caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Saad፣ አንቀጽ 24

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 38 · 38:24

قَالَ لَقَدْ ظَلَمَكَ بِسُؤَالِ نَعْجَتِكَ إِلَىٰ نِعَاجِهِۦ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلْخُلَطَآءِ لَيَبْغِى بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَقَلِيلٌ مَّا هُمْ وَظَنَّ دَاوُۥدُ أَنَّمَا فَتَنَّٰهُ فَٱسْتَغْفَرَ رَبَّهُۥ وَخَرَّ رَاكِعًا وَأَنَابَ

Amharic Translation - Africa Academy24. «ሴት በግህን ወደ በጎቹ ለመቀላቀል በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ። ከተጋሪዎች ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ:: እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት ብቻ ሲቀሩ፤ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው።» አለ:: ዳውድም የፈተንነው መሆኑን ወዲያዉኑ አወቀ:: ከጌታዉም ምህረትን ለመነና ሰጋጅ ሆኖም ወደቀ። በመጸጸትም ተመለሰ:: {1}
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ሴት በግህን ወደ በጎቹ (ለመቀላቀል) በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ፡፡ ከተጋሪዎችም ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው» አለ፡፡ ዳውድም የፈተንነው መኾኑን ዐወቀ፡፡ ጌታውንም ምሕረትን ለመነ፡፡ ሰጋጅ ኾኖ ወደቀም፡፡ በመጸጸት ተመለሰም፡፡{1}
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70