caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Anbiyaa الأنبياء

112 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 73

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٱقْتَرَبَ لِلنَّاسِ حِسَابُهُمْ وَهُمْ فِى غَفْلَةٍ مُّعْرِضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy1. ለሰዎች እነርሱ በዝንጋታ ውስጥ መሰናዳትን የተዉ ሆነው ሳሉ ምርመራቸው ቀረበ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا يَأْتِيهِم مِّن ذِكْرٍ مِّن رَّبِّهِم مُّحْدَثٍ إِلَّا ٱسْتَمَعُوهُ وَهُمْ يَلْعَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy2. ከጌታቸው አዲስ የተወረደ ቁርኣን አይመጣላቸዉም:: እነርሱ የሚያላግጡበት ሆነው ፤ የሚያዳምጡት ቢሆኑ እንጂ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَاهِيَةً قُلُوبُهُمْ وَأَسَرُّوا۟ ٱلنَّجْوَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ هَلْ هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ أَفَتَأْتُونَ ٱلسِّحْرَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3.ልቦቻቸው ዝንጉዎች ሆነው። እነዚያም የበደሉት ሰዎች መንሾካሾክን ደበቁ:: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ ነውን? እናንተም የምታዩ ስትሆኑ ድግምትን ለመቀበል ትመጣላችሁን?» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّى يَعْلَمُ ٱلْقَوْلَ فِى ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy4. (ሙሐመድም) «ጌታዬ ቃልን ሁሉ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለ ሲሆን ያውቃል:: እርሱም ሰሚና አዋቂ ነው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ قَالُوٓا۟ أَضْغَٰثُ أَحْلَٰمٍۭ بَلِ ٱفْتَرَىٰهُ بَلْ هُوَ شَاعِرٌ فَلْيَأْتِنَا بِـَٔايَةٍ كَمَآ أُرْسِلَ ٱلْأَوَّلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy5. በእውነቱ «ቁርኣኑ የሕልሞች ቅዠቶች ነው። ይልቁንም ቀጠፈው፤ እንዲያዉም እርሱ ቅኔን ገጣሚ ነው:: የቀድሞዎቹም እንደ ተላኩ ሁሉ መልዕክተኛ ከሆነ በተዓምር ይምጣብን።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَآ ءَامَنَتْ قَبْلَهُم مِّن قَرْيَةٍ أَهْلَكْنَٰهَآ أَفَهُمْ يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy6. ከእነርሱ በፊት ያጠፋናት ከተማ አላመነችም:: ታዲያ እነርሱ ያምናሉን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy7.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአንተም በፊት ወደእነሱ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፡፡ የማታውቁ ከሆናችሁ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا جَعَلْنَٰهُمْ جَسَدًا لَّا يَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَمَا كَانُوا۟ خَٰلِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy8.ምግብን የማይበላ አካልም አላደረግናቸዉም:: ዘውታሪዎችም አልነበሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ صَدَقْنَٰهُمُ ٱلْوَعْدَ فَأَنجَيْنَٰهُمْ وَمَن نَّشَآءُ وَأَهْلَكْنَا ٱلْمُسْرِفِينَ

Amharic Translation - Africa Academy9.ከዚያ ቀጠሮን ሞላንላቸውና እነርሱንና የምንሻውን ሰው አዳንናቸዉም:: ወሰን አላፊዎችንም አጠፋን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ أَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ كِتَٰبًا فِيهِ ذِكْرُكُمْ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. (ሙስሊሞች ሆይ!) ክብራችሁ በውስጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደእናንተ በእርግጥ አወረድን፡፡ አታውቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَمْ قَصَمْنَا مِن قَرْيَةٍ كَانَتْ ظَالِمَةً وَأَنشَأْنَا بَعْدَهَا قَوْمًا ءَاخَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy11. በዳይም ከነበረች ከተማ ያጠፋናትና ከኋላዋም ሌሎችን ህዝቦች ያስገኘነው ብዙ ናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّآ أَحَسُّوا۟ بَأْسَنَآ إِذَا هُم مِّنْهَا يَرْكُضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy12. ቅጣታችንም በተሰማቸው ጊዜ እነርሱ ወዲያውኑ ከርሷ ለመሸሽ ይገሰግሳሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا تَرْكُضُوا۟ وَٱرْجِعُوٓا۟ إِلَىٰ مَآ أُتْرِفْتُمْ فِيهِ وَمَسَٰكِنِكُمْ لَعَلَّكُمْ تُسْـَٔلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy13. «አትገስግሱ፤ ትጠየቁም ይሆናልና በእርሱ ወደ ተቀማጠላችሁበት ጸጋ ወደ መኖሪያዎቻችሁም ተመለሱ።» ይባላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ يَٰوَيْلَنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy14. «ዋ ጥፋታችን! እኛ በእርግጥ በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَا زَالَت تِّلْكَ دَعْوَىٰهُمْ حَتَّىٰ جَعَلْنَٰهُمْ حَصِيدًا خَٰمِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy15.