caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Hajj፣ አንቀጽ 26

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 103 · 22:26

وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ

Amharic Translation - Africa Academy26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለኢብራሂም የቤቱን የከዕባን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት (እንዲህ) ባልነውም ጊዜ (የሆነውን አስታውስ): «በኔ ምንንም አታጋራ:: ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት (ለኢባዳ) ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸዉም ለሚደፉት (ሩኩዕና ሱጁድ ለሚያደርጉት) ንጹህ አድርግላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» (ባልነው ጊዜ አስታውስ)፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70