أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يَسْجُدُ لَهُۥ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ وَٱلشَّمْسُ وَٱلْقَمَرُ وَٱلنُّجُومُ وَٱلْجِبَالُ وَٱلشَّجَرُ وَٱلدَّوَآبُّ وَكَثِيرٌ مِّنَ ٱلنَّاسِ وَكَثِيرٌ حَقَّ عَلَيْهِ ٱلْعَذَابُ وَمَن يُهِنِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن مُّكْرِمٍ إِنَّ ٱللَّهَ يَفْعَلُ مَا يَشَآءُ
Amharic Translation - Africa Academy18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ጸሐይና፤ ጨረቃም፤ ከዋክብትም፤ ተራሮችም፤ ዛፎችም፤ ተንቀሳቃሾችም ፍጡራንና ከሰዎች ብዙዎችም ለእርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቅምን? ብዙዉም በእርሱ ላይ የአላህ ቅጣት ተረጋገጠበት:: አላህ የሚያዋርደው ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለዉም:: አላህ የሻውን ይሰራልና:: {1}
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ በሰማያት ያለው ሁሉ፣ በምድርም ያለው ሁሉ፣ ፀሐይና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾችም ከሰዎች ብዙዎችም፣ ለርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቁምን? ብዙውም በርሱ ላይ ቅጣት ተረጋገጠበት፡፡ አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም፡፡ አላህ የሻውን ይሠራልና፡፡ {1}