የታጨዱ ሬሳዎችም እስካደረግናቸው ድረስ ይህቺ ጥሪያቸው ከመሆን አልተወገደችም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا خَلَقْنَا ٱلسَّمَآءَ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا لَٰعِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy16. ሰማይንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ أَرَدْنَآ أَن نَّتَّخِذَ لَهْوًا لَّٱتَّخَذْنَٰهُ مِن لَّدُنَّآ إِن كُنَّا فَٰعِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy17.መጫዎቻን (ሚስትንና ልጅን) ልንይዝ በሻን ኖሮ ከኛ ዘንድ በያዝነው ነበር፤ ግን ሰሪዎች አይደለንም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ نَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَى ٱلْبَٰطِلِ فَيَدْمَغُهُۥ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٌ وَلَكُمُ ٱلْوَيْلُ مِمَّا تَصِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy18. በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን:: አንጎሉን ያፈርሰዋልም:: ወዲያዉም እርሱ ጠፊ ነው:: ለእናንተም ከዚያ (ሚስትና ልጅ) አለው በማለት ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ:: (ወዮላችሁ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَهُۥ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَنْ عِندَهُۥ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِۦ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. በሰማያትና በምድር ዉስጥ ያለው ሁሉም የእርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም:: አይሰለቹምም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُسَبِّحُونَ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ لَا يَفْتُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy20. በበሌሊትና በቀንም ያጠሩታል:: አይታክቱም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمِ ٱتَّخَذُوٓا۟ ءَالِهَةً مِّنَ ٱلْأَرْضِ هُمْ يُنشِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. ይልቁንም ከምድር የሆኑን ሙታንን የሚያስነሱ አማልክትን ያዙን? የለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ كَانَ فِيهِمَآ ءَالِهَةٌ إِلَّا ٱللَّهُ لَفَسَدَتَا فَسُبْحَٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy22.በሰማያትና በምድር ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ ሁለቱም በተበላሹ ነበር:: የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يُسْـَٔلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْـَٔلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. አላህ ከሚሰራው ሁሉ አይጠየቅም:: እነርሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمِ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةً قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ هَٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِىَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِى بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ ٱلْحَقَّ فَهُم مُّعْرِضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም ከርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን? «አስረጃችሁን አምጡ:: ይህ ቁርኣን እኔ ዘንድ ያለው ህዝብ መገሰጫ፤ ከኔ በፊትም የነበሩት ህዝቦች መገሠጫ ነው።» በላቸው:: እንዲያዉም አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም:: ስለዚህ እነርሱ እንቢተኞች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

Amharic Translation - Africa Academy25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጂ ከመልዕክተኛ አንድንም አላክንም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحْمَٰنُ وَلَدًا سُبْحَٰنَهُۥ بَلْ عِبَادٌ مُّكْرَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. «አር-ረሕማንም ከመላእክት መካከል ልጅን ያዘ።» አሉ። ጥራት ተገባው። አይደለም መላእክት የተከበሩ ባሮች ብቻ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَسْبِقُونَهُۥ بِٱلْقَوْلِ وَهُم بِأَمْرِهِۦ يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy27. በንግግር አይቀድሙትም፤ ያዘዘውንም ይፈጽማሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ٱرْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِۦ مُشْفِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy28.በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል:: ለወደደውም እንጂ ለሌላው አያማልዱም:: እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَقُلْ مِنْهُمْ إِنِّىٓ إِلَٰهٌ مِّن دُونِهِۦ فَذَٰلِكَ نَجْزِيهِ جَهَنَّمَ كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy29. ከእነርሱም «እኔ ከእርሱ ሌላ አምላክ ነኝ።» የሚል ያንን ገሀነምን እንመነዳዋለን፤ በዳዮችን እንደዚሁ እንመነዳለን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَرَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَنَّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ كَانَتَا رَتْقًا فَفَتَقْنَٰهُمَا وَجَعَلْنَا مِنَ ٱلْمَآءِ كُلَّ شَىْءٍ حَىٍّ أَفَلَا يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy30. እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መሆናችንን አያውቁምን? ህያው የሆነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን። አያምኑምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلْنَا فِى ٱلْأَرْضِ رَوَٰسِىَ أَن تَمِيدَ بِهِمْ وَجَعَلْنَا فِيهَا فِجَاجًا سُبُلًا لَّعَلَّهُمْ يَهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy31. በምድርም ውስጥ በእነርሱ እንዳታረገርግ ጋራዎችን አደረግን። ይመሩም ዘንድ በእርሷ ውስጥ ሰፋፊ መንገዶችን አደረግን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلْنَا ٱلسَّمَآءَ سَقْفًا مَّحْفُوظًا وَهُمْ عَنْ ءَايَٰتِهَا مُعْرِضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. ሰማይንም ከመውደቅ የተጠበቀ ጣራ አደረግን:: እነርሱ ግን ከተዓምራቱ ዘንጊዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ وَٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ كُلٌّ فِى فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy33.እርሱም ሌሊትንና ቀንን ጸሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው:: ሁሉም በየ ምህዋራቸው (ፈለካቸው) ውስጥ ይዋኛሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا جَعَلْنَا لِبَشَرٍ مِّن قَبْلِكَ ٱلْخُلْدَ أَفَإِي۟ن مِّتَّ فَهُمُ ٱلْخَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም:: ታዲያ ብትሞት እነርሱ ዘውታሪዎች ናቸውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كُلُّ نَفْسٍ ذَآئِقَةُ ٱلْمَوْتِ وَنَبْلُوكُم بِٱلشَّرِّ وَٱلْخَيْرِ فِتْنَةً وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy35.(ሰዎች ሆይ!) ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት:: ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን:: ወደ እኛም ትመለሳላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا رَءَاكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَٰذَا ٱلَّذِى يَذْكُرُ ءَالِهَتَكُمْ وَهُم بِذِكْرِ ٱلرَّحْمَٰنِ هُمْ كَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች ባዩህ ጊዜ መሳለቂያ አድርገው እንጂ አይዙህም። እነርሱ በአር-ረህማን መወሳት እነርሱ ከሓዲያን ሲሆኑ: «ያ አማልክቶቻችሁን በክፉ የሚያነሳቸው ይህ ነውን?» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خُلِقَ ٱلْإِنسَٰنُ مِنْ عَجَلٍ سَأُو۟رِيكُمْ ءَايَٰتِى فَلَا تَسْتَعْجِلُونِ

Amharic Translation - Africa Academy37. ሰው ቸኳይ ሆኖ ተፈጠረ:: ታዓምራቶቼን በእርግጥ አሳያችኋለሁና አታቻኩሉኝ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy38. «እውነተኞች ከሆናቸሁ ይህ ቀጠሮም መቼ ነው?» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ يَعْلَمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ حِينَ لَا يَكُفُّونَ عَن وُجُوهِهِمُ ٱلنَّارَ وَلَا عَن ظُهُورِهِمْ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy39.እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች ከፊቶቻቸውና ከጀርቦቻቸው ላይ እሳትን የማይከለክሉበትን እነርሱም የማይረዳዱበትን ጊዜ ቢያውቁ ኖሮ ይህንን አይሉም ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ تَأْتِيهِم بَغْتَةً فَتَبْهَتُهُمْ فَلَا يَسْتَطِيعُونَ رَدَّهَا وَلَا هُمْ يُنظَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy40. ይልቁንም ሰዓቲቱ በድንገት ትመጣቸዋለች:: ታስደነግጣቸዋለችም:: መመለሷንም አይችሉም:: እነርሱም የሚቆይላቸው አይደሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدِ ٱسْتُهْزِئَ بِرُسُلٍ مِّن قَبْلِكَ فَحَاقَ بِٱلَّذِينَ سَخِرُوا۟ مِنْهُم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም የነበሩት መልዕክተኞች በእርግጥ ተቀለደባቸው፤ በእነዚያ ከእነርሱ ይቀልዱ በነበሩት ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ሰፈረባቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ مَن يَكْلَؤُكُم بِٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ مِنَ ٱلرَّحْمَٰنِ بَلْ هُمْ عَن ذِكْرِ رَبِّهِم مُّعْرِضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአር-ረህማን ቅጣት በሌሊትና በቀን የሚጠብቃችሁ ማነው?» በላቸው:: በእውነቱ እነርሱ ከጌታቸው ግሠጼ ከቁርኣን ዘንጊዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ لَهُمْ ءَالِهَةٌ تَمْنَعُهُم مِّن دُونِنَا لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَ أَنفُسِهِمْ وَلَا هُم مِّنَّا يُصْحَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy43.