ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ حُرُمَٰتِ ٱللَّهِ فَهُوَ خَيْرٌ لَّهُۥ عِندَ رَبِّهِۦ وَأُحِلَّتْ لَكُمُ ٱلْأَنْعَٰمُ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ
Amharic Translation - Africa Academy30. ይሀው ነው። የአላህንም ህግጋት የሚያከብር ሁሉ እርሱ እጌታው ዘንድ ለእርሱ በጣም የተሻለ መልካም ነው:: የቤት እንስሳትም በእናንተ ላይ እርም መሆኑ ከሚነበብላችሁ በስተቀር ለእናንተ ተፈቅዳላችኋለች:: ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ:: ሐሰትንም ቃል ራቁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ነገሩ) ይህ ነው፡፡ የአላህንም ሕግጋት የሚያከብር ሰው እርሱ ጌታው ዘንድ ለእርሱ በጣም የተሻለ ነው፡፡ የቤት እንስሳትም (ግመል ከብት በግና ፍየል) በናንተ ላይ (እርም መሆኑ) ከሚነበብላችሁ በስተቀር ለእናንተ ተፈቅዳላችኋለች፡፡ ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ፡፡