وَبَرَزُوا۟ لِلَّهِ جَمِيعًا فَقَالَ ٱلضُّعَفَٰٓؤُا۟ لِلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوٓا۟ إِنَّا كُنَّا لَكُمْ تَبَعًا فَهَلْ أَنتُم مُّغْنُونَ عَنَّا مِنْ عَذَابِ ٱللَّهِ مِن شَىْءٍ قَالُوا۟ لَوْ هَدَىٰنَا ٱللَّهُ لَهَدَيْنَٰكُمْ سَوَآءٌ عَلَيْنَآ أَجَزِعْنَآ أَمْ صَبَرْنَا مَا لَنَا مِن مَّحِيصٍ
Amharic Translation - Africa Academy21. የተሰበሰቡ ሆነው ለአላህ ይገለጻሉ። ሐሳበ ደካማዎቹም ተከታዮች ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርን እናንተ ከአላህ ቅጣት ከእኛ ላይ አንዳችን ነገር ተከላካዮች ናችሁን?» ይሏቸዋል። አስከታዮቹም። «አላህ ባቀናን ኖሮ በመራናችሁ ነበር።» ይሏቸዋል:: «ብንበሳጭ ወይም ብንታገሥም በእኛ ላይ ሁሉም እኩል ነው:: ለእኛ ምንም መጠጊያ የለንም።» ይላሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየተሰበሰቡም ኾነው ለአላህ ይገለጻሉ፡፡ (ሐሳበ) ደካማዎቹም (ተከታዮች) ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርን፤ እናንተ ከአላህ ቅጣት ከኛ ላይ አንዳችን ነገር ተከላካዮች ናችሁን?» ይላሉ፡፡ (አስከታዮቹም) «አላህ ባቀናን ኖሮ በእርግጥ በመራናችሁ ነበር» ይሏቸዋል፡፡ «ብንበሳጭ ወይም ብንታገስም በእኛ ላይ እኩል ነው፡፡ ለእኛ ምንም መጠጊያ የለንም» ይላሉ፡፡