ ቢሆኑም ታመልኳቸዋላችሁን?» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُل لِّلَّهِ ٱلشَّفَٰعَةُ جَمِيعًا لَّهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy44. «ምልጃ ሁሉም የአላህ ብቻ ነው:: የሰማያትና የምድር ስልጣንም የእርሱ ብቻ ነው:: ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَحْدَهُ ٱشْمَأَزَّتْ قُلُوبُ ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱلْـَٔاخِرَةِ وَإِذَا ذُكِرَ ٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦٓ إِذَا هُمْ يَسْتَبْشِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy45. አላህ ብቻዉን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይሸማቀቃሉ (ይደነብራሉ) እነዚያ ከእርሱ ሌላ የሆኑት ጣዖታት በተወሱ ጊዜ ደግሞ እነርሱ ወዲያውኑ ይደሰታሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلِ ٱللَّهُمَّ فَاطِرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ عَٰلِمَ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ أَنتَ تَحْكُمُ بَيْنَ عِبَادِكَ فِى مَا كَانُوا۟ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን የፈጠርክ ሩቁንም ቅርቡንም አዋቂ የሆንከው አላህ ሆይ! አንተ በባሮችህ መካከል በዚያም ይለያዩበት በነበሩት ነገር ትፈርዳለህ» በል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مَا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا وَمِثْلَهُۥ مَعَهُۥ لَٱفْتَدَوْا۟ بِهِۦ مِن سُوٓءِ ٱلْعَذَابِ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَبَدَا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مَا لَمْ يَكُونُوا۟ يَحْتَسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy47. ለነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላዉም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሳኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተበዡበት ነበር:: ለእነርሱም ከአላህ ዘንድ ያስቡት ያልነበሩት ሁሉ ይገለጽላቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَبَدَا لَهُمْ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُوا۟ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ
Amharic Translation - Africa Academy48. ለእነርሱም የሰሯቸው መጥፎዎቹ ይገልጹላቸዋል:: በእነርሱም ላይ በእርሱ ያላግጡበት የነበሩት ቅጣት ይሰፍርባቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا مَسَّ ٱلْإِنسَٰنَ ضُرٌّ دَعَانَا ثُمَّ إِذَا خَوَّلْنَٰهُ نِعْمَةً مِّنَّا قَالَ إِنَّمَآ أُوتِيتُهُۥ عَلَىٰ عِلْمٍۭ بَلْ هِىَ فِتْنَةٌ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy49. ሰውም ጉዳት ባገኘው ጊዜ ይጠራናል:: ከዚያም ከእኛ የሆነውን ጸጋ በሰጠነው ጊዜ «እርሱን የተሰጠሁት በእውቀቴ ብቻ ነው።» ይላል:: ይልቁንም እርሷ (ጸጋይቱ) መፈተኛ ናት:: ግን አብዛሀኞቻቸው አያውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَدْ قَالَهَا ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَمَآ أَغْنَىٰ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy50. እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ህዝቦች ይችኑ ቃል በእርግጥ ብለዋታል:: ይሰሩት የነበሩትም ነገር ከእነርሱ አልጠቀማቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَصَابَهُمْ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُوا۟ وَٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْ هَٰٓؤُلَآءِ سَيُصِيبُهُمْ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُوا۟ وَمَا هُم بِمُعْجِزِينَ
Amharic Translation - Africa Academy51. የሰሯቸዉም መጥፎዎች ቅጣት አገኛቸው:: ከእነዚህም እነዚያ የበደሉት የሰሯቸውን መጥፎዎች ፍዳ በእርግጥ ይነካቸዋል:: እነርሱም አምላጮች አይደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَبْسُطُ ٱلرِّزْقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقْدِرُ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy52. አላህ ሲሳዩን ለሚሻው ሰው የሚያሰፋ፤ ለሚሻው ሰው የሚያጠብም መሆኑን አያውቁምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑት ህዝቦች ሁሉ አያሌ ግሳጼዎች አሉበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ أَسْرَفُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا۟ مِن رَّحْمَةِ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ يَغْفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِيعًا إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ:: አላህ ኃጢአቶችን ሁሉ ይምራልና:: እነሆ እርሱ መሀሪዉና አዛኙ ነውና።