يَوْمَ تَرَوْنَهَا تَذْهَلُ كُلُّ مُرْضِعَةٍ عَمَّآ أَرْضَعَتْ وَتَضَعُ كُلُّ ذَاتِ حَمْلٍ حَمْلَهَا وَتَرَى ٱلنَّاسَ سُكَٰرَىٰ وَمَا هُم بِسُكَٰرَىٰ وَلَٰكِنَّ عَذَابَ ٱللَّهِ شَدِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy2. በምታዩዋት ቀን ሁኔታው አጥቢ ሁሉ ያጠባችውን ልጅ ትዘነጋዋለች። እርጉዝ ሴት ሁሉ እርጉዝዋን ትጨነግፋለች:: ሰዎቹንም በድንጋጤ ብርታት የሰከሩ መስለው ታያቸዋለህ:: እነርሱ ከመጠጥ የሰከሩ ሁው ሳይሆን ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ስለሆነ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበምታዩዋት ቀን አጥቢዋ ሁሉ ከአጠባችው ልጅ ትፈዝዛለች፡፡ የእርግዝና ባለቤት የኾነችም ሁሉ እርጉዟን ትጨነግፋለች፡፡ ሰዎቹንም (በድንጋጤ ብርታት) የሰከሩ ኾነው ታያለህ፡፡ እነርሱም (ከመጠጥ) የሰከሩ አይደሉም፡፡ ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ነው፡፡