caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ibrahim፣ አንቀጽ 10

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 72 · 14:10

قَالَتْ رُسُلُهُمْ أَفِى ٱللَّهِ شَكٌّ فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ يَدْعُوكُمْ لِيَغْفِرَ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُؤَخِّرَكُمْ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى قَالُوٓا۟ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُنَا تُرِيدُونَ أَن تَصُدُّونَا عَمَّا كَانَ يَعْبُدُ ءَابَآؤُنَا فَأْتُونَا بِسُلْطَٰنٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy10. መልዕክተኞቻቸው «ከኃጢአቶቻችሁ እንዲሚራችሁ ወደ ተወሰነ ጊዜም ያለ ቅጣት እንዲያቆያችሁ የሚጠራችሁ ሲሆን ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ በሆነው አላህ በመኖሩ ጥርጣሬ አለን?» አሏቸው:: ህዝቦቹም፡ «እናንተ ብጤያችን ሰው እንጂ (ሌላ ፍጡር) አይደላችሁም:: አባቶቻችን ይገዙት ከነበሩት ልትከለክሉን ትሻላችሁን? ግልጽን አስረጅ ካመጣችሁት ሌላ እስቲ አምጡልን።» አሉ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመልክተኞቻቸው «ከኀጢአቶቻችሁ እንዲምራችሁ ወደ ተወሰነ ጊዜም (ያለ ቅጣት) እንዲያቆያችሁ የሚጠራችሁ ሲኾን ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ በኾነው አላህ (በመኖሩ) ጥርጣሬ አለን?» አሏቸው፡፡ (ሕዝቦቹም) «እናንተ ብጤያችን ሰው እንጂ አይደላችሁም አባቶቻችን ይገዙት ከነበሩት ልትከለክሉን ትሻላችሁ፡፡ ግልጽንም አስረጅ (ካመጣችሁት ሌላ) አምጡልን» አሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70