وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَةَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ أَنجَىٰكُم مِّنْ ءَالِ فِرْعَوْنَ يَسُومُونَكُمْ سُوٓءَ ٱلْعَذَابِ وَيُذَبِّحُونَ أَبْنَآءَكُمْ وَيَسْتَحْيُونَ نِسَآءَكُمْ وَفِى ذَٰلِكُم بَلَآءٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳም ለህዝቦቹ «ከፈርዖን ቤተሰቦች መጥፎን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱና ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆን በአዳናችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለላችሁን የአላህን ጸጋ አስታውሱ:: በዚሃችሁ ከጌታችሁ የሆነ ታላቅ ፈተና አለበት።» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ ከፈርዖን ቤተሰቦች መጥፎን ቅጣት የሚያቀምሱዋችሁ ወንዶች ልጆቻችሁንም የሚያርዱ ሴቶቻችሁንም የሚተዉ ሲኾኑ በአዳንናችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ (የዋለላችሁን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በዚህም ከጌታችሁ የኾነ ታላቅ ፈተና አለበት፡፡