ለእነርሱ ከእኛ ሌላ የምትከላከልላቸው አማልዕክት አለቻቸውን? ነፍሶቻቸውን መርዳትን አይችሉም:: እነርሱም (ከሓዲያኑ) ከእኛ አይጠብቁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ مَتَّعْنَا هَٰٓؤُلَآءِ وَءَابَآءَهُمْ حَتَّىٰ طَالَ عَلَيْهِمُ ٱلْعُمُرُ أَفَلَا يَرَوْنَ أَنَّا نَأْتِى ٱلْأَرْضَ نَنقُصُهَا مِنْ أَطْرَافِهَآ أَفَهُمُ ٱلْغَٰلِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy44.በእውነትም እነዚህንና አባቶቻቸውን በእነርሱ ላይ ዕድሜ እስከ ረዘመባቸው ድረስ አጣቀምናቸው:: ተታለሉም። እኛ ምድርን ከጫፎቿ የምናጎድላት ሆነን ስንመጣባት አያዩምን? እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ إِنَّمَآ أُنذِرُكُم بِٱلْوَحْىِ وَلَا يَسْمَعُ ٱلصُّمُّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا مَا يُنذَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የማስፈራራችሁ በተወረድልኝ ብቻ ነው። ግን ደንቆሮዎች በሚስፈራሩበት ጊዜ ጥሪን አይሰሙም።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَئِن مَّسَّتْهُمْ نَفْحَةٌ مِّنْ عَذَابِ رَبِّكَ لَيَقُولُنَّ يَٰوَيْلَنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. ከጌታህ ቅጣትም ወላፈን ብትነካቸው «ዋ ጥፋታችን! እኛ በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَضَعُ ٱلْمَوَٰزِينَ ٱلْقِسْطَ لِيَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ فَلَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْـًٔا وَإِن كَانَ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ أَتَيْنَا بِهَا وَكَفَىٰ بِنَا حَٰسِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy47.በትንሳኤ ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን:: ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም:: ስራው የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢሆንም እርሷን እናመጣታለን:: ተቆጣጣሪነትም በእኛ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ ٱلْفُرْقَانَ وَضِيَآءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy48. ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንን ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُم بِٱلْغَيْبِ وَهُم مِّنَ ٱلسَّاعَةِ مُشْفِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy49. ለእነዚያ ጌታቸውን በሩቅ ለሚፈሩት እነርሱም ከሰዓቲቱ ተጨናቂዎች ለሆኑት መገሰጫን ሰጠን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهَٰذَا ذِكْرٌ مُّبَارَكٌ أَنزَلْنَٰهُ أَفَأَنتُمْ لَهُۥ مُنكِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy50.ይህም (ቁርኣን) ያወረድነው የኾነ ብሩክ መገሰጫ ነው፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲያን ናችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ ءَاتَيْنَآ إِبْرَٰهِيمَ رُشْدَهُۥ مِن قَبْلُ وَكُنَّا بِهِۦ عَٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy51. ለኢብራሂምም ከዚያ በፊት ቅን መንገዱን በእርግጥ ሰጠነው:: እኛም በእርሱ ተገቢነት አዋቂዎች ነበርን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا هَٰذِهِ ٱلتَّمَاثِيلُ ٱلَّتِىٓ أَنتُمْ لَهَا عَٰكِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy52. ለአባቱና ለህዝቦቹ፡- «ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የሆናችኃት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ وَجَدْنَآ ءَابَآءَنَا لَهَا عَٰبِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy53. «አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ሆነው አገኘን።» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لَقَدْ كُنتُمْ أَنتُمْ وَءَابَآؤُكُمْ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy54. «እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ أَجِئْتَنَا بِٱلْحَقِّ أَمْ أَنتَ مِنَ ٱللَّٰعِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy55. «በምሩ መጣህልን? ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ?» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ بَل رَّبُّكُمْ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ٱلَّذِى فَطَرَهُنَّ وَأَنَا۠ عَلَىٰ ذَٰلِكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy56. (እርሱም) አለ: «አይደለም። ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው:: እኔም በይሃችሁ ላይ ከመስካሪዎች ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَٱللَّهِ لَأَكِيدَنَّ أَصْنَٰمَكُم بَعْدَ أَن تُوَلُّوا۟ مُدْبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy57. «በአላህ እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን ተንኮል እሰራባቸዋለሁ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَجَعَلَهُمْ جُذَٰذًا إِلَّا كَبِيرًا لَّهُمْ لَعَلَّهُمْ إِلَيْهِ يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy58. ዘወር ሲሉም ስብርብሮች አደረጋቸው:: ለእነርሱ የሆነ አንድ ትልቅ ጣዖት ብቻ ሲቀር :: ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እርሱን ብቻ ተወው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ مَن فَعَلَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَآ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy59. «በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራ ማነው? እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُۥٓ إِبْرَٰهِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy60. «ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (ወጣት) በመጥፎ ሲያነሳቸው ሰምተናል።» ተባባሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ فَأْتُوا۟ بِهِۦ عَلَىٰٓ أَعْيُنِ ٱلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَشْهَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. «ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎች ዓይን ፊት ላይ አምጡት።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ ءَأَنتَ فَعَلْتَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَا يَٰٓإِبْرَٰهِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy62. «ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራህ አንተ ነህን?» አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ بَلْ فَعَلَهُۥ كَبِيرُهُمْ هَٰذَا فَسْـَٔلُوهُمْ إِن كَانُوا۟ يَنطِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy63. «አይደለም:: ይህ ትልቃቸው ሰራው፤ ይናገሩም እንደ ሆነ ጠይቋቸው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَرَجَعُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ فَقَالُوٓا۟ إِنَّكُمْ أَنتُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy64. ወደ ነፍሶቻቸዉም ተመለሱ: «እናንተ በመጠየቃችሁ በዳዮቹ እናንተው ናችሁ።» ተባባሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ نُكِسُوا۟ عَلَىٰ رُءُوسِهِمْ لَقَدْ عَلِمْتَ مَا هَٰٓؤُلَآءِ يَنطِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy65. ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡና «እነዚህ የሚናገሩ አለመሆናቸውን በእርግጥ አውቀሃል።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَفَتَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمْ شَيْـًٔا وَلَا يَضُرُّكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy66.ኢብራሂምም አላቸው: «ታዲያ ለእናንተ ብታመልኳቸው ምንም የማይጠቅማችሁንና ባታመልኳቸዉም በምንም ነገር የማይጎዳችሁን ጣዖታትን ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُفٍّ لَّكُمْ وَلِمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy67. «ኡፍ! ለእናንተም ሆነ ከአላህ ሌላ ለምትገዙት ጣዖታት። አታስተውሉምን?» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ حَرِّقُوهُ وَٱنصُرُوٓا۟ ءَالِهَتَكُمْ إِن كُنتُمْ فَٰعِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy68. «ሰሪዎች (ተቆርቋሪዎች) እንደ ሆናችሁ ኢብራሂምን በእሳት አቃጥሉት አማልክቶቻችሁንም እርዱ።» አሉ:: (በእሳት ላይ ጣሉትም።)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْنَا يَٰنَارُ كُونِى بَرْدًا وَسَلَٰمًا عَلَىٰٓ إِبْرَٰهِيمَ

Amharic Translation - Africa Academy69. «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛና ሰላም ሁኚ።» አልን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَرَادُوا۟ بِهِۦ كَيْدًا فَجَعَلْنَٰهُمُ ٱلْأَخْسَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy70. በእርሱም ተንኮልን አሰቡ። በጣም ከሳሪዎች አደረግናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَجَّيْنَٰهُ وَلُوطًا إِلَى ٱلْأَرْضِ ٱلَّتِى بَٰرَكْنَا فِيهَا لِلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy71. እርሱንና ሉጥንም ወደዚያች በውስጡ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር በመውሰድ አዳንናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَوَهَبْنَا لَهُۥٓ إِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ نَافِلَةً وَكُلًّا جَعَلْنَا صَٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy72.ለእርሱም ኢስሐቅን ያዕቆብንም ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው:: ሁሉንም መልካሞች አደረግን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلْنَٰهُمْ أَئِمَّةً يَهْدُونَ بِأَمْرِنَا وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰةِ وَكَانُوا۟ لَنَا عَٰبِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy73. በትእዛዛችንም ወደ በጎ ስራ የሚመሩ መሪዎች አደረግናቸው:: ወደነሱም መልካም ስራዎችን መስራትን፤ ሶላትንም መስገድን ዘካንም መስጠትን አወረድን:: ለእኛም ተገዢዎች ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلُوطًا ءَاتَيْنَٰهُ حُكْمًا وَعِلْمًا وَنَجَّيْنَٰهُ مِنَ ٱلْقَرْيَةِ ٱلَّتِى كَانَت تَّعْمَلُ ٱلْخَبَٰٓئِثَ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمَ سَوْءٍ فَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy74. ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው:: ከዚያችም መጥፎ ስራዎችን ትሰራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው:: እነርሱ ክፉ ሰዎች አመጸኞች ነበሩና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَدْخَلْنَٰهُ فِى رَحْمَتِنَآ إِنَّهُۥ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy75. በችሮታችንም ውስጥ አስገባነው:: እርሱ ከመልካሞች አንዱ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنُوحًا إِذْ نَادَىٰ مِن قَبْلُ فَٱسْتَجَبْنَا لَهُۥ فَنَجَّيْنَٰهُ وَأَهْلَهُۥ مِنَ ٱلْكَرْبِ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy76.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኑሕንም ከዚያ በፊት ጌታውን በጠራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَصَرْنَٰهُ مِنَ ٱلْقَوْمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَآ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمَ سَوْءٍ فَأَغْرَقْنَٰهُمْ أَجْمَعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy77.ከእነዚያም በታዓምራቶቻችን ከአስተባበሉት ህዝቦች ተንኮል ጠበቅነው:: እነርሱ ክፉ ህዝቦች አመጸኞች ነበሩና ሁሉንም አሰመጥናቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَدَاوُۥدَ وَسُلَيْمَٰنَ إِذْ يَحْكُمَانِ فِى ٱلْحَرْثِ إِذْ نَفَشَتْ فِيهِ غَنَمُ ٱلْقَوْمِ وَكُنَّا لِحُكْمِهِمْ شَٰهِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy78.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! ) ዳውድንና ሱለይማንንም በአዝመራው ነገር በሚፈርዱ ጊዜ የህዝቦቸ ፍየሎች ሌሊት በእርሱ ውስጥ በተሰማሩ ጊዜ አስታውስ:: ፍርዳቸውንም አዋቂዎች ነበርን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَفَهَّمْنَٰهَا سُلَيْمَٰنَ وَكُلًّا ءَاتَيْنَا حُكْمًا وَعِلْمًا وَسَخَّرْنَا مَعَ دَاوُۥدَ ٱلْجِبَالَ يُسَبِّحْنَ وَٱلطَّيْرَ وَكُنَّا فَٰعِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy79. ለሱለይማንም ትክክለኛይቱን ፍርድ አሳወቅነው:: ለሁሉም ጥበብንና እውቀትን ሰጠን:: ተራራዎችን ከዳውድ ጋር የሚያወድሱ ሲሆን ገራን፤ አእዋፍንም እንደዚሁ ገራን ሰሪዎችም ነበርን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَلَّمْنَٰهُ صَنْعَةَ لَبُوسٍ لَّكُمْ لِتُحْصِنَكُم مِّنۢ بَأْسِكُمْ فَهَلْ أَنتُمْ شَٰكِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy80.የብረት ልብስንም ስራ ለእናንተ ከጦራችሁ ትጠብቃችሁ ዘንድ አስተማርነው:: እናንተ አመስጋኞች ናችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِسُلَيْمَٰنَ ٱلرِّيحَ عَاصِفَةً تَجْرِى بِأَمْرِهِۦٓ إِلَى ٱلْأَرْضِ ٱلَّتِى بَٰرَكْنَا فِيهَا وَكُنَّا بِكُلِّ شَىْءٍ عَٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy81. ለሱለይማንም ነፋስን በኃይል የምትነፍስ በትእዛዙ ወደዚያች በእርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (ወደ ሻም) የምትነፍስ ስትሆን (ገራንለት) በነገሩ ሁሉም አዋቂዎች ነበርን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنَ ٱلشَّيَٰطِينِ مَن يَغُوصُونَ لَهُۥ وَيَعْمَلُونَ عَمَلًا دُونَ ذَٰلِكَ وَكُنَّا لَهُمْ حَٰفِظِينَ

