caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Hajj፣ አንቀጽ 78

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 103 · 22:78

وَجَٰهِدُوا۟ فِى ٱللَّهِ حَقَّ جِهَادِهِۦ هُوَ ٱجْتَبَىٰكُمْ وَمَا جَعَلَ عَلَيْكُمْ فِى ٱلدِّينِ مِنْ حَرَجٍ مِّلَّةَ أَبِيكُمْ إِبْرَٰهِيمَ هُوَ سَمَّىٰكُمُ ٱلْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ وَفِى هَٰذَا لِيَكُونَ ٱلرَّسُولُ شَهِيدًا عَلَيْكُمْ وَتَكُونُوا۟ شُهَدَآءَ عَلَى ٱلنَّاسِ فَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱعْتَصِمُوا۟ بِٱللَّهِ هُوَ مَوْلَىٰكُمْ فَنِعْمَ ٱلْمَوْلَىٰ وَنِعْمَ ٱلنَّصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy78. በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ:: እርሱ መርጧችኋል:: በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም:: የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ:: እርሱ (አላህ) ከዚህ በፊት በነበሩት መጽሐፍትም ሆነ በዚህ ቁርኣን ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል። (ይሄዉም) መልዕክተኛው በእናንተ ላይ መስካሪ እንዲሆን እና እናንተም በሰዎች ላይ መስካሪዎች እንድትሆኑ ነው:: ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ:: ዘካንም በአግባቡ ለተገቢው ስጡ:: በአላህም ተጠበቁ:: እርሱ ረዳታችሁ ነውና:: እርሱ ምን ያማረ ጠባቂ፤ ምን ያማረም ረዳት ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ፡፡ እርሱ መርጧችኋል፡፡ በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፡፡ የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት (ተከተሉ)፡፡ እርሱ ከዚህ በፊት ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል፡፡ በዚህም (ቁርኣን)፤ መልክተኛው በእናንተ ላይ መስካሪ እንዲሆን እናንተም በሰዎቹ ላይ መስካሪዎች እንድትኾኑ (ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል)፡፡ ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ዘካንም ስጡ፣ በአላህም ተጠበቁ፣ እርሱ ረዳታችሁ ነው፡፡ (እርሱ) ምን ያምር ጠባቂ! ምን ያምርም ረዳት!
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70