ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy125. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ በለዘብተኛ ቃልም ሰዎችን ጥራ:: በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው ዘዴ ተከራከራቸው:: ጌታህ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው:: እንደዚሁም እርሱ ቅን የሆኑትን ሰዎች አዋቂ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