caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tahrim التحريم

12 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 107

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَ تَبْتَغِى مَرْضَاتَ أَزْوَٰجِكَ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy1. አንተ ነብይ ሆይ! አላህ ላንተ የፈቀደልህን ነገር ሚሰቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَدْ فَرَضَ ٱللَّهُ لَكُمْ تَحِلَّةَ أَيْمَٰنِكُمْ وَٱللَّهُ مَوْلَىٰكُمْ وَهُوَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy2. አላህ ለእናንተ የመሐሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፤ አላህ ረዳታችሁ ነው:: እርሱም ሁሉን አዋቂና እጅግ ጥበበኛ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ أَسَرَّ ٱلنَّبِىُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَٰجِهِۦ حَدِيثًا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِۦ وَأَظْهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُۥ وَأَعْرَضَ عَنۢ بَعْضٍ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتْ مَنْ أَنۢبَأَكَ هَٰذَا قَالَ نَبَّأَنِىَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْخَبِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy3. ነብዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ (አስታውስ):: እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራቷን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አሳወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፤ «ሁሉን አዋቂው እና ውስጠ አዋቂው ነገረኝ» አላት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن تَتُوبَآ إِلَى ٱللَّهِ فَقَدْ صَغَتْ قُلُوبُكُمَا وَإِن تَظَٰهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ هُوَ مَوْلَىٰهُ وَجِبْرِيلُ وَصَٰلِحُ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ بَعْدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy4. (ሁለታችሁም) ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና (ትስማማላችሁ):: በእርሱ (ጥቃት) ላይ ብትረዳዱ ግን ረዳቱ አላህ ነው። ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَسَىٰ رَبُّهُۥٓ إِن طَلَّقَكُنَّ أَن يُبْدِلَهُۥٓ أَزْوَٰجًا خَيْرًا مِّنكُنَّ مُسْلِمَٰتٍ مُّؤْمِنَٰتٍ قَٰنِتَٰتٍ تَٰٓئِبَٰتٍ عَٰبِدَٰتٍ سَٰٓئِحَٰتٍ ثَيِّبَٰتٍ وَأَبْكَارًا

Amharic Translation - Africa Academy5. ሁላችሁንም ቢፈታችሁ ከናንተ የበለጡ ሚስቶች ሙስሊሞች፤ ትክክለኛ አማኞች፤ ታዛዦች፤ ተጸፃቾች፤ ለአላህ ተገዢዎች፤ ጿሚዎች፤ ፈቴዎችም ደናግልም የሆኑትን ጌታው ሊለውጠው ይከጅላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَٰٓئِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ ٱللَّهَ مَآ أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy6. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከሆነች እሳት ነፍሶቻችሁንም ቤተሰቦቻችሁንም ጠብቁ፤ በእርሷ ላይ ጨካኝና ኃይለኛ የሆኑ መላዕክት አሉ:: አላህን ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَا تَعْتَذِرُوا۟ ٱلْيَوْمَ إِنَّمَا تُجْزَوْنَ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy7. እናንተ በአላህ የካዳችሁ ሰዎች ሆይ! ዛሬ አታመካኙ፤ የምትመነዱት ያንን ትሰሩት የነበራችሁትን ብቻ ነው (ይባላሉ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ تُوبُوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ تَوْبَةً نَّصُوحًا عَسَىٰ رَبُّكُمْ أَن يُكَفِّرَ عَنكُمْ سَيِّـَٔاتِكُمْ وَيُدْخِلَكُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ يَوْمَ لَا يُخْزِى ٱللَّهُ ٱلنَّبِىَّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ نُورُهُمْ يَسْعَىٰ بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَٰنِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَآ أَتْمِمْ لَنَا نُورَنَا وَٱغْفِرْ لَنَآ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy8. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ነብዩን እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያመኑትን በማያሳፍርበት፤ ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲሆን፡- «ጌታችን ሆይ! ብርሃናችንን ሙላልን፤ ለእኛ ምህረትንም አድርግልን፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና» በሚሉበት ቀን ጌታችሁ ከናንተ ኃጢአቶቻችሁን ሊሰርዝላችሁ፤ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችም ሊያስገባችሁ ይከጅላልና ንጹህ የሆነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ جَٰهِدِ ٱلْكُفَّارَ وَٱلْمُنَٰفِقِينَ وَٱغْلُظْ عَلَيْهِمْ وَمَأْوَىٰهُمْ جَهَنَّمُ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy9. አንተ ነብይ ሆይ! ከሓዲያን እና አስመሳዮችን ታገል፤ በእነርሱም ላይ በርታ፤ መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ምን ትከፋም መመለሻ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا لِّلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱمْرَأَتَ نُوحٍ وَٱمْرَأَتَ لُوطٍ كَانَتَا تَحْتَ عَبْدَيْنِ مِنْ عِبَادِنَا صَٰلِحَيْنِ فَخَانَتَاهُمَا فَلَمْ يُغْنِيَا عَنْهُمَا مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا وَقِيلَ ٱدْخُلَا ٱلنَّارَ مَعَ ٱلدَّٰخِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy10. አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች የኑህን ሚስት እና የሉጥን ሚስት ምሳሌ አደረገ፤ ባሮቻችን ከሆኑ ሁለት መልካም ባሪያዎች ስር ነበሩ ከዷቸዉም፤ ኑሕም ሉጥም ከሚስቶቻቸው ምንም የአላህን ቅጣት አልገፈተሩላቸዉም፤ «ከገቢዎችም ጋር እሳትን ግቡ» ተባሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱمْرَأَتَ فِرْعَوْنَ إِذْ قَالَتْ رَبِّ ٱبْنِ لِى عِندَكَ بَيْتًا فِى ٱلْجَنَّةِ وَنَجِّنِى مِن فِرْعَوْنَ وَعَمَلِهِۦ وَنَجِّنِى مِنَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy11. ለእነዚያ ለአመኑትም አላህ የፈርዖንን ሚስት ምሳሌ አደረገ:: «ጌታየ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለእኔ ቤት ገንባልኝ፤ ከፈርዖንና ከስራዉም አድነኝ፤ ከበደለኞች ህዝቦችም አድነኝ» ባለች ጊዜ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَرْيَمَ ٱبْنَتَ عِمْرَٰنَ ٱلَّتِىٓ أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهِ مِن رُّوحِنَا وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَٰتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِۦ وَكَانَتْ مِنَ ٱلْقَٰنِتِينَ

Amharic Translation - Africa Academy12. የዒምራን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ:: በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፋን:: በጌታዋ ቃላትና በመጽሐፍቱም አረጋገጠች፤ ከታዛዦችም ነበረች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70