إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَٱلَّذِينَ هَادُوا۟ وَٱلصَّٰبِـِٔينَ وَٱلنَّصَٰرَىٰ وَٱلْمَجُوسَ وَٱلَّذِينَ أَشْرَكُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy17. እነዚያ በአላህ ያመኑ እነዚያ አይሁዳውያን፤ እነዚያ ምንም እምነት የሌላቸው ሳቢያኖች፤ ክርስቲያኖችም፤ መጁሶችም እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ ሁሉ አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ ያመኑት፣ እነዚያም ይሁዳውያን የሆኑ፣ ሳቢያኖችም፣ ክርስቲያኖችም፣ መጁሶችም እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ አላህ በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና፡፡