caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ash-Shams الشمس

15 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 26

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَٱلشَّمْسِ وَضُحَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy1. በጸሐይና በብርሀኗ፤ (እምላለሁ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْقَمَرِ إِذَا تَلَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy2. በጨረቃም ጸሐይን በተከተላት ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلنَّهَارِ إِذَا جَلَّىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy3. በቀንም ጸሐይን በገለፃት ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّيْلِ إِذَا يَغْشَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy4. በሌሊቱም ጸሐይን በሸፈናት ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلسَّمَآءِ وَمَا بَنَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy5. በሰማይ እና በገነባትም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْأَرْضِ وَمَا طَحَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy6. በምድር እና በዘረጋትም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَفْسٍ وَمَا سَوَّىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy7. በነፍስም ባስተካከላትም

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy8. አመጽዋንና ፍርሃቷንም ባሳወቃት (አምላክም በአላህ እምላለሁ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy9. (ነፍስን) ከኃጢአት ያጠራ ሰው ሁሉ በእርግጥ ተሳካለት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy10. በኃጢአትም የሸፈናት ሰው ሁሉ በእውነት አፈረ (ከሰረ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِطَغْوَىٰهَآ

Amharic Translation - Africa Academy11. ሰሙድ ወሰን በማለፍዋ ምክንያት አስተባበለች፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذِ ٱنۢبَعَثَ أَشْقَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy12. ጠማማዋ በተነሳ ጊዜ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ ٱللَّهِ نَاقَةَ ٱللَّهِ وَسُقْيَٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy13. ለእነርሱም የአላህ መልዕክተኛ (ሷሊህ)፡-የአላህን ግመልና የመጠጥ ተራዋን (ጠብቁላት) አላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمْدَمَ عَلَيْهِمْ رَبُّهُم بِذَنۢبِهِمْ فَسَوَّىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy14. እነርሱ አስተባበሉትም፤ ከዚያ ወጓት፤ በኃጢአታቸዉም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يَخَافُ عُقْبَٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy15. (የምታስተካክለውን) ፍፃሜዋንም አይፈራም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70