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنِيبُوٓا۟ إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا۟ لَهُۥ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ ٱلْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy54. (ሰዎች ሆይ!) ቅጣቱ ወደ እናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትረዱ ከመሆናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ (በመጸጸት) ተመለሱ:: ለእርሱም ታዘዙ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتَّبِعُوٓا۟ أَحْسَنَ مَآ أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ ٱلْعَذَابُ بَغْتَةً وَأَنتُمْ لَا تَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy55. እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን መልካሙን መጽሐፍ ተከተሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَن تَقُولَ نَفْسٌ يَٰحَسْرَتَىٰ عَلَىٰ مَا فَرَّطتُ فِى جَنۢبِ ٱللَّهِ وَإِن كُنتُ لَمِنَ ٱلسَّٰخِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy56. የካደች ነፍስ ሁሉ «እኔ ከሚሳለቁት የነበርኩ ስሆን በአላህ በኩል ባጓደልኩት ዋ! ጸጸቴ!» የምትል እንዳትሆን
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوْ تَقُولَ لَوْ أَنَّ ٱللَّهَ هَدَىٰنِى لَكُنتُ مِنَ ٱلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy57. ወይም «አላህ በመራኝ ኖሮ ከሚጠነቀቁት ሰዎች እሆን ነበር።» የምትል እንዳትሆን
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوْ تَقُولَ حِينَ تَرَى ٱلْعَذَابَ لَوْ أَنَّ لِى كَرَّةً فَأَكُونَ مِنَ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy58. ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ ወደ ምድረ አለም አንድ ጊዜ የመመለስ ዕድል በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎች በሆንኩ።» የምትል ከመሆኗ በፊት መልካሙን ተከተሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلَىٰ قَدْ جَآءَتْكَ ءَايَٰتِى فَكَذَّبْتَ بِهَا وَٱسْتَكْبَرْتَ وَكُنتَ مِنَ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy59. የለም ተመርተሃል:: አንቀፆቼ በእርግጥ መጥተውሃል:: በእነርሱም አስተባብለሃል፤ ኮርተሃልም:: ከከሓዲያንም ሆነሃል (ይባላል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ تَرَى ٱلَّذِينَ كَذَبُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ وُجُوهُهُم مُّسْوَدَّةٌ أَلَيْسَ فِى جَهَنَّمَ مَثْوًى لِّلْمُتَكَبِّرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በትንሳኤ ቀንም እነዚያን በአላህ ላይ የዋሹትን ፊቶቻቸው የጠቆሩ ሆነው ታያቸዋለህ:: በገሀነም ውስጥ ለትዕቢተኞች መኖሪያ የለምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيُنَجِّى ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ بِمَفَازَتِهِمْ لَا يَمَسُّهُمُ ٱلسُّوٓءُ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy61. እነዚያም የተጠነቀቁትን በማግኛቸው ስፍራ ሆነው አላህ ያድናቸዋል፤ ክፉ ነገር አይነካቸዉም:: እነርሱም አያዝኑም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ وَكِيلٌ
Amharic Translation - Africa Academy62. አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّهُۥ مَقَالِيدُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْخَٰسِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy63. የሰማያትና የምድር (ድልብ) መከፈቻዎች የእርሱ ብቻ ናቸው:: እነዚያም በአላህ አናቅጽ የካዱት እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَفَغَيْرَ ٱللَّهِ تَأْمُرُوٓنِّىٓ أَعْبُدُ أَيُّهَا ٱلْجَٰهِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ መሃይማን ሆይ! ከአላህ ሌላን እንድንገዛ ታዙኛላቸሁን?» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أُوحِىَ إِلَيْكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብታጋራ ስራህ በእርግጥ ይታበሳል:: በእርግጥም ከከሓዲያን ትሆናለህ በማለት ወደ አንተና እነዚያ ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሰዎች በእርግጥ ተወርዷል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلِ ٱللَّهَ فَٱعْبُدْ وَكُن مِّنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy66. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቅ አላህን ብቻ ተገዛም:: ከአመስጋኞችም ሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا قَدَرُوا۟ ٱللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِۦ وَٱلْأَرْضُ جَمِيعًا قَبْضَتُهُۥ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَٱلسَّمَٰوَٰتُ مَطْوِيَّٰتٌۢ بِيَمِينِهِۦ سُبْحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ
Amharic Translation - Africa Academy67. አላህንም በትንሳኤው ቀን ምድርን በመላ ጭብጡ ስትሆንና ሰማያትም በቀኝ እጁ የሚጠቀለሉ ሲሆኑ ከእርሱ ጋር ሌላን በማጋራታቸው ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም:: ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ። ላቀም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنُفِخَ فِى ٱلصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ إِلَّا مَن شَآءَ ٱللَّهُ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy68. በቀንዱም ይነፋል:: በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡርና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል:: ከዚያም በእርሱ ሌላ መነፋት ይነፋል:: ወዲያውኑም እነርሱ የሚሰራባቸውን የሚጠባበቁ ሆነው ቋሚዎች ይሆናሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَشْرَقَتِ ٱلْأَرْضُ بِنُورِ رَبِّهَا وَوُضِعَ ٱلْكِتَٰبُ وَجِا۟ىٓءَ بِٱلنَّبِيِّـۧنَ وَٱلشُّهَدَآءِ وَقُضِىَ بَيْنَهُم بِٱلْحَقِّ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy69. ምድርም በጌታዋ ብርሃን ታበራለች፤ መጽሐፉም ይቀርባል:: ነብያትና ምስክሮችም ይመጣሉ:: በመካከላቸዉም በእውነት ይፈረዳል:: እነርሱም አይበደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوُفِّيَتْ كُلُّ نَفْسٍ مَّا عَمِلَتْ وَهُوَ أَعْلَمُ بِمَا يَفْعَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy70. ነፍስም ሁሉ የሰራቸውን ስራ ትሞላለች (ትሰፍራለች):: እርሱም የሚሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا وَقَالَ لَهُمْ خَزَنَتُهَآ أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَتْلُونَ عَلَيْكُمْ ءَايَٰتِ رَبِّكُمْ وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَآءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا قَالُوا۟ بَلَىٰ وَلَٰكِنْ حَقَّتْ كَلِمَةُ ٱلْعَذَابِ عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy71. እነዚያ በአላህ የካዱትም የተከፋፈሉ ቡድኖች ሆነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፤ በመጧትም ጊዜ በሮቿ ይከፈታሉ:: ወደሷ በመጡም ጊዜ ዘበኞቿ «ከእናንተ የሆኑ የጌታችሁን አናቅጽ በእናንተ ላይ የሚያነቡላችሁ የዚህንም ቀን መገናኘት የሚያስጠነቅቋችሁ መልዕክተኞች አልመጧችሁምን ነበርን?» ይሏቸዋል፤ «የለም መጥተውልናል። ግን የቅጣቲቱ ቃል በከሓዲያን ላይ ተረጋገጠች።» (ይላሉ።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قِيلَ ٱدْخُلُوٓا۟ أَبْوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَا فَبِئْسَ مَثْوَى ٱلْمُتَكَبِّرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy72. «የገሀነምን በሮች በውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ ግቡ የትዕቢተኞችም መኖሪያ ምን ትከፋ!» ይባላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَسِيقَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ رَبَّهُمْ إِلَى ٱلْجَنَّةِ زُمَرًا حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا وَفُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا وَقَالَ لَهُمْ خَزَنَتُهَا سَلَٰمٌ عَلَيْكُمْ طِبْتُمْ فَٱدْخُلُوهَا خَٰلِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy73. እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ቡድኖች ሆነው ወደ ገነት ይነዳሉ:: በመጧትም ጊዜ ደጃፎቿ የተከፈቱ ሲሆኑ ዘበኞቿም ለእነርሱ «ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን ተዋባችሁ፤ ዘወታሪዎች ሆናችሁ ግቧት።» ይሏቸዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى صَدَقَنَا وَعْدَهُۥ وَأَوْرَثَنَا ٱلْأَرْضَ نَتَبَوَّأُ مِنَ ٱلْجَنَّةِ حَيْثُ نَشَآءُ فَنِعْمَ أَجْرُ ٱلْعَٰمِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy74. «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ለዚያ የተስፋ ቃሉን ለሞላልን፤ የገነትንም ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንሆን ላወረሰን ይገባው።» ይላሉ። የሰሪዎችም ምንዳ ምን ያምር!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَرَى ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ حَآفِّينَ مِنْ حَوْلِ ٱلْعَرْشِ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَقُضِىَ بَيْنَهُم بِٱلْحَقِّ وَقِيلَ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትንም በጌታቸው ምስጋና ቀላቅለው የሚያጠሩ ሲሆኑ በአርሹ ዙሪያ ከባቢዎች ሆነው ታያለህ፡፡ በመካከላቸውም እውነት ይፈረዳል። ይባላልም፤ «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→