وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا رَّجُلَيْنِ أَحَدُهُمَآ أَبْكَمُ لَا يَقْدِرُ عَلَىٰ شَىْءٍ وَهُوَ كَلٌّ عَلَىٰ مَوْلَىٰهُ أَيْنَمَا يُوَجِّههُّ لَا يَأْتِ بِخَيْرٍ هَلْ يَسْتَوِى هُوَ وَمَن يَأْمُرُ بِٱلْعَدْلِ وَهُوَ عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy76. አላህ ሁለትን ወንዶች (ለከሓዲያንና ለአማኞች) ምሳሌ አደረገ:: አንደኛቸው በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው:: እርሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው:: ወደ የትም ቢያዞረው ደግ ነገር አያመጣም:: እርሱና ያ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሆኖ በማስተካከል (ፍትህ) የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን?
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህም ሁለትን ወንዶች (ለከሓዲና ለምእመን) ምሳሌ አደረገ፡፡ አንደኛቸው በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው፡፡ እርሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው፡፡ ወደ የትም ቢያዞረው በደግ ነገር አይመጣም፡፡ እርሱና ያ እርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ኾኖ በማስተካከል የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን?