caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Hajj፣ አንቀጽ 72

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 103 · 22:72

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٍ تَعْرِفُ فِى وُجُوهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلْمُنكَرَ يَكَادُونَ يَسْطُونَ بِٱلَّذِينَ يَتْلُونَ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِنَا قُلْ أَفَأُنَبِّئُكُم بِشَرٍّ مِّن ذَٰلِكُمُ ٱلنَّارُ وَعَدَهَا ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን የተብራሩ ሆነው በእነርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ በእነዚያ በአላህ በካዱት ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻን ታውቃለህ:: በእነዚያ አናቅጻችንን በሚያነቡት ላይም በኃይል ሊተናኮሏቸው ይቃረባሉ:: ይልቅ ከዚህ የከፋን ነገር ልንገራችሁን? እርሷም እሳት ናት:: አላህ ለእነዚያ በርሱ ለካዱት ሰዎች ሁሉ ቀጥሯታል:: መመለሻነቷ ምን ይከፋ በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአንቀጾቻችንም የተብራሩ ኾነው በእነሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ በእነዚያ በካዱት ሰዎች ፊቶች ላይ ጥላቻን ታውቃለህ፡፡ በእነዚያ በእነሱ ላይ አንቀጾቻችንን በሚያነቡት ላይ በኃይል ሊዘልሉባቸው ይቃረባሉ፡፡ «ከዚህ ይልቅ የከፋን ነገር ልንገራችሁን?» በላቸው፡፡ «(እርሱም) እሳት ናት፡፡ አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች ቀጥሯታል፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70