caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nahl፣ አንቀጽ 30

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 70 · 16:30

وَقِيلَ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ مَاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمْ قَالُوا۟ خَيْرًا لِّلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ فِى هَٰذِهِ ٱلدُّنْيَا حَسَنَةٌ وَلَدَارُ ٱلْـَٔاخِرَةِ خَيْرٌ وَلَنِعْمَ دَارُ ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy30. ለእነዚያም ለተጠነቀቁት ሰዎች «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ?» ተባሉ:: «መልካምን ነገር አወረደ» አሉ:: ለእነዚያ ደግ ለሠሩት ህዝቦች ሁሉ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አለላቸው:: የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት:: የጥንቁቆቹም አገር ገነት ምን ታምር!
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእነዚያም ለተጠነቀቁት «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ» ተባሉ፡፡ «መልካምን ነገር» አሉ፡፡ ለእነዚያ ደግ ለሠሩት በዚሀች በቅርቢቱ ዓለም መልካም (ኑሮ) አላቸው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ የጥንቁቆቹም አገር ምን ታምር!
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70