وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنۢ بُيُوتِكُمْ سَكَنًا وَجَعَلَ لَكُم مِّن جُلُودِ ٱلْأَنْعَٰمِ بُيُوتًا تَسْتَخِفُّونَهَا يَوْمَ ظَعْنِكُمْ وَيَوْمَ إِقَامَتِكُمْ وَمِنْ أَصْوَافِهَا وَأَوْبَارِهَا وَأَشْعَارِهَآ أَثَٰثًا وَمَتَٰعًا إِلَىٰ حِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy80. አላህም ከቤቶቻችሁ ለእናንተ መርጊያን (ማረፊያን) አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ):: ከእንስሳዎችም ቆዳዎችን በጉዟችሁ ቀንም ሆነ በመቀመጫችሁ ቀን የምታቀሏቸውን ቤቶች (ዳሶች) ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: ከበጓ ሱፎች፣ ከግመሏም ጠጉሮች፣ ከፍየሏም ጠጉሮች የቤት እቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን አደረገላችሁ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህም ከቤቶቻችሁ ለእናንተ መርጊያን አደረገላችሁ፡፡ ከእንስሳዎችም ቆዳዎች በጉዟችሁ ቀን በመቀመጫችሁም ቀን የምታቀልላቸውን ቤቶች ለናንተ አደረገላችሁ፡፡ ከበግዋ ሱፎች፣ ከግመልዋም ጠጉሮች፣ ከፍየልዋም ጠጉሮች የቤት ዕቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን (አደረገላችሁ)፡፡