وَٱلْبُدْنَ جَعَلْنَٰهَا لَكُم مِّن شَعَٰٓئِرِ ٱللَّهِ لَكُمْ فِيهَا خَيْرٌ فَٱذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ عَلَيْهَا صَوَآفَّ فَإِذَا وَجَبَتْ جُنُوبُهَا فَكُلُوا۟ مِنْهَا وَأَطْعِمُوا۟ ٱلْقَانِعَ وَٱلْمُعْتَرَّ كَذَٰلِكَ سَخَّرْنَٰهَا لَكُمْ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy36. ግመሎችንም ለእናንተ ከአላህ ሃይማኖት ምልክቶች አደረግናቸው:: በእነርሱ ለእናንተ ብዙ መልካም ጥቅሞች አሏችሁ:: በእርሷም ላይ ስታርዷት በሦስት እግሮቿ ቆማ የተሰለፈች ሆና የአላህን ስም አውሱ:: ጎኖቻቸዉም በወደቁ ጊዜ ከእርሷ ብሉ:: በግልጽ ለማኝንም ለልመና የሚያገዳድምንም አብሉ:: ልክ እንደዚሁ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ገራናት::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqግመሎችንም ለእናንተ ከአላህ ሃይማኖት ምልክቶች አደረግናቸው፡፡ በእርሷ ለእናንተ መልካም ጥቅም አላችሁ፡፡ በእርሷም ላይ (ስታርዷት) በሶስት እግሮችዋ ቆማ የተሰለፈች ሆና የአላህን ስም አውሱ፡፡ ጎኖቻቸውም በወደቁ ጊዜ ከእርሷ ብሉ፡፡ ለማኝንም ለልመና የሚያገዳድምንም አብሉ፡፡ እንደዚሁ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ገራናት፡፡