وَقَالَ ٱلشَّيْطَٰنُ لَمَّا قُضِىَ ٱلْأَمْرُ إِنَّ ٱللَّهَ وَعَدَكُمْ وَعْدَ ٱلْحَقِّ وَوَعَدتُّكُمْ فَأَخْلَفْتُكُمْ وَمَا كَانَ لِىَ عَلَيْكُم مِّن سُلْطَٰنٍ إِلَّآ أَن دَعَوْتُكُمْ فَٱسْتَجَبْتُمْ لِى فَلَا تَلُومُونِى وَلُومُوٓا۟ أَنفُسَكُم مَّآ أَنَا۠ بِمُصْرِخِكُمْ وَمَآ أَنتُم بِمُصْرِخِىَّ إِنِّى كَفَرْتُ بِمَآ أَشْرَكْتُمُونِ مِن قَبْلُ إِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy22. ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን ይላቸዋል: «አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ እኔም ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ:: አፈረስኩባችሁም:: ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ሥልጣን አልነበረኝም:: ግና ጠራኋችሁና ታዘዛችሁኝ:: ስለዚህ አትውቀሱኝ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ:: እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም። እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ሁሉ ካድኩ በዳዮቹ ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።»
Amharic Translation - Muhammad Sadiqነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን ይላቸዋል «አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ፡፡ ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ፤ አፈረስኩባችሁም፡፡ ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልበረኝም፡፡ ግን ጠራኋችሁ፡፡ ለእኔም ታዘዛችሁ፡፡ ስለዚህ አትውቀሱኝ፤ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ፡፡ እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም፡፡ እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም፡፡ እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ካድኩ፡፡ በዳዮቹ ለእነርሱ በእርግጥ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡»