وَقَالَ ٱلَّذِينَ أَشْرَكُوا۟ لَوْ شَآءَ ٱللَّهُ مَا عَبَدْنَا مِن دُونِهِۦ مِن شَىْءٍ نَّحْنُ وَلَآ ءَابَآؤُنَا وَلَا حَرَّمْنَا مِن دُونِهِۦ مِن شَىْءٍ كَذَٰلِكَ فَعَلَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَهَلْ عَلَى ٱلرُّسُلِ إِلَّا ٱلْبَلَٰغُ ٱلْمُبِينُ
Amharic Translation - Africa Academy35. እነዚያም ጣዖታትን በአላህ ያጋሩ ህዝቦች «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም ሆንን አባቶቻችን ምንንም ባልተገዛን ነበር:: ያለ እርሱም ትዕዛዝ ምንንም እርም ባላደረግን ነበር።» አሉ:: እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት ህዝቦች ልክ እንደዚሁ ሠሩ:: በመልዕክተኞቹም ላይ ግልጽ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸዉም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም (ጣዖታትን) ያጋሩት «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም አባቶቻችንም ምንንም ባልተገዛን ነበር፤ ያለእርሱም (ትእዛዝ) ምንንም እርም ባላደረግን ነበር አሉ፡፡» እነዚያም ከነሱ በፊት የነበሩት እነደዚሁ ሠሩ፡፡ በመልክተኞቹም ላይ ግልፅ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸውም፡፡