يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَٱسْتَمِعُوا۟ لَهُۥٓ إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَن يَخْلُقُوا۟ ذُبَابًا وَلَوِ ٱجْتَمَعُوا۟ لَهُۥ وَإِن يَسْلُبْهُمُ ٱلذُّبَابُ شَيْـًٔا لَّا يَسْتَنقِذُوهُ مِنْهُ ضَعُفَ ٱلطَّالِبُ وَٱلْمَطْلُوبُ
Amharic Translation - Africa Academy73. ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ:: ለእርሱም አድምጡት፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት ሁሉ ዝንብን ለመፍጠር ቢሰበሰቡ ፈጽሞ መፍጠር እንኳ አይችሉም:: አንዳችንም ነገር ዝንብ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም:: ፈላጊዉም (አምላኪው) ተፈላጊዉም (ተመላኪው) ደከሙ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ፡፡ ለእርሱም አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት) ዝንብን ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡ እርሱን (ለመፍጠር) ቢሰበሰቡም እንኳን (አይችሉም)፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም፡፡ ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ፡፡