caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ibrahim፣ አንቀጽ 1

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 72 · 14:1

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓر كِتَٰبٌ أَنزَلْنَٰهُ إِلَيْكَ لِتُخْرِجَ ٱلنَّاسَ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ بِإِذْنِ رَبِّهِمْ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَمِيدِ

Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ቁርኣን ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ፤ ምስጉን ወደ ሆነው ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ ወደ አንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርአን) ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ ወዳንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70