caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Hajj፣ አንቀጽ 52

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 103 · 22:52

وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ وَلَا نَبِىٍّ إِلَّآ إِذَا تَمَنَّىٰٓ أَلْقَى ٱلشَّيْطَٰنُ فِىٓ أُمْنِيَّتِهِۦ فَيَنسَخُ ٱللَّهُ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ ثُمَّ يُحْكِمُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት አንድንም መልዕክተኛ ወይም ነብይ አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ውስጥ የማጥመሚያን ሀሳብ የሚጥል ቢሆን እንጂ:: ወዲያዉም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ማጥመሚያ ቃል ያስወግዳል:: ከዚያም አላህ አናቅጽን ያጠነክራል (ያጸናል):: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከመልክተኛና ከነቢይም ከአንተ በፊት አንድንም አላክንም ባነበበ (እና ዝም ባለ) ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ (ማጥመሚያን ቃል) የሚጥል ቢሆን እንጅ፡፡ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70