إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ ٱلَّذِى جَعَلْنَٰهُ لِلنَّاسِ سَوَآءً ٱلْعَٰكِفُ فِيهِ وَٱلْبَادِ وَمَن يُرِدْ فِيهِ بِإِلْحَادٍۭ بِظُلْمٍ نُّذِقْهُ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy25. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችን ከአላህ መንገድና ከዚያም በውስጡ ነዋሪ ለሆኑትም ሆነ ከሩቅ ለሚመጡት (ሰዎች) እኩል ካደረግነው ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሁሉ (አሳማሚ ቅጣት እንቀጣቸዋልን::) በእርሱም ውስጥ ከትክክለኛ መንገድ በመዘንበል ራሱን በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚያስብ ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ የካዱ ከአላህም መንገድና ከዚያም ለሰዎች በውስጡ ነዋሪ ለሆኑትም፣ ከሩቅ ለሚመጡትም እኩል ካደረግነው ከተከበረው መስጊድ (ሰዎችን) የሚከለክሉ (አሳማሚን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን)፡፡ በእርሱም ውስጥ (ከትክክለኛ መንገድ) በመዘንበል በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚፈልግ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን፡፡