Amharic Translation - Africa Academy82.ከሰይጣናትም ለእርሱ (ሉልን ለማውጣት) የሚጠልሙንና ከዚያ ሌላ ያለን ስራ የሚሰሩን ገራንለት፤ ለእነርሱም ተጠባባቂዎች ነበርን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّى مَسَّنِىَ ٱلضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ:: አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ።» ሲል በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱسْتَجَبْنَا لَهُۥ فَكَشَفْنَا مَا بِهِۦ مِن ضُرٍّ وَءَاتَيْنَٰهُ أَهْلَهُۥ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنْ عِندِنَا وَذِكْرَىٰ لِلْعَٰبِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy84. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን:: ቤተሰቦቹንም ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا ٱلْكِفْلِ كُلٌّ مِّنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy85. ኢስማዒልንም፤ ኢድሪስንም፤ ዙልኪፍልንም፤ አስታውስ:: ሁሉም ከታጋሾች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَدْخَلْنَٰهُمْ فِى رَحْمَتِنَآ إِنَّهُم مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy86. በችሮታችንም ውስጥ አስገባናቸው:: እነርሱ ከመልካሞቹ ናቸውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَذَا ٱلنُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَٰضِبًا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقْدِرَ عَلَيْهِ فَنَادَىٰ فِى ٱلظُّلُمَٰتِ أَن لَّآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنتَ سُبْحَٰنَكَ إِنِّى كُنتُ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በሄደ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ:: ዓሳም ዋጠው:: በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ «ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ጥራት ይገባህ:: እኔ በእርግጥ ከበዳዮች ነበርኩ።» በማለት ተጣራ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱسْتَجَبْنَا لَهُۥ وَنَجَّيْنَٰهُ مِنَ ٱلْغَمِّ وَكَذَٰلِكَ نُـۨجِى ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy88. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ከጭንቅም አዳነው:: ልክ እንደዚሁም ምዕምናንን እናድናለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَزَكَرِيَّآ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥ رَبِّ لَا تَذَرْنِى فَرْدًا وَأَنتَ خَيْرُ ٱلْوَٰرِثِينَ

Amharic Translation - Africa Academy89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ:: አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ።» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ አስታውስ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱسْتَجَبْنَا لَهُۥ وَوَهَبْنَا لَهُۥ يَحْيَىٰ وَأَصْلَحْنَا لَهُۥ زَوْجَهُۥٓ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ يُسَٰرِعُونَ فِى ٱلْخَيْرَٰتِ وَيَدْعُونَنَا رَغَبًا وَرَهَبًا وَكَانُوا۟ لَنَا خَٰشِعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy90. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ለእርሱም የህያን ሰጠነው:: ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት:: እነርሱ በበጎ ስራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ:: ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّتِىٓ أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلْنَٰهَا وَٱبْنَهَآ ءَايَةً لِّلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy91.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያችንም ብልቷን (ከዝሙት) የጠበቀችውንና በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን እርሷንም ሆነ ልጇን ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ

Amharic Translation - Africa Academy92. እነዚህ ህግጋት አንድ መንገድ ሲሆኑ በእርግጥ የሃይማኖታችሁ ህግጋት ናቸው:: እኔም ጌታችሁ ነኝና ተገዙኝ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَقَطَّعُوٓا۟ أَمْرَهُم بَيْنَهُمْ كُلٌّ إِلَيْنَا رَٰجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy93.በሃይማኖታቸዉም ነገር በመካከላቸው ተለያዩ:: ሁሉም ወደ እኛ ተመላሾች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَن يَعْمَلْ مِنَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَا كُفْرَانَ لِسَعْيِهِۦ وَإِنَّا لَهُۥ كَٰتِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy94. እርሱ ያመነ ሆኖ ከበጎ ስራዎች ማንኛውንም የሚሰራም ምንዳውን አይነፍግም፤ እኛም ለእርሱ መዝጋቢዎች ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَحَرَٰمٌ عَلَىٰ قَرْيَةٍ أَهْلَكْنَٰهَآ أَنَّهُمْ لَا يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy95. ባጠፋናትም ከተማ ላይ ዘበት ነው፤ (ወደ ዱኒያ) አይመለሱምና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَا فُتِحَتْ يَأْجُوجُ وَمَأْجُوجُ وَهُم مِّن كُلِّ حَدَبٍ يَنسِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy96.የዕጁጅና መዕጁጅም እነርሱ ከየሸንተረሩ የሚንደረደሩ ሲሆኑ ግድባቸው በተከፈተች ጊዜ ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱقْتَرَبَ ٱلْوَعْدُ ٱلْحَقُّ فَإِذَا هِىَ شَٰخِصَةٌ أَبْصَٰرُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يَٰوَيْلَنَا قَدْ كُنَّا فِى غَفْلَةٍ مِّنْ هَٰذَا بَلْ كُنَّا ظَٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy97. እውነተኛዉም ቀጠሮ በቀረበ ጊዜ ያንን ጊዜ እነሆ የእነዚያ ከሀዲያን ዓይኖች ይፈጥጣሉ:: «ዋ ጥፍታችን! ከዚያ ቀን በእርግጥ በዝንጋቴ ላይ ነበርን:: በእውነትም በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمْ لَهَا وَٰرِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy98. (ከሓዲያን ሆይ!) እናንተና ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ:: እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ كَانَ هَٰٓؤُلَآءِ ءَالِهَةً مَّا وَرَدُوهَا وَكُلٌّ فِيهَا خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy99.እነዚህ ጣዖታት አማልክት በነበሩ ኖሮ ገሀነምን አይገቧትም ነበር:: ግን ሁሉም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَهُمْ فِيهَا زَفِيرٌ وَهُمْ فِيهَا لَا يَسْمَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy100.እነርሱ በእርሷ ውስጥ ይንሰቀሰቃሉ:: እነርሱም በውስጧ ምንንም አይሰሙም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ سَبَقَتْ لَهُم مِّنَّا ٱلْحُسْنَىٰٓ أُو۟لَٰٓئِكَ عَنْهَا مُبْعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy101. እነዚያ ከእኛ መልካሟ ቃል ለእነርሱ ያለፈችላቸው እነዚያ ከእርሷ የተራቁ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَسْمَعُونَ حَسِيسَهَا وَهُمْ فِى مَا ٱشْتَهَتْ أَنفُسُهُمْ خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy102. ድምጿንም አይሰሙም:: እነርሱም ነፍሶቻቸው በሚሹት ነገር ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَحْزُنُهُمُ ٱلْفَزَعُ ٱلْأَكْبَرُ وَتَتَلَقَّىٰهُمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ هَٰذَا يَوْمُكُمُ ٱلَّذِى كُنتُمْ تُوعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy103. ታላቁ ድንጋጤ አያስተክዛቸዉም:: መላእክትም «ይህ ያ ! ትቀጠሩት የነበራችሁት ቀናችሁ ነው።» እያሉ ይቀበሏቸዋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ نَطْوِى ٱلسَّمَآءَ كَطَىِّ ٱلسِّجِلِّ لِلْكُتُبِ كَمَا بَدَأْنَآ أَوَّلَ خَلْقٍ نُّعِيدُهُۥ وَعْدًا عَلَيْنَآ إِنَّا كُنَّا فَٰعِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመጽሐፎች ገፆች እንደሚጠቀለሉ ሁሉ ሰማይን የምንጠቀልልበትን ቀን አስታውስ:: የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን:: ይህን መፈጸሙ የማይቀር ቀጠሮን ቀጠርን:: እኛ የቀጠርነውን ሰሪዎች ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ كَتَبْنَا فِى ٱلزَّبُورِ مِنۢ بَعْدِ ٱلذِّكْرِ أَنَّ ٱلْأَرْضَ يَرِثُهَا عِبَادِىَ ٱلصَّٰلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy105. ምድርንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል ማለትን ከመጽሐፉ (ከተጠበቀው ሰሌዳ) በኋላ በመጽሐፎች በእርግጥ ጽፈናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى هَٰذَا لَبَلَٰغًا لِّقَوْمٍ عَٰبِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy106.በዚህ ቁርኣን ውስጥ ያሉት ህግጋት ለአላህ ተገዢ ህዝቦች ሁሉ በቂ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَرْسَلْنَٰكَ إِلَّا رَحْمَةً لِّلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ወደ እኔ የሚወርደው መልዕክት ‹አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው።› የሚል ነው:: ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን?» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُلْ ءَاذَنتُكُمْ عَلَىٰ سَوَآءٍ وَإِنْ أَدْرِىٓ أَقَرِيبٌ أَم بَعِيدٌ مَّا تُوعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እምቢ ቢሉም (እንዲህ) በላቸው: «የታዘዝኩትን በእኩልነት አሳውቂያችኋለሁ:: የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ ወይም ሩቅ መሆኑን አላውቅም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُۥ يَعْلَمُ ٱلْجَهْرَ مِنَ ٱلْقَوْلِ وَيَعْلَمُ مَا تَكْتُمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy110. «እርሱ ከንግግር ጩኸቱን ያውቃል:: የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنْ أَدْرِى لَعَلَّهُۥ فِتْنَةٌ لَّكُمْ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱም ቅጣትን ማቆየት ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጣቀሚያ እንደ ሆነም አላውቅም።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَٰلَ رَبِّ ٱحْكُم بِٱلْحَقِّ وَرَبُّنَا ٱلرَّحْمَٰنُ ٱلْمُسْتَعَانُ عَلَىٰ مَا تَصِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy112. «ጌታዬ ሆይ! በእውነት ፍረድ:: ጌታችንም እጅግ በጣም ሩህሩህን በምትሉት ነገር ላይ መታገዣ ነው።» አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70