caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ibrahim፣ አንቀጽ 9

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 72 · 14:9

أَلَمْ يَأْتِكُمْ نَبَؤُا۟ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ قَوْمِ نُوحٍ وَعَادٍ وَثَمُودَ وَٱلَّذِينَ مِنۢ بَعْدِهِمْ لَا يَعْلَمُهُمْ إِلَّا ٱللَّهُ جَآءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَرَدُّوٓا۟ أَيْدِيَهُمْ فِىٓ أَفْوَٰهِهِمْ وَقَالُوٓا۟ إِنَّا كَفَرْنَا بِمَآ أُرْسِلْتُم بِهِۦ وَإِنَّا لَفِى شَكٍّ مِّمَّا تَدْعُونَنَآ إِلَيْهِ مُرِيبٍ

Amharic Translation - Africa Academy9. (ሙስሊሞች ሆይ!) የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑህ ህዝቦች፤ የዓድ፣ የሠሙድም የእነዚያም ከእነርሱ በኋላ የነበሩት ከአላህ በስተቀር ሌላ የማያውቃቸው ህዝቦች ወሬ (ታሪክ) አልመጣላችሁምን? መልዕክተኞቻቸው በማስረጃዎች መጡላቸውና እጆቻቸውን በቁጭት ሊነክሱ ወደ አፎቻቸው መለሱ: «በተላካችሁበት ነገር ካድን እኛም ወደ እርሱ ከምትጠሩን ነገር አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ነን።» አሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየእነዚያ ከናንተ በፊት የነበሩት የኑሕ ሕዝቦች የዓድም የሰሙድም የእነዚያም ከእነሱ በኋለ የነበሩት ከአላህ በስተቀር ሌላ የማያውቃቸው (ሕዝቦች) ወሬ አልመጣላችሁምን? መልክተኞቻቸው በማስረጃዎች መጧቸው፡፡ እጆቻቸውንም (በቁጭት ሊነክሱ) ወደ አፎቻቸው መለሱ፡፡ አሉም «እኛ እናንተ በርሱ በተላካችሁበት ነገር ካድን እኛም ወደርሱ ከምትጠሩን ነገር አወላዋይ በኾነ ጥርጣሬ ውስጥ ነን፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70